Posts

በደቡብ ክልል በከተሞች ለነዋሪዎች ስኳር ስንዴና የምግብ ዘይት ተከፋፈለ

አዋሳ ጥቅምት 22/2005 በደቡብ ክልል ከተሞች ገበያን ለማረጋጋት ባለፉት ሶስት ወራት 27ሺህ 475 ኩንታል ስኳርና ስንዴ እንዲሁም ከ613ሺህ ሊትር በላይ የምግብ ዘይት ለተጠቃሚው መከፋፈሉን የክልሉ ግብይትና ህብረት ስራ ቢሮ ገለፀ፡፡ የቢሮው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የስራ ሂደት ባለቤት አቶ መላኩ እንዳለ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት የፍጆታ ሸቀጦቹ የተከፋፈሉት ሀዋሳን ጨምሮ በክልሉ ከተሞች በሚገኙ 133 የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት አማካኝነት ነው፡፡ ከተከፋፈለው መካከል 19ሺህ 345 ኩንታል ስኳር፣ 8ሺህ 130 ኩንታል ስንዴና ከ613ሺህ ሊትር በላይ የምግብ ዘይት ለአባላትና ለአካባቢው ህብረተሰብ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ባለፉው የበጀት ዓመትም በ123 የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት አማካኝነት ከ2 ነጥብ 5 ሚልዮን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት፣ ከ533ሺህ ኩንታል በላይ ስኳር ፣ የምግብ እህልና የተለያዩ ሸቀጦች በተመሳሳይ ለተጠቃሚዎች መከፋፈሉን ገልጸዋል፡፡

የትናንቱ ጐዳና ተዳዳሪ የዛሬው ብሔራዊ ቡድን ፈርጥ

Image
በደረጀ ጠገናው ብራዚል ለዛሬው የእግር ኳስ ስፖርቷ፣ ክብሯንና ማንነቷን የገነባችው ትናንት ከየጐዳናውና ጉራንጉሩ ትመለምላቸው በነበሩ የኳስ ፈርጦቿ አማካይነት መሆኑ የአደባባይ ሚስጢር ነው፡፡ ከእነዚህ የምንግዜም ዝነኛ የኳስ ክዋክብት መካከል ጋሪንቻና ሌሎችም በርካታ ቁጥር ያላቸው ብራዚላውያን ታዳጊዎች ይጠቀሳሉ፡፡ ገና በለጋ ዕድሜያቸው የሕይወት ውጣ ወረድ ገፈት ሊጋፈጡ የተገደዱት ጋሪንቻና ሌሎቹም የቱንም ያህል እግር ኳስን ቢወዱም፣ የቱንም ያህል ችሎታና ክህሎቱ ቢኖራቸውም በተለይ ጋሪንቻ ‹‹እግረ ደጋን›› እየተባለ ፈላጊ አልነበረውም፡፡ እግሩ ያነክሳልና ለእግር ኳስ አይመጥንም እየተባለ ብዙ ተንከራቷል፡፡ የኋላ ኋላ ግን የኳስ አምላክ ትክከለኛውን የኳስ ግጣም አገናኘና ጋሪንቻ በብራዚል ሜዳዎች ብቻ ሳይሆን በዓለም ዋንጫ መድረኮች ሁሉ ገነነባቸው፡፡ እንደ ጋሪንቻ ሁሉ ሌሎችም ከብራዚል ጐዳናዎች የተገኙ የእግር ኳስ ጠበብት ሮናልዶ ናዛሪዮ ሊዊስ ዴሌማ፣ ሮናልዲኒሆ ጐቹን ጨምሮ ለዓይን የሚታክት በርካታ ፈርጦች ልጥቀስ ይቻላል፡፡ ለመነሻ ያህል ስለብራዚላውያን የጐዳና ፈርጦች አወሳን እንጂ ልናወራ ያሰብነው፣ የኢትዮጵያ ጐዳናዎችም የጨርቅ ኳስን ከእግራቸው አፋቅረው የመንገደኞችን ቀልብ እየገዙ ኳስን የሚያንከባልሉ ጥቂት አይደሉምና የምንለውን ለማለት ነው፡፡ በርካቶች ግን ፈላጊ እያጡ ችሎታቸውን አይቶ ተገቢ ቦታ የሚሰጣቸው ባለማግኘታቸው እየደበዘዙ ሲጠፉ ቆይተዋል፡፡ በዚህ ዘመን ግን አንድ ያልተጠበቀ ጮራ በድንገት ፈንጥቋል፡፡ አስገዳጁና እንዲያም ሲል በጐዳና የጨርቅ ኳሶች ላይ ሲሾሩ የቆዩት የታዳጊ ወጣት እግሮች ቦታቸውን እንዲያገኙ ግድ ብሏል፡፡ በአሁኑ ጊዜም የአገርን ባንዲራ አስከብረው የባላንጣ ውጋት እየሆነ እግሮቹ ምትሀት እያሳዩ ይገኛሉ፡

