Posts

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

Image
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እስኪጠናቀቅ ከቦንድ ግዥ በተጨማሪ በምርምር ስራ አስፈላጊውን ሙያዊ ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀቱን የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡ የህዳሴ ግድቡን ዋንጫ አቀባበል ምክንያት በማድረግ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች፣ መምህራንና ሰራተኞች ለግድቡ ግንባታ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት አቶ አያኖ በራሶ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እስኪጠናቀቅ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ድጋፉን አጠናክሮ ለመቀጠል ቃል ገብቷል፡፡ የህዳሴ ግድቡ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ከተጣለበት ጊዜ አንስቶ በቦንድ ግዥ፣ በዕውቀትና በክልሉ በግድቡ ዙሪያ በሚደረጉ የውይይት መድረኮች የተቋሙ ምሁራን ሙያዊ ማብራሪያ በመስጠት ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በምርምር ረገድም ራሱን የቻለ የውሀ ዘርፍ እንዳለው ጠቁመው በቀጣይም የአባይ ውሀ ሀገሪቱ የበለጠ መጠቀም የምትችልበትን ሁኔታን በጥናት በመለየት አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን አቶ አያኖ ገልጸዋል፡፡ የህዳሴ ግድቡ ዋንጫ ሀዋሳ መግባቱን ተከትሎ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች፣ መምህራንና ሰራተኞች በስጦታና በቦንድ ግዥ ከ30 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውንም አመልክተዋል፡፡ በግላቸው ለሶስተኛ ጊዜ በወር ደመወዛቸው የቦንድ ግዥ መፈጸማቸውንም ጠቁመዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲው የኬሚስትሪ የትምህርት መስክ የሶስተኛ ዓመት ተማሪ ዮርዳኖስ ገብረስላሴ በበኩሏ የአባይ ወንዝ ለሀገሩ ጥቅም እንዲሰጥ የግድቡ መገንባት የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ እንደሆነ ጠቅሳ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ዋንጫ ወደ ዩኒቨርሲቲው መምጣቱ እንዳስደሰታት ተናግራለች፡፡ የኮምፒውተር ሳይንስ የአራተኛ ዓመት ተማሪው  ታደሰ አይጠገብ በሰጠው አስተ