Posts

ለድርቅ አደጋ በተጋለጡ አንዳንድ አካባቢዎች ዝናብ መዝነብ ጀምሯል

Image
በሰኔና ሐምሌ ዝናብ ባልዘነበባቸውና ለድርቅ አደጋ በተጋለጡ አፋርና ወሎ እንዲሁም ሃረርና ድሬደዋ አካባቢ ሰሞኑን ዝናብ መዝነብ እንደጀመረ ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡ በድርቅ አደጋ በቀን እስከ 100 የቤት እንስሳት እየሞቱ በነበረበት የአፋር ክልል በአሁን ወቅት አስቸኳይ እርዳታና ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮቹ፤ በተለይ ከሎጊያ እስከ ክልሉ ዋና መቀመጫ ሠመራና አካባቢው ተደጋጋሚ ዝናብ እንደዘነበ ተናግረዋል፡፡ ድርቅ ተከስቶባቸው ከነበሩ ቦታዎች አንዱ የድሬደዋና ሀረር ቆላማ አካባቢ ከባለፈው ሠኞ ጀምሮ መጠነኛ ዝናብ እየዘነበ ሲሆን በድሬደዋ ከተማ ጠንከር ያለ ዝናብ መዝነቡን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በድሬደዋ ገጠራማ አካባቢዎች ግን አሁንም የዝናቡ ሁኔታ የሚጠበቀውን ያህል አለመሆኑን ምንጮች ለአዲስ አድማስ ጠቁመዋል፡፡ ከሰሜኑ የአገሪቱ ክፍሎች አንዱ በሆነውና ከፍተኛ የድርቅ ስጋት አንዣቦበት የነበረው ከሸዋሮቢት እስከ ወሎ ባለው መስመር በሣምንቱ ተደጋጋሚ ዝናብ መዝነቡን በአካባቢው የሚገኙ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ በምስራቅ ስምጥ ሸለቆ አካባቢ ተብሎ በሚታወቀው ከአዳማ እስከ መተሃራ ባለው አካባቢም በሳምንቱ የሚጠበቀውን ያህል ባይሆንም ዝናብ መዝነብ መቻሉን በአካባቢው የሚመላለሱ ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡ የብሄራዊ ሜትሪዎሎጂ አገልግሎት ማክሰኞ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በሰኔና በሐምሌ ወር በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እንዲሁም በመካከለኛው ምስራቅ ስምጥ ሸለቆ አካባቢዎችና በምስራቁ የሀገሪቱ ክፍሎች ከመደበኛ በታች ዝናብ መዝነቡን ጠቅሶ በነሐሴ ወር በነዚህ አካባቢዎች የዝናቡ መጠን ሊጨምር እንደሚችል ተንብይዋል፡፡ በዘንድሮ ክረምት የተፈጠረው የዝናብ እጥረት

ሂዩማን ራይትስ ዎች ለኢትዮጵያ የመረጃ ጠለፋ ቴክኖሎጂ ሸጧል ያለውን ተቋም ከሰሰ

Image
ተቋሙ ከኢትዮጵያ ጋር መስራቴን  ሙሉ ለሙሉ አቋርጫለሁ ብሏል አለማቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ሂዩማን ራይትስ ዎች ለኢትዮጵያ የመረጃ ጠለፋ ቴክኖሎጂዎችን ሸጧል፤ ለደህንነት ባለሙያዎች ስልጠና በመስጠት የዜጎች መብቶች እንዲጣሱ እገዛ አድርጓል ያለውን “ሃኪንግ ቲም” የተባለ የጣሊያን ተቋም በጉዳዩ ዙሪያ በቂ ምላሽ አልሰጠም፣ የመብቶች ጥሰቶችን ለማስቆምም እርምጃ አልወሰደም ሲል ከሰሰ፡፡ ሃኪንግ ቲም ለተለያዩ አገራት መንግስታት የመረጃ መጥለፊያ ቴክኖሎጂዎችን በመሸጥና ለባለሙያዎች ስልጠና በመስጠት፣ መንግስታት የዜጎችን ሰብአዊ መብቶች እንዲጥሱ እገዛ ያደርጋል ያለው ሂዩማን ራይትስ ዎች፣ በኢትዮጵያ ሲከናወን የቆየውን የመረጃ ጠለፋና የመብቶች ጥሰት በተመለከተ ምላሽ እንዲሰጠው ቢጠይቅም በቂ ምላሽ ሊሰጠው እንዳልቻለ ከትናንት በስቲያ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ተቋሙ ጉዳዩን በተመለከተ ምርመራ ለማድረግም ሆነ የኢትዮጵያ መንግስት ቴክኖሎጂውን በመጠቀም በዜጎቹ ላይ የሚያደርሰውን የመብቶች ጥሰት ለማስቆም ምንም አይነት ተጨባጭ እርምጃ አልወሰደም ሲል የከሰሰው ሂዩማን ራይትስ ዎች፣ ሃኪንግ ቲም ለኢትዮጵያ የደህንነት ባለሙያዎች የግለሰቦችን ኮምፒውተሮች ሰብረው መግባት የሚችሉበትን ስልጠና መስጠቱን እንደቀጠለና ቀጣይ ስምምነቶችን ለማድረግ እንቅስቃሴ ጀምሮ እንደነበር የሚያረጋግጡ መረጃዎችን በሃምሌ ወር እንዳገኘ አስታውቋል፡፡ ሃኪንግ ቲም ለኢትዮጵያ መንግስት የሸጣቸው የመረጃ መጥለፊያ ቴክኖሎጂዎች ከቫይረስ መከላከያ ፕሮግራሞች አቅም በላይ እንደሆኑና በቀላሉ ወደ ግለሰቦች ኮምፒውተሮች በመግባት መረጃዎችን እንደሚወስዱ የጠቆመው ሂዩማን ራይትስ ዎች፣ ከተቋሙ ኢሜይል አፈትልከው የወጡ መረጃዎችም ተቋሙ በሚያዝያ ወር ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር

