Posts

ፓርላማው መደበኛ ስብሰባዎቹን እያካሄደ አይደለም

-    ከ18 መደበኛ ስብሰባዎች ስድስቱን ብቻ ተሰብስቧል በዮሐንስ አንበርብር በመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት የሦስተኛ ዓመት የሥራ ዘመኑን የጀመረው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) በሳምንት ሁለት ጊዜ ማክሰኞና ሐሙስ ማካሄድ የሚገባውን መደበኛ ስብሰባዎች በአብዛኛው አላካሄደም፡፡ በምክር ቤቱ የአሠራር ሥነ ሥርዓት ደንብ መሠረት የምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባዎች በሳምንት ሁለት ጊዜ መካሄድ ይገባቸዋል፡፡ በዚህም መሠረት ምክር ቤቱ ሥራውን ከጀመረበት የመስከረም ወር መጨረሻ አንስቶ እስከ ታህሳስ ወር የመጀመሪያ ሳምንት ድረስ 18 መደበኛ ስብሰባዎች መካሄድ ነበረባቸው፡፡ ይሁን እንጂ እስካሁን ያደረገው ስድስት መደበኛ ስብሰባዎችን ብቻ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በምክር ቤቱ ከሁለት ሳምንት በፊት ተገኝተው ያፀደቁት አዲስ የካቢኔ አወቃቀርና የሚኒስትሮች ሹመት የመጨረሻው ወይም ስድስተኛው መደበኛ ስብሰባው ነበር፡፡ ኅዳር 20 ቀን 2005 ዓ.ም. ከተካሄደው ከዚህ መደበኛ ስብሰባ በኋላ እንኳን አራት የመደበኛ ስብሰባ ቀናት ቢኖሩትም፣ “ዛሬ ይካሄድ የነበረው መደበኛ ስብሰባ የማይካሄድ መሆኑን ከይቅርታ ጋር እንገልጻለን” የሚሉ ማስታወቂያዎችን የምክር ቤቱ አባላት መኖሪያዎች አካባቢ በሚገኙ የማስታወቂያ ሰሌዳዎች፣ እንዲሁም በምክር ቤቱ ሰሌዳዎች ላይ በመለጠፍ የመደበኛ ስብሰባ ፕሮግራሞቹን መዝለል የተለመደ እየሆነ መጥቷል፡፡ የምክር ቤቱ ዋና ሥልጣንና ተግባሮች የሚቀርቡለትን ረቂቅ አዋጆች ተወያይቶ ማፅደቅና አስፈጻሚውን ወይም ራሱ የሚያመነጫቸውን የመንግሥት አካላት መቆጣጠር ናቸው፡፡ እስካሁን ካካሄዳቸው ስድስት መደበኛ ስብሰባዎች መካከል የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ የዚህን ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሥራ ዘመን

ፌዴራል ፖሊስ አገሪቱን በስለላ ካሜራዎች ለማጥለቅለቅ አቅዷል

ታህሳስ ፭(አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የፌዴራል ፖሊስ ከሁለት ዓመት በፊት በአዲስአበባ ተክሎ ሥራ ላይ ያዋላቸው የስለላ ካሜራዎች (cctv ካሜራዎች) ውጤታማ በመሆናቸው ወደክልሎች ለማስፋፋት ማቀዱን አስታወቀ፡፡ ከፌዴራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ እንዳመለከተው በኢትዮጵያ የፖሊስ ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስአበባ ዋናዋና መንገዶች ላይ ካሜራዎችን በመግጠም የመቆጣጠሪያ ክፍል በማቋቋም በመንገዶቹ ላይ የሚሰሩ ሕገወጥ ድርጊቶችንና የትራፊክ አደጋዎችን በአነስተኛ የፖሊስ ኃይል ያለብዙ ወጪና ድካም ለመቆጣጠርና ጸጥታ ለማስከበር መቻሉን ይጠቅሳል፡፡ ይህንኑ ቴክኖሎጂ በከተማውና በክልሎች ለማስፋፋትና ተጨማሪ ሥራ እንዲያከናውን ለማድረግ ተከታታይ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን መረጃው ጠቅሶ ፣ “ተጨማሪ ሥራዎች” ያላቸውን ስራዎች ግን ከመግለጽ ተቆጥቧል፡፡ በሚሊየን ዶላር ወጪ በአዲስአበባ ከተማ የተተከሉት እነዚሁ ዘመናዊ ካሜራዎች ዋንኛ ጥቅማቸው ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ዜጎችን ለመሰለል ካለው ጥልቅ ፍላጎት ጋር የተያያዘ መሆኑን በመግለጽ መንግስት ለሕዝብ የሚያስብ ቢሆን ኖሮ ገንዘቡን ድህነትንና የኑሮ ውድነትን ለመቅረፍ ባዋለው ነበር ሲሉ አንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተቃውሞ አሰምተው እንደነበር አይዘነጋም፡፡ በተያያዘ ዜና ፌዴራል ፖሊስ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በመታገዝ የሚፈጸሙ የሳይበር ወንጀሎችን ለመከታተልና አጥፊዎችን ለመያዝ ቢሮ ከፍቶ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ(ICT) በመደገፍ የሚሰሩ ወንጀሎች(ሳይበር ክራይም) አሳሳቢ እየሆኑ በመምጣታቸው ወንጀሎችን ለመከታተል፣ለመመርመርና ለማጣራት፣አጥፊዎችንም ለፍርድ ለማቅረብ በፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ዘርፍ በፎረንሲክ ዳይሬክቶሬት ስር የሳይበር ላብራቶሪ ተቋቁሟል፡፡ላብራቶሪ

የኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ ዛሬና ነገ ይቀጥላል

Image
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 6፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ እግር ኳስ ውድድር ዛሬና ነገ በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ከተሞች ይቀጥላል። ዛሬ በአዲስ አበባ ስታድየም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከመከላከያ በ9 ሰዓት ፥ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ውሃ ስፖርት በ11 ሰዓት ይጫወታሉ። ውድድሩ ነገ ቀጥሎ ፥ ደደቢት ከኢትዮጵያ መድን ፣ መብራት ኃይል ከኢትዮጵያ ቡና በ9 እና በ11 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታድየም ይጫወታሉ። አዳማ ላይ አዳማ ከነማ  ድሬዳዋ ከነማን ሃዋሳ ላይ ደግሞ ሃዋሳ ከነማ ሲዳማ ቡናን ያስተናግዳሉ። አርባ ምንጭ ከነማ የሳምንቱ አራፊ ቡድን እንደሚሆን አራያት ራያ ዘግባለች።

ከተለያዩ የገቢ አርዕሰቶች ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን በሲዳማ ዞን የአለታ ጩኮ ወረዳ ገቢዎች ባለሥልጣን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ መንግስቱ መለስ እንደገለፁት የተገኘው ገቢ በዓመት ውስጥ ሊሰበሰብ ከታቀደው የ3ዐ ሚሊዮን ብር አካል ክንውኑም 1ዐ7 ብልጫ እንደሚኖረው አስታውቋል፡፡ ገቢው ከአመና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ1 ሚሊዮን ብልጫ እንዳለው ጠቁመዋል፡፡ የመስሪያ ቤቱ ሠራተኞችን በገቢ አሰባሰብ ስምሪት በ24 ሰዓት በፈረቃ በማድረግና ህገ ወጥ ነጋዴዎችን ወደ ህጋዊ መስመር ማስገባት መቻሉ አቶ መንግስቱ ተናግረዋል፡፡ ለገቢው መጨመር አስተዋፅኦ እንደነበረው በወረዳው የግብር ከፋይና ምዝገባ ክትትል የንግዱ ማህበረሰብ ግብር በወቅቱ በመክፈል ሀላፊነቱን እንዲወጣ ትልቅ አገዛ እንዳደረገላቸው ገልፀዋል፡፡ አንዳንድ  ግብር ከፋዮች በሰጡት አስተያየት መንግስት ያቀዳቸውን ውጥኖች ማሳካት ግብርን በወቅቱ መክፈል የገባነው ቃል እንወጣለን ሲሉ መናገራቸውን የዞኑ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ዘግቧል፡፡

