Posts

ለዝናብ እጥረት ተጐጂዎች የ230 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ ተጠየቀ

Image
- 4.5 ሚሊዮን ሕዝብ ዕርዳታ ይፈልጋል የኢትዮጵያ መንግሥትና ለጋሾች በጋራ በመሆን ባወጡት የሰብዓዊ ድጋፍ ሰነድ፣ በክረምት ዝናብ እጥረት ምክንያት 230 ሚሊዮን ዶላር ሰብዓዊ ዕርዳታ እንደሚያስፈልግ ይፋ አደረጉ፡፡  ነሐሴ 18 ቀን 2007 ዓ.ም. የኢትዮጵያ መንግሥት ተወካዮችና ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ድርጅቶች ባወጡት መግለጫ፣ እ.ኤ.አ. በማርች 2015 ወጥቶ የነበረውን የሰብዓዊ ዕርዳታ ሰነድ በመከለስ፣ ቀደም ሲል ተገምቶ ከነበረው በተጨማሪ 1.6 ሚሊዮን ሕዝብ የሰብዓዊ ዕርዳታ እንደሚያስፈልገው ገልጸዋል፡፡  የዚህ ምክንያቱም በበልግና በክረምት ወቅቶች በኢትዮጵያ የታየው የዝናብ እጥረት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም ቀደም ሲል ሰብዓዊ ዕርዳታ ያስፈልገዋል ተብሎ ተገምቶ ከነበረው 2.9 ሚሊዮን ሕዝብ በተጨማሪ 1.6 ሚሊዮን ሕዝብ የሰብዓዊ ዕርዳታ በመሻቱ፣ አጠቃላይ የተረጂዎች ቁጥርን 4.5 ሚሊዮን እንዳደረሰው የመንግሥትና የሰብዓዊ ድርጅቶቹ የጋራ መግለጫ ያስረዳል፡፡ ለአፋጣኝ የሰብዓዊ ዕርዳታ ፍላጐቶች የኢትዮጵያ መንግሥት 700 ሚሊዮን ብር ወይም 33 ሚሊዮን ዶላር መመደቡን መግለጫው ያስረዳል፡፡  ‹‹የአውሮፓውያኑ 2015 ሲጀምር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ ስለበልግ የአየር ሁኔታ ከተነበየው እጅግ የከፋ የዝናብ እጥረት በመከሰቱ፣ የምግብ እህልና የተመጣጠነ ምግብ እህል ችግር ተከስቷል፤›› በማለት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ዕርዳታ ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ተጠባባቂ ኃላፊ ዴቪድ ዴል ኮንቴ ገልጸዋል፡፡ በከፍተኛ ደረጃ አምራች የነበሩት የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች በተለይም የአርሲና የምዕራብ አርሲ አካባቢዎች የሰብዓዊ ዕርዳታ እንዳስፈለጋቸው መግለጫው ያብራራል፡፡  በአርብቶ አደር አካባቢዎች የተከሰተው የከብቶች

የሲዳማ ቡና አምራቾች ብቻ የሚሳተፉበት ውድድር

Image
ውድድሩ የቡና ጥራትንና አቅርቦትን ለማሻሻል ያግዛል፤ ውድድሩ ከጥር እስከ የካቲት  2008  ዓ . ም የሚካሄድ ሲሆን፤ በሲዳማ አካባቢ የሚገኙ ከ 24  ሺ በላይ የቡና አምራቾች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል ዩሺማ ኮፊ ካምፓኒ በተሰኘ የጃፓን የቡና ማቀናበሪያ ካምፓኒ አማካኝነት የኢትዮጵያን ቡና በዓለም የቡና ገበያ የበለጠ ለማስተዋወቅ የሚያስችልና የቡና አምራች አርሶ አደሮቹን ተጠቃሚ የሚያደርግ የኢትዮጵያ የቡና አምራቾች ውድድር ሊካሄድ ነው። የውድድር ሂደቱን አስመልክቶ ከትናንት በስቲያ በጃፓን አምባሳደር መኖሪያ ግቢ መግለጫ በተሰጠበት ወቅት እንደተነገረው፤ ውድድሩ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካም የመጀመሪያ ነው። የውድድሩ ተግባራዊ መሆንም የኢትዮጵያ ቡና ዓለም አቀፍ እውቅና ባላቸው ድርጅቶች እንዲተዋወቅ ዕድል የሚፈጥርና አምራቾችም ተገቢውን ጥቅም እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው። የካምፓኒው ዳይሬክተርና የአቅርቦት ትስስር ማኔጅመንት ሊቀመንበር ሚስተር ቲቲሱያ ሴኪ በመግለጫው ላይ እንደተናገሩት፤ በዚህ ውድድርም እስከ ስድስተኛ በመውጣት የሚያሸንፉ አምራች ገበሬዎችን ካምፓኒው ምርቶቻቸውን ከመደበኛው ዋጋ ጨምሮ የሚገዛና ለምርት ጥራት የሚያግዙ ድጋፎችን የሚያደርግ ሲሆን፤ ከስድስተኛ በላይ ለሚወጡ ደግሞ የምርት ግዥውን በተወሰነ መልኩ የሚያከናውን ይሆናል። በውድድሩም የሲዳማ ቡና አምራቾች ብቻ የሚሳተፉ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የቡና አምራች አገር እንደመሆኗ በቀጣይ የሌሎች አካባቢ አምራቾችን ለማሳተፍ የሚሰራ ይሆናል። ቡናው ወደ ጃፓን ከተወሰደ በኋላም አስፈላጊው የጥራት መመዘኛ ተከናውኖ የማስተዋወቅ ሥራ ይሰራበታል። በመሆኑም አምራቾቹ በውድድሩ መሳተፋቸው የቡና ምርትና ጥራትን ጠብቀው እንዲያመርቱና በዛው ልክ ከሚገኘው የገበያ ዋጋ ተጠቃ

