በደቡብ ክልል ከ17ሺህ ለሚበልጡ ህፃናት የህፃን ለህፃናት ትምህርት ሊሰጥ ነው::በሲዳማ ዞን በዳራ ወረዳ በ2003 የትምህርት ዘመን የህፃን ለህፃን ትምህርት ፕሮግራም በሙከራ ደረጃ ተጀምሮ ውጤታማ መሆኑን ተልጸዋል፡
New አዋሳ, የካቲት 28 ቀን 2004 (ሃዋሳ) - በደቡብ ክልል ከ17 ሺህ ለሚበልጡ ህፃናት የህፃን ለህፃናት አቀራረብ ዘዴን በመጠቀም የቅድመ መደበኛ ትምህርት ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለጸ፡፡ በፕሮግራሙ ከስድስተኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል በትምህርታቸው የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ከአምስት ሺህ የሚበልጡ ጎበዝ ተማሪዎች በማስተማሩ ስራ ላይ ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡ የትምህርት አሰጣጥ ሂደቱን በመደገፍ የቁጥጥርና ክትትል ስራዎችን ለሚያከናውኑ ርዕሳነ መምህራን ፣ መምህራን፣ ሱፐር ቫይዘሮችና የወላጅ መምህር ህብረት ተወካዮች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ የቢሮው መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የስራ ሂደት ተወካይ ወይዘሮ እናኑ ብዙነህ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት የቅድመ መደበኛ ትምህርትና ክብካቤ የህፃናትን አካልና አዕምሮ በማዳበር ለመደበኛ ትምህርት ለማዘጋጀትና መሰረት ለመጣል ቁልፍ ድርሻ አለው፡፡ አስተማማኝ ድጋፍና ክብካቤ ያገኙ ህፃናት ለመደበኛ ትምህርት በጥሩ ሁኔታ እንዲዘጋጁ ስለሚያደረጋቸው ወደ መደበኛ ትምህርት ሲገቡ ለየደረጃው የተዘጋጀውን ስርዓተ ትምህርት በቀላሉ መረዳት እንደሚችሉና አጥጋቢ የመማር ብቃት መመዘኛዎችን አሟልተው ወደ ሚቀጥሉት እርከኖች መሸጋገር ይችላሉ ብለዋል፡፡ በክልሉ በሲዳማ ዞን በዳራ ወረዳ በ2003 የትምህርት ዘመን የህፃን ለህፃን ትምህርት ፕሮግራም በሙከራ ደረጃ ተጀምሮ ውጤታማ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የክልሉ ትምህርት ቢሮ በወረዳው የተገኘውን ምርጥ ተሞክሮ በመቀመር ፕሮግራሙን በክልሉ ሁሉም አካባቢ በማስፋፋት እድሜያቸው ከሶስት እስከ ስድስት ዓመት የሆኑ ህፃናትን ተጠቃሚ ለማደረግ እየሰራ መሆኑን ወይዘሮ እናኑ ገልጸው በ2004 በጀት ዓመት በአራት ዞ