Posts

A Call to the Ethiopian Regime to unconditionally stop Systematic and Continuous Violation of the Constitutional rights of the Sidama People!

New United Sidama Parties for Freedom and Justice (USPFJ)  J)   Press Release, June 10, 2012    The Systematic and Continued Violations of Human Rights by the Ethiopian  Regime     The current Ethiopian regime continues to grossly violate the rights of its citizens disregarding its own constitution that guarantees these rights. Human misery and suffering continues amid abject poverty, high diseases burden and lack of respect to fundamental human rights such as freedom of expression, assembly, and continued intolerance to diverging ideas and opinions.    The complete absence of the aforementioned essential elements in a modern democratic principle makes the current Ethiopian regime the only place on the planet where the disciples of darkness lead the country towards an unpredictable end. The regime does conduct such hideous actions enjoying the support of Western powers politicians whose vested  interests outweigh the sufferings of over 85 million Ethiopians althou

የፌደራሉ መንግስትና የሲዳማ ዞን በአዋሳ እጣ ፈንታ ላይ ውጥረት የበዛበት ውይይት እያካሄዱ ነው

New ሰኔ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌደራል መንግስቱ አዋሳን በስሩ ለማድረግ እቅድ እንዳለው ሲታወቅ፣ የሲዳማ ዞን በበኩሉ ድርጊቱን ይቃመዋል። በቅርቡ በተደረገው ውይይት ላይ አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበር፣ የሲዳማ ዞን ባለስልጣናትም የፌደራል መንግስቱ ባለስልጣናት የሚመሩትን ስብሰባ ረግጠው መውጣታቸውንና ጉዳዩን ከፌደራል መንግስት ባለስልጣናት እውቅና ውጭ እያካሄዱት ነው። አዲሱ ውዝግብ የአዋሳን ህዝብ ትኩረት መያዙም ታውቋል። በ1994 ኣም በፌደራል መንግስትና በዞኑ መካከል በተፈጠረው አለመግባባት  ከ40 እስከ 100 የሚደርሱ የሲዳማ ተወላጆች መገደላቸው ይታወሳል። የመለስ መንግስት ከፍተኛ የህዝብ እልቂት ያስከተለውን የቆየ ችግር መልሶ በማምጣት ሌላ ችግር ለመፍጠር ለምን እንደተነሳሳ ግልጽ የሆነ ነገር የለም ይላሉ የአካባቢው ነዋሪዎች። http://www.ethsat.com/2012/06/09/%E1%8B%A8%E1%8D%8C%E1%8B%B0%E1%88%AB%E1%88%89-%E1%88%98%E1%8A%95%E1%8C%8D%E1%88%B5%E1%89%B5%E1%8A%93-%E1%8B%A8%E1%88%B2%E1%8B%B3%E1%88%9B-%E1%8B%9E%E1%8A%95-%E1%89%A0%E1%8A%A0%E1%8B%8B%E1%88%B3/

የሲዳማን ህዝብ ራሱን በራሱ የማስተዳደር ህገ መንግስታዊ መብት መጣስ ማለት የኢትዮጵያን ህገ መንግስት መናድ ስለሆነ ሁሉም ብሄርና ብሄረስብ ከሲዳማ ህዝብ ጎን ሊቆም እንደምገባ ተገለጸ:: በሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ውስጥ 30 ከመቶ የሚሆነውን የኣስተዳደር ቦታ በሌሎች ብሄር እንዲያዝ በሚል የተቀመጠውን የኢህኣዴግ ኣቅጣጫ የሲዳማን ህዝብ ራሱን በራሱ የማስተዳደር ህገ መንግስታዊ መብቱን የጣሰ ነው በሚል ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል::

