Posts

የኢህአዴግ ካድሬዎች ህዝቡ ፍቅሩን ከግለሰብ ወደ ድርጅት እንዲለውጥ ጥረት እንዲያደርጉ ታዘዙ::

ኢሳት ዜና:- ሰሞኑን በመካሄድ ላይ ያለው አቶ መለስ ዜናዊን ልዩ ሰው አድርጎ የመሳል እንቅስቃሴ ድርጅቱን ስጋት ላይ እየጣለው በመምጣቱ ካድሬዎች የፕሮጋንዳ ስራቸውን ከግለሰብ ወደ ድርጅት እንዲያዞሩ ታዘዋል። ኢህአዴግ በመጀመሪያ በአቶ መለስ ዜናዊ የግለሰብ ስብእና አስታኮ ስልጣኑን ለማደላደል የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ቀይሶ የነበረ ቢሆንም፣ የፕሮፓጋንዳው እንቅስቃሴ አቅጣጫውን እየቀየረ መምጣቱ ድርጅቱን ስጋት ላይ ጥሎታል። አቶ መለስ የሁሉም ፕሮጀክቶች አፍላቂ ፣ የኢህአዴግ ጭንቅላት ተደርገው እንዲሳሉ መደረጉ ሌሎች ሰዎች በድርጅቱ ውስጥ እንደሌሉ፣ ድርጅቱ እርሳቸው ከሌሉ ህይወት የሌለው ድርጅት ነው የሚል መልእክት እያስተላለፈ መምጣቱ ሌሎች የደርጅቱን አባላት በተለይም የህወሀት ባለስልጣኖችን  እያበሳጨ ነው። ከሁሉም በላይ ኢህአዴግ ያለመለስ ህይወት አይኖረውም የሚለው አመለካከት በስፋት እንዲሰራጭ ያደረገው የአቶ በረከት ስምኦን የፕሮፓጋንዳ ስልት ነው በሚል ህወሀቶች ወቀሳ እያቀረቡ ነው። ከኢህአዴግ የደህንነት ምንጮቻቸን ባገኘነው መረጃ መሰረት ግንባሩ የፕሮፓጋንዳ ስራው ከግለሰብ ወደ ድርጅት እንዲዞርና የሁሉም መስሪያቤት ሰራተኞች ለኢህአዴግ  ያላቸውን ታማኝነት መግለጥ እንዲጀምሩ መመሪያ አውርደዋል። ኢህአዴግ እንደ ድርጅት ያደረገው አስተዋጽኦ ተረስቶ ሁሉም ነገር አቶ መለስ እንደሆኑ ተደርጎ የሚተላለፈው ቅስቀሳ፣ ድርጅቱን ሰው አልባ አድርጎ ከመሳል በተጨማሪ በድርጅቱ ውስጥ ፈላጭ ቆራጩ አንድ ሰው ብቻ እንደሆኑ ተደርጎ እንዲሳል እያደረገው ነው። ህዝቡ አቶ መለስ ኬለለ ኢህአዴግ የለም የሚል አመለካከት እዬያዘ መምጣቱ እየተነገረ ነው። የኢህአዴግን ስርአት የሚቃወሙትም ከአቶ መለስ በሁዋላ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም መጠየቃቸው የህወሀት

የሥልጣን መተካት በሕገ መንግሥቱ

የዚህ ሰሞን የአገራችን ድባብ ተለውጧል፡፡ ሚዲያው በሐዘን ዜና፣ ሕዝቡም በትካዜ ተውጧል፡፡ በአንድ ሳምንት ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንና የኢትዮጵያ ሕዝብ መሪዎቹን አጥቷል፡፡ ፓትርያርኩም ጠቅላይ ሚኒስትሩም ከነበራቸው አገራዊና አኅጉራዊ ተሰሚነት አንፃር ዜና ዕረፍታቸው አስደንጋጭ ነበር፡፡ በየሚዲያው የምንሰማው የእንጉርጉሮ የዋሽንት ድምፅ፣ በየመንገዱ የተመለከትናቸው ጥቁር አልባሳት፣ የሐዘን መግለጫዎችና ለቅሶዎች ሁሉንም የኩነቱ አካል አድርጎታል፡፡ ‹‹ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ . . . ›› እንዲል ሰዎች ከሞታቸው ጋር የሚኖሩ ቢሆንም፣ መልካም ለሠሩት ወይም ለሚሠሩት የሥራ ጊዜ ቢያገኙ መልካም ነበር፡፡ ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ግን የሥራው መቀጠል፣ የተተኪ አመጣጥ ወዘተ. እኛው ጋ የሚቀሩ ሀቆች ናቸው፡፡ ለዚህም ነው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ‘ዓቃቤ መንበረ ፓትርያርክ’ የኢትዮጵያ መንግሥትም ‘ጊዜያዊ የጠቅላይ ሚኒስትር’ የሾሙት፡፡ የፕትርክናው አመራረጥ አካሄድ በቃለ አዋዲ የሚመራና ለሲኖዶሱ ደንብ የማውጣት፣ ኮሚቴ የማዋቀርና ምርጫውን የማስፈጸም ሥልጣን የተሰጠ ቢሆንም፣ ሥራው የተወሰኑ ተግዳሮቶች እንዳሉት ይታመናል፡፡ የቤተ ክርስቲያኗን አንድነት መጠበቅ፣ አካሄዱን በተቀደሰ መንፈስ መምራት፣ ነገሮችን በጥበብና በጥንቃቄ መፈጸም ግቡን ያሳምረዋል፡፡ የመንግሥትም ጠቅላይ ሚኒስትሩን የመሾም ወይም የመተካት አካሄድ የሚኖረው የሕግ ክርክር ሊኖር እንድሚችል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕመም ላይ በነበሩበት ጊዜ በሪፖርተር ጋዜጣ የተለያዩ አምዶች ላይ ሲስተናገዱ የነበሩ የአቋም ልዩነቶች አመላካች ናቸው፡፡ ክርክሮች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ዜና ዕረፍት በኋላም የሚነሱ በመሆናቸው ሕገ መንግሥቱን መሠረት አድርጎ እልባት መስጠቱ አማራጭ የለውም፡፡ በዚህ ጽሑፍ የሚስተናገደ

