በዛሬው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች የሲዳማ ክለቦች ድል ቀንቷቸዋል
  አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 22፣ 2006 ( ኤፍ.ቢ.ሲ )  የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በተለያዩ  ጨዋታዎች በዛሬው እለት ቀጥሏል።   በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረጉ ጨዋታዎች ፥  የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ አስራ አንደኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ከመብራት ሀይል በ9 ሰዓት ተገናኝቶ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ረቷል።   በተመሳሳይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሲዳማ ቡና 11 ከ 30 ላይ ተገናኝተው  ፥ ጨዋታው በሲዳማ ቡና 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል። ።   በክልል ጨዋታዎች በደቡብ ደርቢ ሀዋሳ ከነማ አርባ ምንጭ ከነማን ፣ ቦዲቲ ላይ ወላይታ ዲቻ ኢትዮጵያ ቡናን በተመሳሳይ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት  መርታት ችለዋል።   ደደቢት በበኩሉ በአበበ በቂላ ስታዲየም በወራጅ ቀጠና ላይ የሚገኘውን ሀረር ከተማን  በ10 ሰዓት አስተናግዶ 1 ለ 1 ተለያይቷል።   
 
 
 
 
