Posts

The player left St. George FC by mutual consent after five years

Uganda Cranes central defender Isaac Isinde is on the verge of joining Ethiopian side Hawassa F.C. Isinde was last month released by another Ethiopian side St. George . The player left St. George FC by mutual consent after five years. Reports from Ethiopia indicate that St. George FC were reluctant to renew Isinde's contract after they recruited younger defenders. Sources indicate that Isinde's move to Hawassa F.C will be completed after the 2017 AFCON that is going on in Gabon. Isinde is currently part of the Uganda Cranes squad for the Africa Nations Cup finals in Port Gentil, Gabon. - See more at: http://www.newvision.co.ug/new_vision/news/1444500/isinde-join-hawassa-fc#sthash.3mbBsRA7.dpuf

​‹‹ከፍተኛ አመራሩ ተጠያቂ ያልሆነው ማስረጃ ስለሌለ ነው›› ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ

Image
ለመሆኑ የዛሬ 15 ኣመት ከሲዳማ የክልል ጥያቄ ጋር በተያያዘ ለተነሳው ጥያቄ የጥይት እሩምታ ምላሽ በመስጠት ለበርካታ ንጽሃን ሲዳማዎች እልቂት ምክንያት የሆኑት የዛሬዎቹ ከፍተኛ ኣመራሮች የማይጠየቁት መረጃ ጠፊቶ ነውን? የኣገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰሞኑን በኣጠቃላይ ወቅታዊ ፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ከጋዜጠኞች ጋር የተወያዩ ሲሆን፤ የገዥውን ፓርቲ ከፍተኛ ኣመራሮችን በተመለከተ ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል የከፍተኛ ኣመራር ተጠያቂነትን የተመለከቱ ሲሆን፣ '' ከፍተኛ አመራሩ ተጠያቂ ያልሆነው ማስረጃ ስለሌለ ነው''ብለዋል። ለመሆኑ የዛሬ 15 ኣመት ከሲዳማ የክልል ጥያቄ ጋር በተያያዘ ለተነሳው ጥያቄ የጥይት እሩምታ ምላሽ በመስጠት ከበርካታ ንጽሃን ሲዳማዎች እልቂት ምክንያት የሆኑት የዛሬዎቹ ከፍተኛ ኣመራሮች የማይጠየቱት መረጃ ጠፊቶ ነው?ለማንኛውም ዝርዝር ወሬው ከታች ያንቡ፦  ፎቶ  ከሪፖሪተር ጋዜጣ  ​ ‹‹ከፍተኛ አመራሩ ተጠያቂ ያልሆነው ማስረጃ ስለሌለ ነው›› ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ -  ማስረጃ ከተገኘ የትኛውንም አመራር አንተውም ብለዋል -  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማንሳት የሚያጣድፍ ነገር አለመኖሩን ጠቁመዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ መደበኛውን ጋዜጣዊ መግለጫ ከሰጡ ሁለት ዓመት ገደማ ሆኖታል፡፡ ባለፈው ሰኞ ጥር 1 ቀን 2009 ዓ.ም. የግሉን ፕሬስ ጨምሮ ለውጭ ጋዜጠኞች በጽሕፈት ቤታቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር፡፡ በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተገኙ ጋዜጠኞች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተለያዩ ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡ ዋና ዋና ከሚባሉት መካከል የመንግሥት ከፍተኛ አመራሮች ሥልጣንን ለግል ጥቅም ማዋልና አለመጠየቅ፣ በአጥፊዎች ላይም ዕርምጃ

የሲዳማ ቡና ኣብቃዮች እና ያልከፈሉት በቢሊዮኖች የምቆጠር ውዝፍ እዳ

Image
የደቡብ ክልል ቡና አቅራቢዎች ያጋጠማቸውን ኪሳራ በማስመልከት ባለፈው ዓመት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ በፋይናንስ ኢንዲስትሪው ውስጥ እንግዳ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል፡፡ ብሔራዊ ባንክ ሰኔ 10 ቀን 2008 ዓ.ም. ይፋ ያደረገው መመርያ፣ በባንክ ዘርፉ ውስጥ ያለተለመደ ስለነበር ጉዳዩ ሲያነጋግር ቆይቷል፡፡ ገዥው ባንክ የአገሪቱ ባንኮች እንዲተገብሩት ያስተላለፈው ሰርኩላር፣ ከተለያዩ ባንኮች ብድር የወሰዱ የደቡብ ክልል ቡና አቅራቢዎች የነበረባቸውን የብድር ዕዳ ከሌሎች ተበዳሪዎች በተለየ እንዲታይና ለብድር አከፋፈል ከተቀመጠው መመርያ ውጭ እንዲስተናገድ የሚያዝ ነው፡፡ የአገሪቱ ባንኮች የሚሰጡትን ብድር እንዲሁም የአመላለስ ሥርዓቱን የተመለከተው ይህ የገዥው ባንክ መመርያ፣ ለአንድ ብድር የተሰጠው የመክፈያ ጊዜ ከሦስት ጊዜ በላይ ማራዘም ወይም ማስታመም እንደማይቻል ይደነግጋል፡፡ የደቡብ ቡና አቅራቢዎች ግን ይህ መመርያ ሳይተገበርባቸው እንዲስተናገዱ ብሔራዊ ባንክ  ለንግድ ባንኮች የላከው ሰርኩላር ያሳስባል፡፡    ቡና አቅራቢዎቹ ከዚህ መመርያ ውጭ ብድራቸው ከሦስት ጊዜ በላይ እንዲራዘምላቸው ከመፍቀዱም ባሻገር የነበረባቸውን ውዝፍ ብድር በወቅቱ ባለመክፈላቸው ለማስያዣነት ያቀረቧቸው ንብረቶችም እንዳይሸጡ የሚከላከል ነው፡፡ በብሔራዊ ባንክ ለአጭርና ለመካከለኛ ጊዜ ተበዳሪዎች የብድር ማስታመሚያ ጊዜ እንደተሰጠ የሚገልጸው አንቀጽ፣ ቡና አቅራቢዎቹ ላይ እስከ መጪው 2010 ዓ.ም. ድረስ ተፈጻሚ እንዳይሆን የሚያዝ የሁለት ዓመት የዕፎይታ ጊዜ ሰጥቷል፡፡ በዚህ ሰርኩላር ምክንያት ባንኮች ለሰጡት ብድር መያዣ የነበሩ ንብረቶችን በሐራጅ ለመሸጥ ሲያነጋግሩ የነበሩትን የሐራጅ ማስታወቂያ አቁመዋል፡፡ ለቡና አቅራቢዎቹ የተሰጠው ይህ ዕድል፣ ከ200 በላይ የደ