Posts

Lake Hawassa project

Image
Lake Hawassa project

የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት በጨፌ ኮቲጀቤሳ ለሚገኙ እማወራ ገበሬዎች የምርጥ ዶሮ ዝርያዎች አከፋፈለ

Image
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በጨፌ ኮቲጀቤሳ ለሚገኙ ባለሙያዎችና እማወራ ገበሬዎች ለሁለት ቀናት (ከ11/2/ዐ9-12/2/ዐ9) በዘመናዊ ዶሮ እርባታና አያያዝ ዙሪያ ስልጠና በመስጠት ምርጥ የዶሮ ዝርያዎችን አከፋፈለ፡፡   ዶ/ር ተስፋዬ አበበ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴ/ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት በወቅቱ እንደተናገሩት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በስሩ በርካታ ስራዎችን እየሰራ ያለ ሲሆን የዛሬውም ይህ ስልጠና እና የምርጥ ዘርዶሮዎች ማከፋፈል ከነዚሁ አንዱ መሆኑን ገልጸው ይህንን Ýሮግራም የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከኤስ.ኦ.ኤስ የህፃናት መንደር ጋር በጋራ የሚሰሩት መሆኑን አክለው ገልፀዋል፡፡   ይህ ፕሮጀክት ከዚህ በፊት ለ5ዐ7 ተማሪዎች ድጋፍ በማድረግ ትምህርታቸውን እንዲማሩ ያስቻለ ሲሆን ልጆቹ በአግባቡ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ወላጆቻቸውን መደገፍ አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት ለሃያ አምስት እማወራዎች አስር ምርጥ የዶሮ ዝርያዎችን ከሃምሳ ኪሎ ግራም መኖ ጋር መከፋፈላቸውን አቶ ዮሐንስ ዮና የዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ገልፀዋል፡፡   እኝህ እማወራዎች የተመረጡት በመነሻ ጥናትና የቤተሰቡ የዕድገት ዕቅድ ጥናት ታይቶ ሲሆን ምርጥ የዶሮ ዝርያዎቹም በአካባቢው አርሶ አደሮች ተሞክረው ውጤታማ የሆኑና ተቀባይነት ያገኙ መሆናቸውን አቶ ካሳው አስማረ የኤስ.ኦ.ኤስ የህፃናት መንደር Ýሮግራም ዳይሬክተር አስታውቀዋል፡፡ Source:http://www.hu.edu.et/hu/index.php/news/470-%E1%88%9D%E1%88%AD%E1%88%9D%E1%88%AD.html