‹‹የተቃዋሚ ድርጅት አባል ሆኖ ከመንግሥት ሥራ ማግኘት ከባድ ነው››፦ በሲዳማም እውኔታው ከዚህ የተለየ ኣይደለም
ፎቶ ኢትዮጵያን ሪፖርተር ጋዜጣ ኢንጂነር ዘለቀ ረዲ የኮንስትራክሽን ሥራና የሆቴል ባለቤት ተወልደው ያደጉት በኦሮሚያ ክልል ጂማ ዞን ሊሙ ኮሳ ወረዳ ጋሉ አካባቢ ነው፡፡ ትምህርታቸውን በጂማ ዞን ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች ከተከታተሉ በኋላ በመምህርነት አገልግለዋል፡፡ ለዓመታት በጂማ ማዘጋጃ ቤት ከዚያም ባቱ (ዝዋይ) ከተማ በሚገኘው ሼሪ ኢትዮጵያ አበባ እርሻ ውስጥ በቴክኒካል ማኔጀርነት ሠርተዋል፡፡ ኢንጂነር ዘለቀ ረዲ በአሁኑ ወቅት የራሳቸውን የኮንስትራክሽን ኩባንያ አቋቁመውና በመቂ ከተማ ሆቴል ከፍተው በመሥራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ኢንጂነር ዘለቀ ከቢዝነስ ሥራቸው ውጭ በፖለቲካም ንቁ ተሳታሳፊ ናቸው፡፡ ሥራቸውን አስመልክቶ ውድነህ ዘነበ አነጋግሯቸዋል፡፡ ሪፖርተር:- በሆቴልና በኮንስትራክሽን ሥራዎች ውስጥ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ሥራዎች ውስጥ ሆቴሉ በምን ደረጃ እንደሚገኝ ቢገልጹልኝ? ኢንጂነር ዘለቀ :- ሆቴሉ የሚገኘው ከአዲስ አበባ ወደ ሐዋሳ በሚወስድ መንገድ ላይ በምትገኘው መቂ ከተማ ነው፡፡ የቱሪስት ማረፊያ የቱሪስት መሸጋገሪያ ለማድረግ ሆቴሉን በአዲስ መልክ እንደገና ልገነባ እየተዘጋጀሁ ነው፡፡ ሪፖርተር:- በኮከብ ደረጃ ለማሳደግ ነው? ኢንጂነር ዘለቀ :- አዎ፡፡ በኮከብ ደረጃ ለማሳደግ ነው እቅዴ፡፡ ምክንያቱም መስመሩ የቱሪስት ነው፡፡ በርካታ ቱሪስቶች ይመጣሉ፡፡ ሆኖም በመስመሩ ጥሩ ሆቴል አያገኙም፡፡ የግድ ሐዋሳ መጓዝ ይኖርባቸዋል፡፡ አማካይ ቦታ ላይ ጥሩ ሆቴል ቢሠራ ከሚል ነው ይህንን እቅድ ያመነጨሁት፡፡ አሁን ነባሩን ሆቴል አፍርሼ ዘመናዊ ባለ ኮከብ ሆቴል ለመገንባት ዲዛይን እየሠራሁ እገኛለሁ፡፡ ከአዲስ አበባ እስከ ሐዋሳ 270 ኪሎ ሜትር ነው፡፡ መቂ በሁለቱ ከተሞች አማካይ ቦታ ላይ ትገኛለች፡