Press Statement by Sidama Civil Servants from Hawassa City Administration and Sidama Zone

Image
Press Statement By Sidama Civil Servants from Hawassa City Administration and Sidama Zone, 31 August, 2012 English Version From Hawassa, Sidama, August 31st 2012 We, the Sidama civil servants are deprived of our fundamental rights to leading our daily lives in peace and harmony due to an increased intimidation, harassments and imprisonments that the regime pursues against the Sidama nation for claiming its constitutional rights to regional self administration. The regime's regional cadres with federal forces brutalize Sidama people changing their tactics on daily basis. Despite these, the Sidama nation's continued claims to assert their aforementioned rights further created an atmosphere where the regime deliberately and systematically crushes Sidama civil servants and others members of the Sidama society under the pretext of violating constitution. We express our utter disappointments to doing so. Therefore:- 1. We all the sons and daughters of the Sidama nation u

ሲዳማ ውስጥ ጋብ ብሎ የነበረው እስር ቀጥሏል፤ ሰዎች እውኔት በተናገሩ እየታሰሩ ናቸው

Image
ካላ ኡጋሞ ሃናጋ የተባሉ ግለሰብ በሲዳማ ዞን በማልጋ ወረዳ የወረዳው ነዋሪዎች በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ሰዎችን መታሰራቸው እና በወረዳው ያለው የእስረኞ ኣያያዝ ኣሳሳብ ደረጃ ላይ መሆኑን እና ወደ 56 የምሆኑ እስረኞች በኣንድ ጠባብ ክፍል ለመቆሚያ  እንኳን የምሆን ቦታ በሌለበት ሁኔታ ታስረው እንደምገኙ የምገልጽ መልዕክት በፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ በማስቀመጣቸው የተነሳ መታሰራቸው ብሎም በመከሰሳቸው ተነግሯል። ካላ ኡጋሞ ሃናጋ    Arrest and torture have been commonplace occurrences in Sidamaland and it has been worsened since last June when Sidama public pressed the demand of Self adminstration right. Since then, many Sidamas are languishing in jails illegally. Charges brought up against them are fake and fabricated. For instance, Ougamo Hanaga, who is an employee of Save the Children, made the following comment on facebook about the ordeal of innocent Sidamas and he was arrested few days later. He then charged with terrorism. http://sidamaliberation-front.org/

ባራክ ኦባማ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሥርዓተ ቀብር የሚገኝ ቡድን እንደሚልኩ አስታወቁ

አዲስ አበባ ነሃሴ 25/2004 የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሥርዓተ ቀብር ላይ የሚገኝ የልዑካን ቡድን ዛሬ ይፋ አደረጉ። በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው የፕሬዝዳንቱ ልዑካን በተባበሩት መንግስታት የአሜሪካ ቋሚ ተወካይ በአምባሳደር ሱዛን ራይስ መሪነት ነሐሴ 27 ቀን 2004 ዓ.ም በሚፈጸመው ሥርዓተ ቀብር ላይ ይገኛል። የፕሬዝዳንቱ ልዑካን አባላትም በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ዶናልድ ቡዝ፣ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ፀሃፊ ጆኒ ካርሰን እና የፕሬዝዳንቱ ልዩ አማካሪና የብሔራዊ ደህንነት ከፍተኛ ዳይሬክተር ሚስ ጋይሌ ስሚዝ ናቸው።