የስኳር ምርትን ወደ ውጭ ለመላክ ከፍተኛ ጥረት እንደሚደረግ ተገለጸ

Image
አዲስ አበባ፣ጥቅምት 21 ፣2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የስኳር ምርትን ባለፈው ዓመት ወደ ውጭ መላክ ይጀመራል ተብሎ የነበረ ቢሆንም የስኳር ፕሮጀክቶቹ በታሰበላቸው ፍጥነት እየሄዱ እንዳልሆነ ተገለጸ።  የስኳር ኮርፖሬሽን እንደሚለው ለፕሮጀክቶቹ መጓተት ዋነኛው ምክንያት የአቅም ውስንነት ነው።  ቀደምሲልየማስፋፊያስራእየተሳራባቸውየነበሩየስኳርፋብሪካዎችንና ነባርየስኳርፋብሪካዎችንበመጠቀምካለፈውዓመትጀምሮየስኳርምርትለውጭገበያለማቅረብታቅዶየነበረሲሆን፥እንደታቀደውግንማድረግአተቻለም። የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ልዩ አማካሪ አቶ አስፋው ዲንጋሞ እንዳሉት ፥ የኮንትራክተሮችም ሆነ የአማካሪዎች አቅም ውስንነት ፣ የገንዘብ እጥረት ፣ በበቂ የሰው ኃይል አለመደራጀት ፣ ለፕሮጀክቶቹ መጓተት በምክንያትነት ከሚጠቀሱት ውስጥ ዋነኞቹ ናቸው። ከፕሮጀክቶቹ ግዝፈትና ውስብስብነት ጋር በተያያዘም ፥ የስኳር ኮርፖሬሽንም ቢሆን የፕሮጀክት አመራርና አስተዳደር ድክመት እንደነበረበትና፥ በአሁን ወቅት ግን ችግሮቹ በመለየታቸው በያዝነው ዓመት ፕሮጀክቶቹን በአዲስ መልክ ለማፋጠንና ለማጠናቀቅ ርብርብ በመደረግ ላይ መሆኑንም ነው ያስረዱት። ኮርፖሬሽኑ ፕሮጀክቶቹን በአዲስ መልክ ለመምራት እንዲያስችለውም ፥ ባለፉት ሶስስት ወራት ቁልፍ ችግሬ ነበር ላለው የአቅም ውስንነት ትኩረት ሰጥቶ ሰርቷል ፥ እየሰራም ነው። የሰው ኃይሉን አቅም ለማጎልበትም በውጭ ሃገራት ጭምር በመላክ የተለያዩ ስልጠናዎችን እንዲያገኙ እያደረገ ነው። የከሰም ስኳር ፋብሪካ በጣም ከዘገዩት ውስጥ አንዱ ሲሆን ፥ የፋብሪካ ግንባታውንም በዚህ ዓመት በአብዛኛው በማጠናቀቅ በቀጣዩ ዓመት ወደ ማምረት ስራ እንዲገባ ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል ፥ የወልቃይት፣የበለስና ስድስት ፋብሪካዎች የሚገነቡበት የደ