New የሲዳማን ህዝብ ራሱን በራሱ የማስተዳደር ህገ መንግስታዊ መብት መጣስ ማለት የኢትዮጵያን ህገ መንግስት መናድ ስለሆነ ሁሉም ብሄርና ብሄረስብ ከሲዳማ ህዝብ ጎን ሊቆም እንደምገባ ተገለጸ:: በሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ውስጥ 30 ከመቶ የሚሆነውን የኣስተዳደር ቦታ በሌሎች ብሄር እንዲያዝ በምል የተቀመጠውን የኢህኣዴግ ኣቅጣጫ የሲዳማን ህዝብ ራሱን በራሱ የማስተዳደር ህገ መንግስታዊ መብቱን የጣሰ ነው በሚል ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል:: እስከ ኣሁን በይፋ ያልተነገረው ነገር ግን ለወራት ውስጥ ለውስጥ በህዝቡ ዘንድ ስወራ የቆየው በሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ውስጥ ከሲዳማ ብሄር ውጪ ሌሎች ብሄሮችን የመቀላቀል ጉዳይ በተለይ የሲዳማ ተወላጆች ክፉኛ ያስቆጣ ሲሆን የኢህኣዴግ መንግስት በሲዳማ ህዝብ ዘንድ ያለውን ደጋፊ ሊያሳጣው ይችላል ተብሏል::   ጉዳዩን በትኩረት ስጥተው በመከታተል ላይ የሚገኙ ግለሰቦች እንደምሉት ከሆነ፥ የኢትዮጵያ ህገ መንግስት የኣገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች እራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር መብት ካጎናጸፈ ከ 20 ኣመታት በኋላ የሃዋሳን ከተማ ኣስተዳደር የሲዳማ ህዝብ ከሌላው ብሄር ጋር እንድጋራ ለማድረግ የምደረገው እንቅስቃሴ የኣገሩቱን ህገ መንግስት እንደመናድ ይቆጠራል:: የኢህኣዴግ ኣመራር በራሱ ኣስተዳደር ውስጥ ያለውን የመልካም ኣስተዳደር ችግር ለመቅረፍ ኣጥጋቢ የሆነ እርምጃ ካለመውሰዱ በላይ በመልካም ኣስተዳደር እጦት በመሰቃየት ላይ የምገኘው የሲዳማ ህዝብ እራሱ በራሱ የማስተዳደር መብት ለማፈን እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ '' እንኳን ዘንባብሽ ….'' ኣይነት እንደሆነባቸው ኣንዳንድ የብሄሩ ተዋላጆች ተናግረዋል:: በከፍተኛ የኢህኣዴግ ኣመራሮች ሊወሰድ ነው እየተባለ የ

ጫፍ ፍቅር ሀይቅ ጋ ወራጅ አለ!

Image
አዲስ አበባ የምር ናፍቃኛለች፡፡ ልክ ፍቅረኛውን ፒያሣ መሀሙድ ጋር እንደቀጠረ ጐረምሳ፡፡ እኔ አዋሳ ነው ያለሁት፡፡ አዋሳ ደግሞ ሙቀት አለ፡፡ ሙቀት ስላችሁ የፀሐይ እንዳይመስላችሁ፡፡ የመሬት ሙስና የወለደው የፖለቲካ ሙቀት እንጂ፡፡ እሳት እንደነካው ፌስታል አንጀት የሚያኮማትር ትኩሳት! እንጨት እንደወጋው የፊት ቁስል ሆድ የሚያሳምም ወላፈን! ቀጣዩ በረሀ ወለድ ሃሜት ግን ጭራሽኑ ተስፋ አስቆረጠኝ፡፡ የፌደራሉ መንግስት ሀዋሳን እንደ ማደጐ ልጅ ወስዶ በሞግዚትነት ሊያሳድጋት ነው፡፡ አላመንኩም፤ አይደረግም ብዬም ልጮህ ነበር፡፡ አላደረኩትም፡፡ የመንግስቴን ሰምና ወርቅ ፀባይ አውቀዋለሁ፡፡ ብዙም ሳይቆይ የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ሽፈራው ሽጉጤ “የሆነ በሬ ወለደ ዓይነት የኪራይ ሰብሳቢዎች አሉባልታ” ሲሉ ጭንቀቴ ላይ ቀዝቃዛ ልማታዊ ውሀ አፈሰሱበት፡፡ አዋሳ ላንጋኖ ለሽርሽር ሄጄ ያየሁሽ… ይገባኛል፡፡ ከአዱ ገነት መውጣት ያስጨንቃል፡፡ መራቅ ያስፈራል፡፡ መሸሽ ሆድ ያባባል፡፡ ደግሞስ ወዴት ይኬዳል? የክፍለ ሀገራት ቅጥ ያጣ የዘውጌ ፖለቲካ፣ ወንዝ የማያሻግር የሠፈር ኢኮኖሚ እና ባህላዊ የአኗኗር ዘይቤያቸው አንገት ያስደፋል፡፡ በዚያ ላይ ባቅላባ የላቸውም፡፡ የኛ ዓላማ ግን አዋሳን መውረር ነውና የምግብ ጥያቄ ተቀባይነት የለውም፡፡ ታጋይ ሆዳም ነው እንዴ? የመሀል ሠፈሪ ልጆች አዲስ ከተማ ት/ቤት ጐን ካለው መነሀርያ ትኬት መቁረጥ ትችላላችሁ፡፡ ከሳሪስ በታች ወይም የጥጉ መደብ ባለቤቶች፡፡  ከአዲሱ የቃሊቲ መነሀሪያም የአዋሳን “በሮ ገዳይ” ሚኒባሶች ታገኛላችሁ፡፡ ዕቃ እንዳትረሱ፡፡ መታወቂያ ካሜራ፣ ደብተር፣ ብዕር፣ እርሳስ፡፡ ት/ቤት የምንሄድ አስመሰልኩት እንዴ? በፍፁም! አዋሳ ለሚቆዝም፣ ለሚያዜም፣ ለሚጽፍና ለሞንጭሮ አደር ተመራጭ ናት፡፡