ጥራት ያለው ትምህርት ለልማት ያለው ፋይዳ ጉልህ በመሆኑ ሁሉመ ባለድርሻ አካላት መረባረብ እንደሚጠበቅባቸው በሲዳማ ዞን የአለታ ጩኮ ወረዳ ትምህርት ቤቶች ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በወረዳው የሚገኙ የትምህርት ባለድርሻ አካላት በወረዳው ጥሩ ውጤት በማስመዝገብ ሞዴል በሆነው በማንጉዶ ትምህርት ቤት በመገኘት ሰሞኑን የተሞክሮ ልውውጥ አድርገዋል፡፡ የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ሽመልስ አየለ እንደገለፁት ጥራት ያለው ትምህርት ለልማት ያለው ፋይዳ የላቀ መሆኑን በመገንዘብ ጥራቱን ለማስጠበቅ ከሚመለከታቸው ከትምህርት ባለ ድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ሥራ መስራታቸውን ተናግረዋል፡፡ በዚሁ በተሰራው ሰፊ ስራ በወረዳው የሚገኙ ትምህርት ቤቶች የትምህርትን ጥራት ለማምጣት የእርስ በርስ የሥራ ፉክክር መንፈስ በመላበስ እንዲሰሩ በተደረገው መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ ከወረዳው ከሚገኙ ከ43 ትምህርት ቤቶች መካከል  የመንጉዶ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተያዘው በአንደኛ ሩብ አመት በትምህርት ሥራ የላቀ ውጤት በማስመዝገብ ሞዴል ትምህርት ቤት መሆኑን አብራርተዋል፡፡ የማንጉዶ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ዱሬሳ ዮኖራ በበኩላቸው ትምህርት ቤቱ በአሁኑ ጊዜ 1ኛና ሞዴል ሊሆን የቻለው መንግስት የቀረፀውን ስድስቱን የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጆችን ከትምህርት ባለ ድርሻ አካላት ጋር ተግባራዊ በማድረጋቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ከሲዳማ ዞን ትምህርት መምሪያ የትምህርት ጥራት ዋና የሰራ ሂደት አስተባባሪ አቶ እሸቱ ቃሬ እንደተናገሩት የትምህርት ቤቶች የልምድ ልውውጥ የትምህርትን ጥራት በማስጠበቁ ረገድ የላቀ ሚና አለው፡፡ ልምድ ልውውጡ ወቅት ለ12 ወላጅ አጥ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው እዳይስተጓጎሉ ከትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ከተገኘው ገንዘብ የተለያዩ አልባሳት ተበርክተውላቸዋል ፡፡ የበንሳ ቅርንጫፈ እንደዘገበው፡፡ http://www.smm.gov.et/

በሀዋሳ ከተማ ከ253 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የልማት ፕሮግራም እየተካሄደ ነው

Image
ሃዋሳ ታህሳስ 04/2005 በሀዋሳ ከተማ መንግስታዊ ያልሆኑ 74 ድርጅቶች ከ253 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ በጀት ህብረተሰቡን ያሳተፉ የልማት ፕሮግራሞች እያካሄዱ መሆናቸውን የከተማው ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ገለጸ፡፡ የመምሪያው ምክትል ሃላፊ አቶ አሻሬ ኡጋ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በከተማው ስምንት ክፍለ ከተሞች የሚካሄደው የልማት ፕሮግራም ለሚቀጥሉት ሶስት አመታት የሚቆዩ ናቸው፡፡ ከልማት ፕሮግራሞቹ መካከል የጤና፣ የትምህርት፣ የከተማ ግብርና፣ የአካባቢ ጥበቃ፣ የህጻናት ድጋፍና ክብካቤ፣የገቢ ማስገኛ ፣አቅም ግንባታን ጨምሮ ሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸው ዘርፎች መሆናቸውን አስታውቀዋል የከተማውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ለማፋጠን መንግስት የሚያደረገውን ጥረት ለማገዝ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ህብረተሰቡን በማሳተፍ የሚካሄዱት የልማት ፕሮግራሞች ሲጠናቀቁ ከ200ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ገልጸዋል፡፡ የድርጅቶቹን የስራ አንቅስቃሴና አፈጻጸም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ክትትልና ቁጥጥር እያደረጉ መሆናቸውንም አመልከተዋል፡፡ እየተጠናቀቀ ባለው የአውሮፓውያኑ 2012 የስራ ዘመን ድርጅቶቹ በመደቡት ከ84 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የከተማው ነዋሪዎች ተጠቃሚ ያደረጉ ተመሳሳይ የልማት ፕሮግራሞች ማካሄዳቸውን የመምሪያው ምክትል ሃላፊ ገልጸዋል፡፡ http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=3941&K=1