ኢትዮጵያና ሳዑዲ አረብያ የሠራተኞች ቅጥር ስምምነት ሊፈራረሙ ነው

Image
( ኤፍ.ቢ.ሲ ) ኢትዮጵያና ሳዑዲ አረብያ የኢትዮጵያውያን ሠራተኞችን መብት የሚያስጠብቀውን የሰራተኞች ቅጥር ስምምነት በመጪው መስከረም ሊፈርሙ ነው። ስምምነቱ የሳዑዲ  አረብያ  መንግሥት ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች ክፍያቸውን በወቅቱ እንዲያገኙ፣ ከማንኛውም አካላዊ ትንኮሳ የመጠበቅና ደህንነታቸው እንደተጠበቀ ወደ አገራቸው የመመለስ ኃላፊነት እንዳለበት ያስቀምጣል። በሳዑዲ  አረብያ  የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጉዳይ አስፈፃሚ አቶ ተመስገን ዑመር እንደገለጹት፥ ስምምነቱ በሳዑዲ ዓረቢያ ተቀጥረው የሚሰሩ ኢትዮጵያውያንን የክፍያና የሥራ ሁኔታን የሚቀይር ነው። በአሰሪዎቻቸው ከሚደርስባቸው ጭቆና የመጠበቅና የመኖሪያ ፈቃድ የማግኘት መብትንም ያስገኝላቸዋል ብለዋል። ስምምነቱ የሳዑዲ መንግሥት ኢትዮጵያውያን በአሰሪዎቻቸውና በኤጀንሲዎች ለሚደርሰባቸው ማንኛውም የመብት ጥሰት ኃላፊነትን እንዲጋራ የሚጠይቅ ነው። በዓረብ አገራት ተቀጥረው የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን በአሰሪዎቻቸው በተደጋጋሚ ደመወዝ መከልከልን ጨምሮ የተለያዩ የመብት ጥሰቶች እየተፈጸመባቸው መሆኑን ይናገራሉ። ይህን ተከትሎም የኢትዮጵያ መንግሥት ለችግሩ እልባት እስኪያገኝለት ድረስ ዜጎቹ ሥራ ፍለጋ ወደ ዓረብ አገራት የሚያደርጉትን ጉዞ ከጥቅምት 2006 ዓ.ም ጀምሮ አግዷል። ይህን ተከትሎ ከሳዑዲ  አረብያ ና ከሌሎች የዓረብ አገራት ጋር የሠራተኞቹን መብትና ጥቅም ሊያስጠብቅ የሚችል የሠራተኛ ቅጥር ስምምነት መፈረም የሚያስችሉ በርካታ ድርድሮች ሲካሄድ ቆይቷል። በኢትዮጵያና ሳዑዲ ዓረቢያ መካከል ሲደረግ በቆየው ድርድር መሰረት ስምምነቱ በመጪው መስከረም እንደሚፈረም ይጠበቃል። በሳዑዲ ዓረቢያ ይኖራሉ ተብሎ ከሚገመተው 500 ሺህ ኢትዮጵያውያን መካከል 200 ሺህ የሚሆኑት ህጋዊ አለመሆናቸውም መ