Posts

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አርሶ አደርን ጨምሮ ከአርቲስትና ከተማሪ ጋር ለምርጫ ይወዳደራሉ

Image
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦና ሕዝቦች ክልል በወላይታ ዞን በቦሎሶሶሬ ሁለት የምርጫ ክልል ገዥው ፓርቲን በመወከል ለፓርላማ እንደሚወዳደሩ ታወቀ፡፡  ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚወዳደሩበት የምርጫ ክልል ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተፎካካሪ የሚሆኑ ዕጩዎችን ያቀረቡት ፓርቲዎች ደግሞ አዲስ ትውልድ ፓርቲ (አትፓ)፣ መድረክና ሰማያዊ ፓርቲዎች ናቸው፡፡ በእነዚህ ፓርቲዎች አማካይነት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለመፎካከር የቀረቡት ደግሞ አትፓን በመወከል አርቲስት ደስታ ደአ፣ መድረክን የወከሉት አርሶ አደሩ አቶ ተስፋዬ ኃይሌና ሰማያዊ ፓርቲን  የወከሉት ተማሪ ቀኙ ሴባ የተባሉ ዕጩዎች ናቸው፡፡  በ1987 እና በ1992 ዓ.ም. በተካሄዱ ምርጫዎች የደቡብ ክልል ምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ ኃይለ ማርያም፣ ደቡብ ክልልን በምክትልነትና በፕሬዚዳንትነት አስተዳድረዋል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1997 ዓ.ም. ለፓርላማ ተወዳድረው የፓርላማ አባል ከሆኑ በኋላ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ፣ የሕዝብ አደረጃጀትና ተሳትፎ አማካሪና በፓርላማ የመንግሥት ተጠሪ ሆነው መሥራታቸው አይዘነጋም፡፡ እንደገና በ2002 ዓ.ም. ተወዳድረው ፓርላማ ከገቡ በኋላ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ በኋላ ከመስከረም 11 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ በጠቅላይ ሚኒስትርነት በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን ለሦስተኛ ጊዜ ነው ለፓርላማ የሚወዳደሩት፡፡ በዚሁ የምርጫ ክልል ቦሎሶሶሬ ሦስት ደግሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ተክለ ወልድ አጥናፉም እንዲሁ ገዥው ፓርቲን ወክለው፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሚደረገው ምርጫ እንደሚወዳደሩ ለ

በሲዳማ ዞን ቦሪቻ ወረዳ የደህኢዴን /ኢህአዴግ ካድሬዎች ህዝቡ እሁድ በሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይወጣ በሜጋ ፎን እየቀሰቀሱ መሆኑን የሰልፉ አስተባባሪዎች ገለጹ

የሃዋሳ ፖሊስ የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ ቁሳቁሶችን ቀማ ‹‹የባጃጅ ሾፌሮችን አድማ የመራው ሰማያዊ ነው›› ባለስልጣናቱ የሃዋሳ ፖሊስ መጋቢት 20/2007 ዓ.ም ለሚደረገው ሰልፍ የተዘጋጁትን የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ ቁሳቁሶች መቀማቱን በሃዋሳ ከተማ የሰልፉ አስተባባሪ አቶ ዮናስ ከድር ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡ ከአዲስ አበባ ሰልፉን ለማስተባበር ወደ ሃዋሳ ያቀኑት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ሃዋሳ በደረሱበት ወቅት የፀጥታ ኃላፊው እና የከንቲባው አማካሪ አስተባባሪዎቹን አስጠርተው በሚያወያዩበት ወቅት ፖሊስ የቅስቀሳ ቁሳቁሶችን ከተቀመጡበት ቦታ ቀምቶ እንደወሰደ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የሃዋሳ ከተማ የፀጥታ ኃላፊ እና የከንቲባው አማካሪ የሰልፉን አስተባባሪዎች በመጥራት ‹‹በከተማችን በሚገኙ አደባባዮች ባዛሮች አሉ፡፡ በተጨማሪም ለህዳሴው ግድብ ከ18-30 የህዝባዊ ስብሰባዊና ህዝባዊ ንቅናቄዎች ይደረጋሉ፡፡ በዚህም ምክንያት የፀጥታ ኃይል ስለሌለን እስከ መጋቢት 30 ድረስ ሰልፍ ማድረግ አትችሉም፡፡›› እንዳሏቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ የሰልፉ አስተባባሪዎች ከከተማው ባለስልጣናት ጋር በሚወያዩበት ወቅት ፖሊስ ቲሸርትና በረሪ ወረቀቶች ቀምቶ የወሰደ ሲሆን ቁሳቁሶቹ አሁንም ድረስ በፖሊስ እጅ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ ሆኖም ፖሊስ ‹‹እቃ አልወሰድንም፣ የምናውቀን ነገር የለም›› ብሎ እንደካዳቸው አስተባባሪዎቹ ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ ዜና በሲዳማ ዞን ቦሪቻ ወረዳ የደህኢዴን /ኢህአዴግ ካድሬዎች ህዝቡ እሁድ በሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይወጣ በሜጋ ፎን እየቀሰቀሱ መሆኑን የሰልፉ አስተባባሪዎች ገልጸዋል፡፡ ካድሬዎቹ ‹‹በእሁዱ ሰልፍ የወጣ ሰው ይታሰራል›› እያሉ እንደቀሰቀሱም ለማወቅ ተችሏል፡፡ በሌላ ዜና በሃዋሳ ከተማ የተከሰተውን