ስራ ኣጥነት እና የወጣቶች እሮሮ በሲዳማ

Image
  በኪንክኖ ኪአ በሲዳማ ዞን በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች በሥራ አጥነት የሚሰቃዩ ወጣቶች ቁጥር ከጊዜ ቀደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ፡፡ ሥራ ያጡ ወጣቶችም በተለያዩ ወረዳዎች ሠላማዊ ሠልፍና ተቃዉሞ እያሰሙ መሆናቸዉ ታዉቀዋል፡፡ ሰሞኑን በአርቤጎና ወረዳ በተካሄደዉ ተቃዉሞ ሰልፍ ሳቢያም ከ15 በላይ ወጣቶች መተሰራቸዉ ተሰመቶአል፡ በአሁኑ ጊዜ በተለያዩ ሙያና ት/ት ዘርፎች ተከታትለዉ ከተመረቁ በኀላ የሥራ እድል በማጣት በርካታ ወጣቶች በከፍተኛ ችግር ላይ መዉደቃቸዉ በሰፊዉ ይነገራል፡፡ የከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ት ካጠናቀቁ በኀላ በተለያዩ ኮሌጆች፡ የሙያ ማሠልጠኛ ተቐማትና ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸዉን የተከታተሉ ወጣቶች ቁጥር በርከት እያሌ መምጣቱ የሚነገር ሲሆን ከዚሁ ቁጥር ጋር የሚመጣጠን የሥራ እድል በመንግሥት ባለመመቻቸቱ ከፍተኛ የሆነ የሥራ አጥነት ችግር በዞኑ ተንሰራፍተዋል፡፡     ወጣቶቹ በት/ት የቀሰሙትን እዉቀት ተጠቅመዉ ሕብረተሰቡን ለማገልገልና የራሳቸዉን ሕይወት ለማሻሻል ከፍተኛ ተነሳሽነትና አቅምያላቸዉ ቢሆንም ት/ታቸዉን አጠናቀዉ ከ5 እና ከዚያ በላይ ዓመታትን የለሥራ በማሳለፋቸዉ ሰቢያ ሊለማ የሚችል እዉቀት፤አቅምና ጉልበት በጥቅም ላይ ሣይዉል እንደሚባክን ተጠቁመዋል፡፡   የሥራ አጥ ወጣቶች የኑሮ መሠረት በአጭሩ አብዛኞቹ የሥራ አጥ ወጣት ምሁራን የተገኙት ከገጠሩ ማህበረሰባችን ከፍል ነዉ፡፡ ትምህርታቸዉን ለመከታተልም ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ወጪ አድርገዉ፤ አብዛኞቹ ደግሞ በግል ት/ት ተቐማት በራሳቸዉ አቅም ትምህርታቸዉን የተከታተሉ ናቸዉ፡፡ እንደሚታወቀዉ አብዛኛዉ የሲዳማ ማህበረሰብ የገጠር ነዋሪ በመሆኑ የኢኮኖሚ መሠረቱ ግብርና ከመሆኑም በተጨማሪ የገቢ ምንጫቸዉና አቅምቸዉ ይኼ ነዉ የሚባል አይደለም፡፡ ይህም ሆኖ እነ

የሀዋሳን መስህቦች ከጎበኙ ቱሪስቶች ከ16 ነጥብ 8ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኘ፡፡

Image
አዋሳ ታህሳስ 3/2005 በሀዋሳ ከተማና አካባቢውን የሚገኙ የመስህብ ቦታዎችን ባለፉት ሶስት ወራት ከጐበኙ የሀገር ውስጥና የውጪ ቱሪስቶች ከ16 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን የከተማው አስተዳደር ባህል፣ ቱሪዝምና የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳይ መምሪያ አስታወቀ፡፡ በመምሪያው የቱሪዝምና ፓርኮች የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ አዲሴ አኔቶ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በሀዋሳ ከተማና አካባቢው የሚገኙ የመስህብ ቦታዎች ባለፉት ሦስት ወራት በ47 ሺህ 728 የሀገር ውስጥና 10 ሺህ 139 የውጪ አገር ቱሪስቶች ተጐብኝተዋል፡፡ ቱሪስቶቹ የጎበኟቸው የመስህብ ቦታዎች የሀዋሳ ሀይቅንና በውስጡ ያሉት ብርቅዬ የአእዋፍ ዝርያዎች፣ ጉማሬዎች ፣ በከተማው ዙሪያ የሚገኙት የአላሙራና የታቦር ተራራዎች፣ የጥቁር ውሃ ደን ፣ የቡርቂቲ ፍል ውሃ ፣ የሲዳማ ባህላዊ ጎጆዎችንና የተለያዩ ብሄረሰቦች የባህል አልባሳት ፣ አመጋገብና የሙዚቃ መሳሪዎች ጨምሮ ሌሎች ተፈጥሯዊ፣ ባህላዊና ታሪካዊ ቅርሶች ነው፡፡ የተገኘው ገቢም ሆነ የቱሪስቶች ቁጥር ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር አምስት በመቶ ብልጫ እንዳለው ገልፀዋል፡፡ ገቢውም ሆነ የቱሪስቶች ቁጥር ሊጨምር የቻለው የቱሪዝም ሀብቱን በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች በማስተዋወቅ ጎብኚዎችን ለመሳብ በተደረገው ጥረት መሆኑን የስራ ሂደቱ አስተባባሪ አመልከተዋል፡፡ የሀዋሳ ከተማ የአየር ንብረት ተሳማሚነት፣ የመስተንግዶና የመሰረተ ልማት መስፋፋትን ጨምሮ ለመዝናናትና ለኑሮ ባለው ምቹነት አካበቢውን ለመጎብኘት የሚመጡ የሀገር ውስጥና የውጪ ቱሪስቶች ቁጥር በየአመቱ እየጨመረ እንዲሄድ አስተዋጽኦ ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡ የጐብኝዎች ቁጥር መጨመርን ተከትሎም የሚገኘው ገቢ በዚያው መጠን እያደገ መሆኑን አስተባበሪው

