Posts

የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አራት አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 15 ነጥብ 5 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በይርጋለም የተቀናጀ ኢንደስትሪ ፓርክ አማካኝነት መገኘቱን ገለፀ

Image

የ1445ኛውን የረመዳን ፆም መግባት አስመልክቶ የሲዳማ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል

Image

ቡና አቅራቢዎች ክፍያ እየተፈጸመላቸው ባለመሆኑ ከገበያ ለመውጣት መገደዳቸውን አስታወቁ

Image
ቡናና ሻይ ባለሥልጣን በአምስት ኤክስፖርተሮች ላይ ዕርምጃ ወስጃለሁ አለ ቡና አቅራቢዎች ቡናቸውን ለኤክስፖርተሮች ሲያቀርቡ ክፍያ በትክክለኛው መንገድ ስለማይፈጸምላቸውና ከባንኮች ብድር በአግባቡ ስለማያገኙ፣ ከገበያ ለመውጣት መገደዳቸውን ተናገሩ፡፡ ቡና አቅራቢዎቹ ይህንን የተናገሩት ዓርብ የካቲት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆን፣ የ‹‹ቀጥታ የገበያ ትስስር››ን ወይም (ቨርቲካል ኢንተግሬሽን)ን በተመለከተ ከአርሶ አደሮችና ከቡና አቅራቢዎች ጋር ውይይት ሲያካሂዱ ነው፡፡ አብዛኛዎቹ ቡና አቅራቢዎች ንብረታቸውን አስይዘው ከአርሶ አደሩ ቡና ከገዙ በኋላ ለኤክስፖርተሮች በሚሸጡበት ጊዜ፣ ኤክስፖርተሮች ‹‹የሸጣችሁልን ቡና የቡናና ሻይ ባለሥልጣን ያስቀመጠውን መሥፈርት አላሟላም›› በማለት ዓመቱ ሙሉ ገንዘባቸውን ይዞ እንደሚያንገላቷቸው የጅማ ዞን ቡና አቅራቢዎች ማኅበር ሊቀመንበር አቶ ናስር አብዱ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በፊት ቡና አቅራቢዎች ለኤክስፖርተሮች ቡናቸውን በመሸጥ ይተዳደሩ እንደነበር፣ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት የቡናና ሻይ ባለሥልጣን ባወጣው ደንብ ቡና አቅራቢዎችም ሆኑ አርሶ አደሮች ቡናቸውን በቀጥታ ኤክስፖርት ማድረግ መቻላቸውን ገልጸው፣ ዘንድሮ በቀጥታ ቡና በመላክ 2.5 ሚሊዮን ዶላር ማግኘት እንደቻሉ አስረድተዋል፡፡ በሌላ በኩል በተወሰኑ ኤክስፖርተሮች የቡና ግብይት በሞኖፖሊ በመያዙ ቡና አቅራቢዎች ብዙ ጊዜ የውጭ ገበያ ሰንሰለቱ ላይ ችግር እንደሚገጥማቸው የተናገሩት ሊቀመንበሩ፣ ቡና አቅራቢዎች በቀጥታ የገበያ ትስስር ከውጭ ገዥዎች ጋር የሚገናኙበት ሁኔታን መንግሥት መፍጠር አለበት ብለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አንዳንድ ኤክስፖርተሮች የውጭ አገር ፈቃድ በማውጣት በሕገወጥ መንገድ ቡና እንደሚሸ

በናይጀሪያ በተካሔደው የብየዳ ክህሎት ውድድር ከሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መምህርት የሆነችው ወለላ ሰኢድ ኢትዮጵያን ወክላ ልዩ ተሸላሚ ሆነች

