Posts

New State of the Art Southern Nationalities, Nations and Peoples Region Regional Laboratory in Hawassa City

Image
New State of the Art Southern Nationalities, Nations and Peoples Region Regional Laboratory in Hawassa City Fig 1: His Excellency President Shiferaw Shegute Right top corner: Rendering of the SNNPR Regional laboratory SNNPR President H.E Shiferaw Shegute, Ethiopian Minister of Health, Dr. Tedros Adhanom, Ato Kare Chawicha Regional Health Bureau Head and Country Director of the United States’ Center for Disease Control and Prevention (CDC) Dr. Tom Kenyon, and invited guests broke ground on the construction of a new SNNPR Regional Laboratory in the city of Hawassa in SNNPR on June 30, 2011 within walking distance from the Hawassa Regional Referral Hospital The New SNNPR Regional Laboratory will augment the current Hawassa Regional Laboratory, which is one of the six regional labs in the country to be upgraded to support DNA PCR and TB culture, DST and Molecular Diagnostic Laboratory supporting four sub-regional laboratories situated in Hossana, Arbaminch, Mizan and Jinka. The Ne

በደቡብ ክልል አዲሱ የሊዝ አዋጅ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል -የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር

Image
በደቡብ ክልል አዲሱ የሊዝ አዋጅ ከዛሬ ጀምሮ በየደረጃው ተግባራዊ እንደሚሆን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የንግድ ፣ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ሀላፊ አስታወቁ ። በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና ህብረተሰቡም ለአዋጁ ተግባራዊነት የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የቢሮው ሃላፊ አቶ ታገሰ ጫፎ ትናንት ለጋዜጠኞች እንደገለጹት በሀገር ደረጃ ህዳር 18/2004 የጸደቀው አዲሱ የሊዝ አዋጅ የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ነው፡፡ መሬት የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዘቦች የጋራ ሀብት እንደመሆኑ የከተማ ቦታ በሊዝ ጨረታ ወስዶ ያለማ ሰው እሴት እንደሚፈጥርለትና ተጠቃሚ እንደሚሆን አስታዉቀዋል ። በአዋጁ መሰረት የተከለከለው ባዶ መሬት በሊዝ ከወሰደ በኋላ ሳይሰራበት መሬቱን አሲዞ አለአግባብ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ብር ከባንክ መበደርና መሸጥ ነው ብለዋል፡፡ መሬት ልማታዊ ባልሆነ መንገድ ወስዶ በአቋራጭ መበልጸግና ሀብት ማግበስበስ እንደማይቻል በአዋጁ ላይ በግልጽ መደንገጉን ያስረዱት አቶ ታገሰ በዚህ ዐይነት ህገ ወጥ አካሄድ የመሬት ዋጋ ጣሪያ ከመድረሱም በላይ ለልማት የሚውለው ገንዘብ በመሬት ግዥና ሽያጭ እየባከነ ችግር መፍጠሩን ተናግረዋል፡፡ የመሬት አስተዳደር ስርዓትና የመሬት አቅርቦትን ከከራይ ሰብሳቢነት የጸዳ ለማድረግ አዋጁ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው አመልከተው በፕላን መሰረት ቤት የሰራና በዙሪያው ያለማውን ሀብት መሸጥ እንደሚችል ፣ ነገር ግን መሰረት በመጣልና ከ50 በመቶ በታች ግንባታ በማካሄድ በከፍተኛ ገንዘብ መሸጥ የማይቻል መሆኑን ህዝቡ በግልጽ መገንዘብ እንዳለበት አስረድተዋል፡፡ ነባር ይዞታዎች በውርስ ማስተላላፍ እንጂ ወደ ሊዝ የሚገባን መሬት ለሶስተኛ ወገን

Ethiopian Coffee Exports Decline

The export of coffee from  Ethiopia  has declined by 38% in the first eight months of the financial year, as compared to the same period last, according to data from players in the sector. The Ethiopia Commodity Exchange has consequently eliminated the 5% +/- price range for coffee intended to regulate against price fluctuations on the international market last week. The range will not be applicable on the trading floor of  Exchange until the price of coffee stabilizes on the international market said Dr. Eleni Z. Gebremedhin, Chief Executive of the ECX. It is estimated that the annual coffee production of Ethiopia for this harvest year will be 8,312,000 bags or 498,720 tons according to forecasts made by the International Coffee Organization.  Ethiopia expects to export 50% of its coffee production amounting to an estimated 249.5 tons this year. Coffee exports in the first eight months of the fiscal year, however have only added up to 75,000 tons. The decrease in  coffee sh