የነጭ ሪቫን ቀን በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ

Image
አዋሳ ታሀሳሰ 03/2005 የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ መምህራን፣ ተማሪዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ፆታዊ ጥቃቶችን ለማስቆም የተቀናጀ ጥረት እንደሚያደርጉ አስታወቁ፡፡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከዩኒቨርስቲ ጋር በመቀናጀት ያዘጋጀው አለም አቀፍ የነጭ ሪቫን ቀን ትናንት በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡ ቀኑን አስመልክቶ በዩኒቨስርቲው በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ እንደተገለፀው በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ፆታዊ ጥቃቶችን ማሰቆም ሰብአዊ መብቶች በማስተባበር ልማትና እድገትን ለማፋጠን ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፡፡ የዩኒቨርስቲው ሶስቱም ካምፓስ መምህራን፣ ተማሪዎችና የአስተዳደር ሰራተኞች በውይይቱ መጨረሻ በተቋሙ ውስጥም ሆነ ውጭ በሴቶች ላይ የሚፈፀመውን ማንኛውንም ጥቃት እና ትንኮሳዎችን ለመከላከል ግንዛቤ በመፍጠር የበለጠ ትኩረት ሰጥተው እንደሚንቀሳቀሱ ተናግረዋል፡፡ በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ የሃይል ጥቃቶች የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በመሆናቸው ከተለያዩ ማህበራት፣ መንግስታዊ ከሆነ ተቋማትና ከተለያዩ የባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ችግሩን ለመግታት ግንባር ቀደም ሚና ለመጫወት ዝግጁ መሆናቸውንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የስርዓተ ፆታ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ በዛ ነገዎ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት መንግስት የብሄር ብሄረሰቦች መብትና ጥቅም ከማስጠበቅ ባሻገር የሴቶችን አኩልነት ፣ የሃይማኖት ነፃነትን ያረጋገጠ በመሆኑ ሁሉም ተገንዝቦ ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ኮሚሽነር አቶ አስማሩ በሪሁን በበኩላቸው ፆታዊ ጥቃትና ትንኮሳዎች ሴቶች ለሀገር ልማትና እድገት የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ የሚገድብ፣ በትምህርት ላይ ያላቸውን ተሳትፎ የሚያቀጭጭ፣ የሀገሪቱ የ

ሹመት ችግር ካልፈታ ፋይዳ ቢስ ነው!

ሰላም! ሰላም! ለዛና ጨዋታ ናፈቀን አይደል ጎበዝ? የድርቅ ታሪካችንን ለማጥፋት ስንረባረብ ሳይታወቀን የጨዋታ ድርቅ እየወረሰን መጣ መሰለኝ። የሚወራው፣ የሚሰማው፣ የሚዘፈነው፣ የሚታየው ሁሉ ለዛ በማጣት ድርቅ ከተመታ ምን ይውጠናል? እንዴ መኖር እየጠላን እንዴት እንዘልቃለን? እውነት እውነት ስላችሁ! ሳቅና ጨዋታ ከአታካቹ ኑሯችን ከተባረረ መሀል ላይ ስንዋልል ጥሩ አይመስለኝም። ‹‹አይ አንተ ሁሌም አንድ ሐሳብ አያጣህም?›› አለችኝ ውዷ ባለቤቴ ማንጠግቦሽ፣ ‹‹ሳቅ አላማረሽም?›› ብዬ ብጠይቃት። በነገራችን ላይ ማንጠግቦሽ ከት ብላ ከሳቀች ድንበር ተሻጋሪ ድምጿን ማንም ነው ሚሰማው። አሁን ታዲያ በገባሁ በወጣሁ ቁጥር ‹‹ምነው ሰላም አይደላችሁም?›› የሚለኝ ሠፈርተኛ በዝቷል።  ይኼኔማ አንዳንዱ ተጣሉም ብሎ ያስወራ ይሆናል። ሰው እንዴት የሰውን ጓዳ ጎድጓዳ እየተከታተለ እንደሚኖር ሳስብ በእጅጉ ይደንቀኝ ጀመር። በነገራችን ላይ ከመሬት እየተነሳ ባለፀጋ የሚሆነው አልበዛባችሁም? መጠቃቀም በሕዝብ ሀብት ባይሆን ጥሩ ነው እያልን ብንመክር ብናስመክር ማን ከመጤፍ ቆጠረን? ‹‹ምርጫ ሲደርስ ብቻ የሚቆጠረው ድምፃችን ከወዲሁ ሰሚ ቢያገኝ ኖሮ የሌባው ቁጥር እንዲህ ባልበዛ ነበር፤›› ይለኛል የባሻዬ ልጅ በአንድ ጀንበር የሚከብሩ ሲበዙበት። መክበራቸው ሳያንስ ተፈርተው መኖራቸው የሚያበሳጨን አደባባይ ይቁጠረን። እናም ሳቅ ጠፋ የምለው በየትኛውም ሥፍራ እያረሩ መሳቅ የደስታ ምልክት ነው ተብሎ ስለማይቆጠር ነው።  ለነገሩ ዝም ብላችሁ ብትታዘቡ እንኳን መሳቅ ይቅርና እሪ ብሎ ማልቀስስ ተወዷል። (ቆይ የማይወደደው ምን ይሆን?) ‹‹ይኼ ለብ ማለት ደግ አይደለም አንበርብር፤›› ይሉኛል ባሻዬ ጋቢያቸውን እያጣፉ። ኑሯችን ከአንዱ ወደ አንዱ እንደኳስ እየጠለዘ ሲጫወትብን መሳቅ

