ደኢህዴን መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው
አዲስ አበባ (ኢዜአ)፡- የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/ ማዕከላዊ ኮሚቴ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመንን የሁለተኛ ዓመት መደበኛ አፈጻጸምና የታላቁ መሪን የመለስ ዜናዊን ራዕይ ለማሳካት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን በዝርዝር ገመገመ፡፡ ለታላቁ መሪ ጓድ መለስ ዜናዊ የህሊና ጸሎት በማድረግ ማዕከላዊ ኮሚቴው ትናንት በጀመረው መደበኛ ስብሰባ ታላቁ መሪ ባወጡት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች በሚፈጸምበት ዝርዝር ሁኔታ ላይ ተዘጋጅተው በቀረቡ ሰነዶች ላይ በመወያየት አቋም ወስዷል። ድርጅቱ በላከው መግለጫ እንዳብራራው፤ በየደረጃው የሚገኙትን ድርጅታዊ፣ መንግሥታዊና ህዝባዊ አመራሮችንና አደረጃጀቶችን ተቋማዊ በማድረግ የህዳሴውን ጉዞ ለማሳካት በቀረበ ሰነድ ላይ በመወያየት የአፈጻጸም ሰልቶች ተቀይሶ በፍጥነት ተግባራዊ እንዲሆን ውሳኔ አሳልፏል። በገጠር ሥራዎች ረገድ ባለፈው ዓመት በአካባቢ ልማት ጥበቃ የነበረው የህዝብ አደረጃጀት ተሳትፎ ከቀዳሚዎቹ ዓመታት የተሻለ አፈጻጸም የታየበት ሲሆን፤ ወደ በልግ መኸር የግል ማሳ ሥራዎች በመሸጋገር ረገድም በአንዳንድ አካባቢዎች መልካም ውጤቶች መመዝገባቸውን የማዕከላዊ ኮሚቴ አረጋግጧል። ምርትንና ምርታማነትን ለማሳደግ ሁሉንም የቴክኖሎጂ ግብዓቶች እጅ በእጅ በመግዛት ጥመርታውን ጠብቆ ጥቅም ላይ በማዋል ረገድ የነበሩ ክፍተቶችን በዝርዝር መመልከታቸውን መግለጫው ጠቁሟል። በከተሞች በሥራ ፈጠራ፣በቤቶች ልማት፣በማህበራዊና በመሰረተ ልማት ዝርጋታ የታየው ለውጥ የተሻለ ሲሆን፤ በየደረጃው የሚቀርቡ ጥያቄዎችን በአግባቡ ተገንዝቦ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ረገድ የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ጉድለቶችን በቀጣይ ሊታረሙ እንደሚገባ የማዕከላዊ ኮሚቴው አስገንዝቧል፡፡ የኮሚቴው መደበኛ ስብሰባ