ሀዋሳ 5ኛውን የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ታዘጋጃለች
ግንባታው እየተጠናቀቀ ያለውና 40 ሺ ሰዎችን መያዝ የሚችለው የሀዋሳ ስታዲየም የውድድሩ ድምቀት እንደሚሆን ይጠበቃል፤ 8 ኛው የፌዴራል ስፖርት ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ከትናንት በስቲያ በተጠናቀቀበት ወቅት በ 2008 ዓም የሚካሄደውን የ 5 ኛውን መላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች እቅድ ሰነድ አጽድቋል። ውድድሩን የሀዋሳ ከተማ ታስተናግዳለች። ጉባኤው ሰነዱን ያጸደቀው ከትናንት በስቲያ በተናቀቀበት ወቅት ነው። በ 1999 ዓም የተጀመረውና ሁሉንም ክልሎች ባሳተፈ መልኩ የሚካሄደው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የኦሎምፒክን ጽንሰ ሃሳብን ይከተላል። በየሁለት ዓመቱ የሚዘጋጀው ይህ ውድድር ብዛት ባለው የስፖርት ዓይነት ብዛት ያላቸውን ስፖርተኞች በማሳተፍም ይታወቃል። በ 2008 ዓ . ም የሚካሄደው የ 5 ኛው መላ ኢትዮጵያ ጨዋታም በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል በሃዋሳ ከተማ የሚዘጋጅ ይሆናል። የጨዋታው እቅድ ሰነድም በፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን የስፖርት ተሳትፎና ውድድር ፌስቲቫል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ በቀለ ቀርቧል። በዕቅዱም ላይ በሃዋሳ ከተማ በሚዘጋጀው ውድድር ተጫዋቾችን፣ አሰልጣኞችን፣ የቡድን መሪዎችንና ሌሎችንም ጨምሮ 4 ሺ 150 የሚሆኑ የልኡካን ቡድን አባላት ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል። በዚህም መሰረት ከጥር 1 እስከ መጋቢት 30 ቀን 2008 ዓ . ም ድረስ ክልሎች ዝግጅታቸውንና የተጫዋቾች መረጣቸውን እንደሚጨርሱ በእቅዱ ላይ ተገልጿል። በዚህም መሰረት የክልሉ መንግስት ባለፈው ዓመት አዘጋጅ ከነበረው የኦሮሚያ ክልል መልካም ተሞክሮዎችን እንዳገኘ ተገልጿል። ክልሉ ለውድድሩ ማካሄጃ የሚያውላቸው የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ዝግጅት ከወዲሁ ተጀምሯል። አዲሱ የሃዋሳ ከተማ ስታዲየም፣ የደቡብ ክልል ፖሊስ ሜዳ እንዲሁም