አማራጭ ሐሳብና አማራጭ ጥንካሬ ያለው ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ይፈለጋል!

Image
አገራችን ኢትዮጵያ ምን እንድትሆን ትፈልጋላችሁ ብንባል ቀጥተኛውና ቀልጣፋው መልሳችን የበለፀገችና ዲሞክራሲያዊት አገር እንድትሆን እንፈልጋለን ነው፡፡ ልማትና ዲሞክራሲ ጐን ለጐን ተያይዘውና ተሳስረው የሚታዩባት አገር እንድትሆን እንፈልጋለን፡፡ ልማት እንጂ ዲሞክራሲ አንፈልግም የሚለውን አንቀበልም፡፡ ዲሞክራሲ እንጂ ልማት አንፈልግም የሚለውንም አንቀበልም፡፡ ልማታዊና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት፣ መንግሥትና ፖለቲካ እንፈልጋለን፡፡ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እንፈልጋለን ስንል አንዱ መገለጫው የተለያዩ ሐሳቦች የሚንሸራሸሩበት ሥርዓት እውን ማድረግ ነው፡፡ ለአገር የሚጠቅም የተሻለ ሐሳብ አለን የሚሉ ኃይሎች የሚሰባሰቡበትና የሚደራጁበት የፖለቲካ ፓርቲ መፍጠርና ሥልጣን ለመያዝ መወዳደር መብት መሆኑን የሚያረጋግጥ ሥርዓት እውን ማድረግ ማለት ነው፡፡ ስለሆነም የፖለቲካ ፓርቲዎች መኖር ለአንድ አገር ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እውን መሆን ወሳኝ ነው፡፡ ሐሳቦች እርስ በርስ ይወዳደራሉ፤ ይታገላሉ፡፡ ሕዝቡም የተሻለውን ሐሳብ ይመርጣል፡፡ በሕዝብ ድምፅ የተመረጠውም አገሪቱን እንዲመራ ኃላፊነት ይሰጠዋል ማለት ነው፡፡ በዚህ ዙሪያ ሕዝብም፣ መንግሥትም፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችም በሥነ ሐሳብ ደረጃ ልዩነት የላቸውም፡፡ ሕዝብ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ኖረው ይወዳደሩ ብሎ ያምናል፡፡ በሕገ መንግሥቱም ሰፍሯል፡፡ በተግባር ግን የጠንካራ ፖለቲካ ፓርቲዎችን ትግል፣ ፉክክርና ውድድር ማየት አልቻልንም፡፡ ጠንካራ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ እውን ማድረግ አልተቻለም፡፡ ለዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስፈላጊ የሆነው ጠንካራ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ በተግባር በኢትዮጵያ እውን መሆን አልቻለም፡፡ ለምን? ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጠንካራ መሆን ያልቻልነው ገዥው ፓርቲ እንዳንጠናከር ስላደረገን ነው የሚል መከራከሪያ ሊ