Image
ወለላ ሰዒድ ተሸላሚ የሆነችው ናይጀሪያ በተሰናዳው የአፍሪካ ብየዳ ፌደሬሽን ጉባኤ እና የጥናትና ምርምር ሴሚናር ላይ በኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ወክለው ከተሳተፉ ባለሙያዎች መካከል አንዷ ናት። በዚህ እየተካሄደ በሚገኘው የብየዳ ክህሎት ውድድር በብየዳ ልህቀት ማዕከል ስልጠና ዓለምአቀፍ ሰርቲፊኬት ባለቤት የሆነችው እና በአሁኑ ጊዜ በክረምት ወራት ቴክኖሎጂ ማበልጸጊያ ፕሮግራም (summer camp) ተሳታፊ የሆነችው ወለላ ሰኢድ ልዩ ተሸላሚ ሆናለች። በዚህ አህጉር አቀፍ የብየዳ ክህሎት ውድድር አለም አቀፍ የደረጃ 6 የብየዳ ሰርተፊኬት ባለቤት የሆኑት ስንታየሁ አብና አግርሶ ሀሪሶ ከሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኢትዮጵያን ወክለው ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነው ታይተዋል። ኢትዮጵያ በኢንስቲትዩታችን እየተመራች የአፍሪካ ብየዳ ፌደሬሽን መስራች አገር መሆኗ ይታወቃል። ምንጭ:- 

የእንሰት ተክልን ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን አየሰራ መሆኑን የፌዴራል ግብርና ሚንስተር የእርሻና ሆርቲ ካልቸር ዘርፍ አስታወቀ

Image

የስኮትላንዱን Kilt/ ክሊትን እና የሲዳማውን ጎንፋ ምን ያመሳስላቸዋል?

Image
ታላቋን ብርቲን UKን ከፈጠሩት አራት አገራት መካከል አንዷ የሆነችው ስኮትላንድ፤ ከሲዳማ ጋር የሚያመሳስላት አንድ ነገር አለ። ይሄውም ወንዶቻቸው የምለብሱት ባህላዊ ልብስ ነው። ልብሱ ከሲዳማዎቹ ጎንፋ ጋር መመሰሰሉ ብቻ ሳይሆን፤ ታርካዊ እና ባህላዊ ፋይዳው አንድ ነው። Kilt ክሊት በስኮትላንድ ሴሊቲክ ህዝብ ዘንድ በባህላዊ ልብስነት በወንዶች የሚለበሰ ሲሆን፤ እስከ ጉልበት የሚረዥም የሴቶቹን ቀምስ የሚመስል አልባስ ነው። አመጣጡን ተመለከተ እንደ አእሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር ከ16ተኛ ክፍለ ዘመን ጀምሮ፤ በተለይ በስኮቲሽ ሃይላንድ/ Scottish Higlands ይኖሩ በነበሩ የሴልቲክ አባል የሆነ ወንድ አዋቂዎች እና ወጣት ወንዶች ለብርድ መከላከያ እንደ ጋቢ ይለበስ የነበረ ሲሆን፤ ከ18ተኛው ክፍለዘመን ጀምሮ ግን ከወገብ በታች እስከ ጉልበት ድረሰ በማስረዘም መልበስ መጀመሩ ይነገራል።   ከ19ተኛው ክፍለዘመን ጀምሮ ክሊት በከፍታማ የአገሩቱ አከባቢዎች ብቻ ሳይሆን፤ በአጠቃላይ እንደየአገሪቱ ባህላዊ ልብስ በአብዘኛው በተለይ በወንዶች በተለያዩ ባህላዊ ክንውኖች እና ዝግጅቶች ላይ መዘወተር መጀመሩ ይነገራል። ክሊት እንደ ጎንፋ ሁሉ ከተለያዩ ማይቴሪያሎች የሚሰራ ቢሆንም፤ በአብዘኛው ግን ከጥጥ ግብአት እንደሚመረት ተገልጿል። በመላው አለም ታዋቂነትን ያተረፈው ክሊት፤ በስኮትላንዶች ዘንድ ከአርበኝነትና ከብሔራዊ ማንነት መገለጫነት አልፈው፤ ጥልቅ የሆነ ባህላዊ እና ታርካዊ ፋይዳ እንደለው ይነገራል። በዚህም ስኮትላንዶች በዚህ ባህላዊ ልብስ ከፍተኛ ኩራት እንደምሰማቸው ታውቋል። በርግጥ እኛም በጎንፋችን ከፍተኛ ኩራት እንደምሰማን ይገባኛል። ለማንኛውም የእኛውን ጎንፋ በአለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ከፊቼ በላይ ምን አማራጭ አለ?   በነገራችን ላይ የድሮው ባለ

ሐዋሳን ጨምሮ፤ የአምስት ዲጂታል መልቲሚዲያ ስቱዲዮዎች ተመረቁ

Image