የቡና ዋጋ ወሰን ሙሉ ለሙሉ ተነሳ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የቡና መገበያያ  የዋጋ ወሰንን ከትናንት በስቲያ ገበያ መዝጊያ ዋጋ አኳያ ወደ ላይና ወደ ታች የአምስት በመቶ ጭማሪና ቅናሽ እንዲያሳይ በማድረግ ሲያገበያይበት የነበረውን አሠራር ላልተወሰነ ጊዜ ማንሳቱን አስታወቀ፡፡ የምርት ገበያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር እሌኒ ገብረ መድኅን ለሪፖርተር እንዳስታወቁት፣ የዋጋውን ወሰን ማንሳት ያስፈለገው በኒውዮርክ ዓለም አቀፍ ገበያ ከጊዜ ወደጊዜ እያሽቆለቆለ የመጣው የቡና ዋጋ፣ ባለፈው ሐሙስ ዕለት በፓውንድ (ግማሽ ኪሎ ገደማ) አንድ ዶላር ከሰባ አምስት ሳንቲም የሆነ ዝቅተኛ ዋጋ በማስመዝገቡ የዋጋ ወሰኑን ሙሉ ለሙሉ ማንሳት አስፈልጓል፡፡ የዓለም የቡና ዋጋ እስኪስተካከል ድረስ የዋጋ ወሰኑ ሙሉ ለሙሉ ተነስቶ እንደሚቆይ የገለጹት ዶክተር እሌኒ፣ የአገር ውስጥ አቅራቢዎች የቡና ዋጋ መው ረዱን የማይቀበሉት ከዚህ ቀደም የተሻለ ዋጋ ለማግኘት አስበው በእጃቸው ያቆዩት ቡና ይበልጥ ዋጋው ሲወርድ ለኪሳራ ስለሚያጋልጣቸው ነው ብለዋል፡፡ ይህም ሆኖ አቅራቢዎች በግድ ሽጡ እንዳልተባሉ ገልጸው፣ ምርቱን በእጃቸው ከማቆየት ይልቅ ግን እንዲህ ያለ ያልታሰበ የዋጋ ማሽቆልቆል እንዳይከሰት በእጃቸው ያለውን ቡና ቶሎ ለገበያ እንዲያቀርቡ መክረዋል፡፡ ከሦስት ወራት በፊት የቡና ዋጋ እስኪጨምር ድረስ ምርቱን በእጃቸው ይዘው ሲጠባበቁ የነበሩ አቅራቢዎች የዋጋው መውረድ እንደጎዳቸው ገልጸው፣ አምና በፓውንድ ሦስት ዶላር ያወጣ የነበረው ቡና ባለፈው ወር ወደ ሁለት ዶላር ሊወርድ መቻሉን አስረድተዋል፡፡ በዚህ ያላቆመው የዋጋ ማሽቆልቆል ከሁለት ሳምንት በፊት የኒውዮርክ ገበያ ዋጋው ወደ አንድ ዶላር ከዘጠና ሊወርድ መቻሉን፣ ባለፈው ሐሙስ ደግሞ ብሶበት አንድ ዶላር ከሰባ አምስት ሳንቲም ማውጣቱን ይገልጻሉ፡፡  በአንፃሩ በምርት

በሐዋሳ በተነሳው የእሳት አደጋ ንብረት አወደመ: በሐዋሳ ከተማ የንግድ ተቋማት ባለንብረቶች: ከኢንሹራንስ ይልቅ ማኅበራዊ ተራድኦን የሚመርጡ መሆናቸው ተነገረ

Image
 በአደጋው የከተማው አስተዳደር እሳት አደጋ መከላከል አቅም ተፈትሿል መጋቢት 9 ቀን 2004 ዓ.ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ገደማ በሐዋሳ ከተማ ፒያሳ አካባቢ በሁለት መደብሮች የተነሳው እሳት ንብረት አወደመ:: ወደ ክብሩ ሆስፒታል መሄጃ ላይ እየሩሳሌም የጨርቃ ጨርቅ መደብርንና አጠገቡ ያለው ጥሩወርቅ የኮምፒውተር ጽሕፈት አገልግሎት በእሳቱ ሙሉ በሙሉ የወደሙ ሲሆን፣ ባለንብረቶቹ እንደሚሉት 1.3 ሚሊዮን ብር የሚገመት የንብረት ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት በተነሳው እሳት የእሳት አደጋ መከላከያ በወቅቱ ባለመድረሱና ዘግይቶ ከደረሰም በኋላ አቅሙ ውስን በመሆኑ፣ በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት ማዳን እንዳልተቻለ የዓይን እማኞች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ እንደ እማኞቹ አስተያየት ያለምንም መከላከያ ለ20 ደቂቃዎች ያህል ሲቀጣጠል የነበረው እሳት፣ በመደብሮች ውስጥ የነበሩትን ጨርቃ ጨርቆችና ኮምፒውተሮች በፍጥነት ጋይተዋል፡፡ የእየሩሳሌም ጨርቃ ጨርቅ መደብር ባለቤት አቶ ጌቱ ደምቦባ ስለደረሰው ጉዳት ተጠይቀው፣ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ጣቃዎችና የተዘጋጁ ልብሶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ገልጸው፣ የእሳቱን መንስዔ በተመለከተ ለተጠየቁት ሲመልሱ፣ ማናቸውንም የኤሌክትሪክ ዕቃዎችንና ካውያዎችን በአግባቡ ካጠፉ በኋላ መደብራቸውን መዝጋታቸውንና እሳቱ ከየት እንደተነሳ እንደማያውቁ ለሪፖርተር ጠቁመዋል፡፡ የጥሩወርቅ ኮምፒውተር ጽሕፈት አገልግሎት ባለቤት በበኩላቸው፣ ከ300 ሺሕ ብር በላይ የሚገመቱ ኮምፒውተሮችና የፎቶ ኮፒ ማሽኖች እንዲሁም የስቴሽነሪ ቁሳቁሶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ገልጸዋል፡፡ በምሽቱ የተፈጠረውን እሳት ለመከላከል የሐዋሳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ የእሳት አደጋ መከላከያና የከተማው የእሳት አደጋ መከላከያ በአጠቃላይ ሦስት ተሽከ