አሞራ ገደልና የዓሳ ገበያው

Image
በሔኖክ ረታ ቀደም ሲል አካባቢውን ለሚያውቀው ጎብኚ የአሞራ ገደል አሰያየም በቀጥታ ከአካባቢው ተፈጥሯዊ ሁኔታ ጋር ስለመዛመዱ መናገር ይችላል፡፡ ከከተማዋ ፈጣን ዕድገትና በየአቅጣጫው ከተስፋፋው የሥራ ዕድል ጋር ተያይዞ ግን ለከተማዋ ጀባ የተባለው ትኩረት ለዚህም የሐይቁ ታዋቂ ስፍራ እንደ ፀበል ደርሶ በመጠኑም ቢሆን የአጥር መከለያ ተሠርቶለትና ከዚህ በፊት እዚህም እዚያም ይጠባበስ የነበረው የዓሳ ምግብ በወጉ እየተዘጋጀ ለተመጋቢው መቅረብ ጀምሯል፡፡ እንደዚያም ሆኖ ግን ይህ ዝነኛ የሐይቁ ክፍል አሁንም ቢሆንም እንደሌላኛው የሐይቁ መዳረሻ በሰንደቅ ዓላማና በቀለማት ባሸበረቁ ጀልባዎች፣ አበቦችና የማስታወቂያ ሰሌዳዎች የደመቀ አይደለም፡፡ ይልቁንም ዓሳ ጎርጓሪ ወፎች፣ እነ አባ ኮዳ፣ አባጆፌዎችና ሌሎቹም ዓሳ ተመጋቢ ወፎች እንደትናንቱ ግቢውን ወረው፤ ከዓሳ አጥማጆች የሚያፈተልኩትን ጥቃቅን ዓሶችንና ከበላተኛው ተርፈው የተጣሉ ትርፍራፊዎችን እየተሻሙ ሲለቅሙ የሚታዩበት እንጂ፡፡ ለሁለት በተከፈለው ሰፊ ግቢ በአንደኛው በር የመግቢያ ትኬት እየተቆረጠበት በፓርክ (መናፈሻ) ውስጥ ፎቶግራፍ ለመነሣት የሚቻል ሲሆን በሌላኛው በር ደግሞ የዓሳ ጥብስና ሾርባን ለመመገብ ብቻ ታስቦ በነፃ የሚስተናገዱበት በር ይገኛል፡፡ በዚህ በር በስተግራ በኩል መደዳውን እንደ ሱቅ የተደረደሩት ደሳሳ ቤቶች እንደዋዛ በደረደሯቸው የመመገቢያ ጠረጴዛና ወንበሮች ተኮልኩሎ ለሚጠብቃቸው ተመጋቢ ፊሌቶ የተሰኘውን የአካባቢውን ተወዳጅ ዓሳ የሚጠበስባቸውና ሾርባው የሚዘጋጅባቸው ኩሽናዎች ናቸው፡፡ ‹‹ኧረ እባካችሁ! ቆየ እኮ!....›› ‹‹ሾርባው ይቅደም!›› ወዘተ የሚሉ የደንበኞች አቤቱታ በጭብጨባ ታጅበው ከዚህም ከዚያም ይሰማሉ፡፡ ጫጫታውና ግርግሩ በአንድ የሐ

Iodine Status and Cognitive Function of Mother-child Pairs in Sidama ...

Image
Iodine Status and Cognitive Function of Mother-child Pairs in Sidama ... By Alemtsehay Bogale Wotang

በሀይማኖት ተቋማት እና በግለሰብ እጅ ያሉ ጥንታዊ ፅሁፉችን የማሰባሰብና የማጥናት ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

Image
የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት የኢትዮጵያን 12 ጥንታዊያን መጽሀፍትና የነገስታት ደብዳቤዎችን በዓለም የስነ ፁሑፍ ቅርስነት መዝግቦታል፡፡ አሁንም ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በአለም እውቅና ያላገኙትን የስነ ጽሁፍ ቅርሶች ለማስመዝገብና መስፈርቶቹን ለማወቅ የሚያስችላቸው ስልጠና በአዲስ አበባ እየተሰጠ ነው፡፡ ቅርሶቹ በአለም ቅርስነት ለመመዝገብ ዋነኛው መስፈርት አለም አቀፍ ይዘት ያላቸው ሊሆኑ ይገባል፡፡ በዩኔስኮ የአለም የስነ ጽሁፍ ቅርስ ፕሮግራም ማናጀር ጆይ ስፐሪንግ የአፍሪካ መገለጫ የሆኑ ቅርሶች ተጠብቀው ሊቆዩ ይገባል ይላሉ፡፡ ኢትዮጵያ ውያን   የራሳቸው የሆኑ ፊደል፣ ቁጥር እና የአጻጻፍ ስሌት ካላቸው ጥቂት የአፍሪካ ሀገራት መካከል አንዷ ናት፡፡ የተለያዩ የስነ ጽሁፍ ቅርሶችም ባለቤት ነች፡፡ ቅርሶች የአፍሪካ ትውስታ፣ ታሪክ፣ ባህልና ማንነት መገለጫ ናቸው፡፡ አፍሪካን አፍሪካ የሚያደርጓት ባለፉት ትውልዶች የተቀመጡ ታሪካዊ ዳራዎችና ቅርሶችን ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ ስትችል ነው፡፡ ይህን ማድረግ የሚቻለው ደግሞ ቅርሶቹን በሚገባ ጠብቆ ማቆየት ሲቻል ነው፡፡ የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጽሀፍት ዋና ዳይሬክተር አቶ አብርሃም ሞቶሽ በሀይማኖት ተቋማት እና በግለሰብ እጅ ያሉ ጥንታዊ ጽሁፉችን የማሰባሰብና የማጥናት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ በጊዜ ብዛት ይዞታቸውን ለመልቀቅ የተቃረቡትን ደግሞ በዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓት እየተቀየሩ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ ለ3 ቀናት የሚቆየውን ስልጠና በዩኔስኮ የደቡብ ኮሪያ ብሄራዊ ኮሚሽን እና የኮሪያ ባህላዊ ቅርሶች አስተዳደር ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻህፍት ኤጀንሲ ጋር በትብብር አዘጋጅተውታል፡

It does not relate to us.

