ጉዞ ወደ ጥበበኞቹ አገር
በዘንድሮው በዓል አዛውንቶች ( አያንቱዎች ) የበዓሉ ድምቀት ሆነው ሰንብተዋል፤ በአንድ አገር ውስጥ ማህበረሰባዊ የተቋም ሽግግር እንዲመጣ፣ የህዝቦች የጋራ እሴት እንዲጎለብት እና የትውልድ ቅብብሎሽ መኖር መሰረታዊ ስለመሆኑ የሚያጠያይቅ አይደለም። ሀገር ያለ ሰው አይደምቅም። ሰውም ያለ ሀገር አይፈጠርም። ለሀገር ዘመን ተሻጋሪ ድርና ማጉ ህዝብ ነው። የአንድ ህዝብ ታሪክ መሰረቱ የተከታታይ ትውልዶች ሥራ ነው። እያንዳንዱ ትውልድ ማህበራዊ አንድነቱንና አብሮ የመኖር ህልውናው አረጋግጦ ለሚቀጥለው ትውልድ የሚያስተላልፈው እሴት የዛ ህዝብ የማንነት መገለጫ ነው። የአንድ ህዝብ አገር በቀል እውቀት፣ ልምድ፣ ትውፊታዊ እምነት፣ ወግና ስርዓት፣ ያለፉትን ተከታታይ ትውልዶች ከዛሬው ከወደፊቱ ትውልዶች ጋር የሚያገናኝ፣ የሚያስተዋውቅና የሚያስተሳስር ሰንሰለት ነው። ያ ህዝብ የራሱን የኑሮ ዘይቤ በመደንገግና በመቅረፅ ሥርዓት ባለው መልኩ ህይወቱን ለመምራት ያደረጋቸው የለውጥ ሂደቶች የስብዕናው መገለጫዎችም ሆነው ይስተዋላሉ። ጉዞአችን በደቡብ ምስራቅ አቅጣጫ ነው። የሲዳማ ህዝብ በደቡብ ክልል ከሚገኙ ብሄር ብሄረሰቦች ህዝቦች መካከል አንዱ ነው። ዞኑ በሰሜን ምስራቅና በደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ክልል እንዲሁም በስተምዕራብ የወላይታ ዞን ያዋስኑታል። የሲዳማ ህዝብ የራሱ የሆነ ቋንቋ ፣ የዘመን አቆጣጠር፣ ባህል፣ ስርዓት፣ ትውፊት፣ ወግና ሥርዓት ያለው ነው። ቋንቋው ሲዳምኛ ነው። የሲዳማ ብሄር የማንነቱ መለያና መገለጫ የሆኑ የበርካታ ባህላዊ ፣ታሪካዊና ማህበራዊ የአኗኗር ዘይቤ እሴቶች ባለቤት ነው። ከእነዚህ መካከል የፊቼ ጨምበላላ በዓል ዋና እና ቀዳሚው ከሆኑ