አሥራ አምስት የመንግሥት ሆስፒታሎች የልቀት ማዕከል ሊሆኑ ነው

በታደሰ ገብረ ማርያም በመላ አገሪቱ የሚገኙና በአጠቃላይ የ15 ሚሊዮን ብር ተሸላሚ የነበሩ 15 ምርጥ የመንግሥት ሆስፒታሎችን ከፍተኛና ጥራት ባለው የሕክምና ቴክኖሎጂ በማደራጀት፣ የልቀት ማዕከል እንዲሆኑ የማድረግ እንቅስቃሴ በመከናወን ላይ መሆኑ ታወቀ፡፡ እስካሁን በተካሄደው እንቅስቃሴ አዲስ አበባ ከተማ ለሚገኝ አንድ ምርጥ ሆስፒታል ኤምአርአይ የተባለ ዘመናዊ የሕክምና መሣርያ የቀረበለት መሆኑን፣ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሜዲካል ሰርቪስ ዳይሬክቶሬት ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ ምንጮች በተለይ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የትኛውንም የአካል ክፍል ጥራት ባለው ምስል የሚያሳየው የተራቀቀ ቴክኖሎጂ የቀረበውም ለቅዱስ ጳውሎስ ስፔሻላይዝድ አጠቃላይ ሆስፒታል ነው፡፡ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ ሌሎችም ምርጥ ሆስፒታሎች አቅም በፈቀደ መጠን በየተራ የዚሁ የተራቀቀ ቴክኖሎጂ ባለቤት የሚሆኑበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን ተጠቁሟል፡፡ በመላ አገሪቱ ከሚገኙ 119 የመንግሥት ሆስፒታሎች መካከል፣ 15ቱ ብቻ ምርጥ ተብለው ሊለዩ የቻሉት የተለያዩ ደረጃዎች ያሉትና የተገልጋዩን እርካታ ማዕከል ያደረገ መስፈርት በማውጣት መሆኑን ምንጮች ጠቅሰው፣ የመጀመርያው መስፈርት የሆስፒታሎቹን አገልግሎትና የአፈጻጸም ሁኔታን የሚመለከት መሆኑንና በመስፈርቱ 30 ሆስፒታሎች መመረጣቸውን አስረድተዋል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው መስፈርት ተግባራዊ የሆነው የሰላሳዎቹን ሆስፒታሎች የሕክምና አገልግሎት አሰጣጥን በአካል ተገኝቶ በማየትና በመገምገም ሲሆን፣ በዚህ ዓይነቱም አካሄድ 15 ሆስፒታሎች የሚፈለገውን ደረጃና መስፈርት አሟልተው በመገኘታቸው፣ ‹‹ምርጥ ሆስፒታሎች›› ተብለው መመረጣቸውን ከምንጮች ማብራሪያ ለመዳት ተችሏል፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ ሆስፒታሎች ትብብር ለጥራት›› በሚል ፕሮጀክት አማካይነት መስፈር

መንግሥት ኢሕአዴግንና የንግዱን ኅብረተሰብ ያጣመረ የንግድ የልማት ሠራዊት ሊፈጥር ነው

በዳዊት ታዬ የንግድ ኅብረተሰቡ የሚጠበቅበትን አገራዊ አስተዋጽኦ እንዲወጣ ለማድረግ መንግሥት፣ ኢሕአዴግራና የንግዱን ኅብረተሰብ ያጣመረ የንግድ ልማት ሠራዊት መፍጠር የግድ ነው ሲሉ የንግድ ሚኒስትሩ አስታወቁ፡፡ የንግድ ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ጫኔ ይህንን የገለጹት ትናንት በተካሄደው የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ የምክክር መድረክ ላይ ነው፡፡ በሦስቱ ጥምረት ይመሠረታል የተባለው የንግድ የልማት ሠራዊት አገሪቱ ለጀመረችውና ተግባራዊ በማድረግ ላይ ላለችው ዕቅድ መሳካት ቁልፍ ሚና ይኖረዋል በማለት ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ የንግድ የልማት ሠራዊት መፍጠርን በተመለከተ ሚኒስትሩ በሰጡት ማብራሪያ፣ በሌሎች ዘርፎች እየተፈጠሩ እንዳሉት የልማት ሠራዊቶች ዓይነት አደረጃጀት እንዲኖረው ይደረጋል፡፡ ልማታዊ አስተሳሰብ እንዲኖር ሚኒስቴሩ የንግድ አሠራር ለውጥ እያደረገ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ከበደ፣ የንግድ ኅብረተሰቡን ከሚመለከቱ ሁለት ፓኬጆች ጐን ለጐን የንግድ ልማት ሠራዊት ለመፍጠር ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡ ‹‹በተደጋጋሚ በመገናኛ ብዙኅን እንደምትሰሙት በሦስት አካላት የሚመሠረት ነው፤›› ያሉት የልማት ሠራዊት ጥምረት የሚፈጠረው ‹‹ከገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ፣ ከመንግሥትና ከሚመለከተው የኅብረተሰብ ክፍል ነው፤›› ካሉ በኋላ፣ ‹‹በዚህ ጥምረት መንግሥትን የሚወክለው ንግድ ሚኒስቴር ነው፡፡ ከንግድ ሚኒስቴር አንፃር ሊፈጠር የታሰበው የንግድ ልማት ሠራዊት መንግሥት፣ ኢሕአዴግንና የንግድ ምክር ቤቶችን በጋራ እንዲሠሩ ዕድል ይፈጥራል፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡ ይህም በመግባባትና በመመካከር የሚፈለገውን ወጤት ለማስመዝገብ የሚያስችል መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡ በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ዘመን ማጠቃለያ የንግዱ ዘርፍ 10.47 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ማስገኘት የሚጠበቅበት መሆኑ