Image
Asfaw Dingamo, deputy director and advisor to the director general of the Ethiopian Sugar Corporation, Abaye Tsehaye, said this speaking about the delay in construction of Tendaho Sugar Factory, whose first phase was reportedly meant to be completed in 2010 and its second phase a year after. If the question is whether the contractor had an implementation problem, I would say yes, Asfaw told Sendeke, an Amharic weekly, in an exclusive interview published on Wednesday, November 28, 2012. http://addisfortune.net/columns/it-does-not-relate-to-us/

ለሥርዓትና ለተቋማት ግንባታ ቅድሚያ ትኩረትና ርብርብ ይደረግ!!

Image
ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እውን መሆን፣ ለልማት፣ ለሰላምና መረጋጋት፣ ለአገር ህልውናና ደኅንነት እጅግ በጣም ወሳኝ መሆኑ በተደጋጋሚ መነገሩ ቢሰለችም፣ አሁንም እንደገና ቅድሚያ ርብርብና ልዩ ትኩረት ለሥርዓትና ለተቋማት ግንባታ ይሰጥ እንላለን፡፡ አገራችን ኢትዮጵያ እንዴት መኖርና መንቀሳቀስ እንዳለባት የሚመራ ሕገ መንግሥት አላት፡፡ ሕገ መንግሥቱን ሥራ ላይ ለማዋል የወጡ በርካታ ሕጎች አሉ፡፡ አዋጆቹንና ሕጎቹን ሥራ ላይ ለማዋል ይበጃል የተባሉ ደንቦችና መመርያዎችም በብዛት አሉ፡፡ ከየት ጀምረን የት እንድረስ በማለት የተለያዩ ዕቅዶች ወጥተዋል፡፡ የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድም አለ፡፡ ህዳሴውን እውን ያደርጋሉ ተብለው የተቀመጡ ራዕዮችም አሉ፡፡ እነዚህን ሥራ ላይ የሚያውላቸው ግን ማን ነው? ሥራ ላይ የሚውሉትስ እንዴት ነው? ሥራ ላይ በትክክል መዋላቸውና አለመዋላቸው የሚታወቀውስ እንዴት ነው? ዋስትናቸው ምንድን ነው? ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ስንሞክር ነው በኢትዮጵያ ተቋማት ያልተገነቡ መሆናቸውን፣ ሥርዓት ተፈጥሮላቸውና ሥርዓቱን ተከትለው የማይሠሩ መሆናቸው በግልጽ የሚታየው፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የመንግሥትና የግል ባንኮችን የሚከታተልና የሚቆጣጠር አካል ነው የሚል ሕግ አለ፡፡ እንደ ተቋም ይህን ኃላፊነት እንዲወጣ ሕግ ያስገድደዋል፡፡ በተግባር ግን ይህን ይፈጽማል? ደፈር ብሎ እንትን የተባለ ባንክን ይቆጣጠራል፤ ያዛል፡፡ ፈርቶ ደግሞ እንትን የተባለ ባንክን ለመቆጣጠር ይሽመደመዳል፡፡ አንዱ ባንክ ዞር በል ሲለው ያዙኝ ልቀቁኝ ይላል፡፡ ሌላው ባንክ ዞር በል ሲለው እውነትም በፍርኃት ዞር ይላል፡፡ እንደ ተቋም አይንቀሳቀስም፡፡ ወጥ ሥርዓት አይከተልም፡፡ መሬት የሚሰጠውና የሚቀማው ማዘጋጃ ቤት ነው፡፡ ሕግን ተከትሎ፡፡

Why such Daunting Silences The Sidama Sons and Daughters?

December 08 2012 (Kukkisa, Our reporter from Sidama Capital Hawassa) Ohi!! the Sidama nation of north East Africa, From where may I start my lament? From where may I begin my argument? How can I reveal the hidden face of all evils and their architects? How can I unravel behind the scene secrets? How can I show you the poisonous policies? Perpetrated against your nation, the biggest story for an ongoing discussion? Or with what language on earth may I speak? The depth, magnitude and the extent of your ongoing grievances? Over a century old neglected pleas? And about the situation you’re obliged to live under, That is causing you untold disaster? How can I say and who can I speak to? In the land of lawlessness where brutalities rule over innocents!! From where may I start my laments? You fathers of the Sidama kids, unable to provide, to your families’ burning needs, As your lone attempt fail to succeed, Extremely confused, not knowing what to do, and where and to who to turn to, when you