በሃዋሳ ነጋዴዎች የሞባይል ካርድ ከታሪፍ በላይ እየሸጡ ነው

ሀዋሳ (ኢዜአ)፡- ኢትዮ ቴሌ ኮም በተመን የሚያከፋፍለውን የሙባይል ካርድ የሀዋሳ ከተማ ነጋዴዎች ከታሪፍ በላይ እየሸጡ መሆኑን አንዳንድ የቴሌ ደንበኞች ገለጹ፡፡ ኢትዮ ቴሌ ኮም በበኩሉ «ከታሪፍ በላይ መሸጥ ወንጀል በመሆኑ እርምጃ እየወሰድኩ ነው» ብሏል፡፡ ፖሊስ ደግሞ ድርጊቱን ሲፈፅሙ የተገኙትን ተከታትሎ በህግ እንደሚጠይቅ አመልክቷል፡፡ በከተማው ከሚገኙ የቴሌ ደንበኞች መካከል አቶ አብነት ደሜ፣ አቶ ሞገስ አይሶና የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሙሉ አበበ ከትናንት በስቲያ በሰጡት አስተያየት፤ ኢትዮ ቴሌ ኮም በተመኑ ለነጋዴዎች የሚያከፋፍለው የሞባይል ካርድ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከታሪፍ በላይ እየገዙ ነው። ነጋዴዎቹ ከታሪፍ በላይ የሚሸጡት ባለ አምስት ብሩ ላይ 50 ሳንቲም በመጨመርና ዋጋቸው ከፍ ባሉት ካርዶች ላይ ደግሞ የአንድና የሁለት ብር ጭማሪ በማድረግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ተጠቃሚዎቹ «ለምን?» ብለው ሲጠይቁ፤ «ብትፈልጉ ግዙ አለበለዚያ መተው ትችላላችሁ» የሚል ምላሽ እንደሚሰጧቸው አመልክተው፤ አማራጭ አጥተው በተባሉት ዋጋ ለመግዛት መገደዳቸውን ገልጸዋል፡፡ የሞባይል ካርድ ከቴሌ ተረክበው ከሚሸጡት መካከል ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ አንዳንድ ነጋዴዎች ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ፤ በተመኑ እንደሚሸጡ ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ሪፖርተር ተዘዋውሮ እንደታዘበው ግን ነጋዴዎቹ ከተመን በላይ እንደሚሸጡ አረጋግጧል፡፡ የኢትዮ ቴሌ ኮም የኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ አብዱራሂም አህመድ ስለጉዳዩ በስልክ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ፤ «ማንኛውም ነጋዴ ከቴሌ በተመኑ የተረከበውን የሞባይል ካርድ ላይ በገባው የውል ስምምነት መሰረት ኮሚሽን ያለው ሲሆን ከታሪፍ በላይ መሸጥ ግን ወንጀል ነው» ብለዋል፡፡ በሌሎችም አንዳንድ ከተሞች ነጋዴዎቹ የገቡትን ውል ተላልፈው ከታሪፍ