Sidama

Image
  Sidamigobba, or Sidama country, extends along the Great Rift Valley from Lake Hawassa in the north to the town of Dilla in the south and from Mount Garamba in the east to the Bilaatte River in the west. The Sidama are one of the original ... Read more at: Link  

የአየር ፀባይ መዛባት ያስከተለው ሥጋት

Image
የክረምቱ ዝናብ መዝነብ በሚገባው መጠንና ጊዜውን ጠብቆ እየዘነበ ባለመሆኑ፣ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ላይ ሥጋት አንዣቧል፡፡ ይህ የዝናብ እጥረት የተከሰተው የአየር ፀባይ ለውጥ ከሚያስከትሉት የንፋስ ዓይነቶች አንዱ የሆነው ኤልኒኖ በመከሰቱ መሆኑን ብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡ የዝናብ እጥረቱ በተለይም በምዕራብ ትግራይ፣ በአማራ፣ በደቡብ ኦሮሚያ፣ በአፋርና በሶማሌ ክልሎች መከሰቱ እየተነገረ ነው፡፡ በዚህም ሳቢያ በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ አርሶ አደሮች የዘሩት ፍሬ ሳይዝ ከመቅረቱም በላይ፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ከብቶች እየሞቱ መሆኑም ታውቋል፡፡ በምሥሉ ላይ በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን ዶዶታ ወረዳ የአንድ አርሶ አደር ቤተሰቦች የዘሩት ስንዴ በዝናብ እጥረት ምክንያት በመበላሸቱ ሽንኩርት ሲተክሉበት ይታያል፡፡  በዝናብ እጥረቱ ሳቢያ የተጋረጠውን ሥጋት የሚያስነብበውን የዳዊት ታዬ ዘገባ ለመመልከት እዚህ ጋር ይጫኑ ወይም በ ቢዝነስ እና ኢኮኖሚ ገጽ ላይ ይመልከቱ፡፡

የሀዋሳ ከተማ ምክር ቤት ከአንድ ቢሊዮን ብር የሚበልጥ በጀት አጸደቀ

Image
ጠንካራ የልማት ሰራዊት በመፍጠር የህብረተሰቡን ማህበራዊና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የምክር ቤት አባላት በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አሳሰቡ። ምክር ቤቱ ለ2008 የበጀት ዓመት ከ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አፅድቋል። የከተማውን የበጀት ዓመት አፈጻጸም ለምክር ቤቱ ባቀረቡበት ወቅት ከንቲባው አቶ ዮናስ ዮሴፍ እንደተናገሩት ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አመራሩ፣መላው ህዝብና ባለድርሻ አካላት ባደረጉት የተቀናጀ ጥረት አበረታታች ውጤት ተመዝግቧል። በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ብቻ በኮንስትራክሽን፣ በከተማ ግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በንግድና አገልግሎት ዘርፍ ከ54 ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል መፈጠሩን ገልጸዋል። በከተማው ከ275ሺህ ካሬ ሜትር የሚበልጥ የመሸጫና የማምረቻ ቦታ አዘጋጅቶ ማቅረቡን ገልጸው አቅማቸውን ለማጎልበትም የአደረጃጀት ፣የተስማሚ ቴክኖሎጂና የመረጃ አገልግሎት ድጋፍ መደረጉን አስታውቀዋል። በተቀናጀ ጥረት ከ320 ሚሊዮን ብር የሚበልጥ የገበያ ትስስር መፈጠሩን አስታውቀው ይህም ማህበራት ምርትና አገልግሎታቸውን በወቅቱ ለገበያ እንዲያቀርቡ ማስቻሉን ገልፀዋል። የከተማውን ንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ለማሻሻልና ተደራሽነቱን ለማሳደግ ከክልሉ መንግስት፣ከከተማው አስተዳደርና ከዓለም ባንክ በተገኘ ከ184 ሚሊዮን ብር የሚበልጥ ወጪ በመካሄድ ያለው የውሃ ተቋም ግንባታ ከ80 በመቶ በላይ መጠናቀቁን አስታውቀዋል። ምክር ቤቱ ለ2008 በጀት ዓመት እቅድ ማስፈፀሚያ ካጸደቀው በጀት አንድ ቢሊዮን ብር ከአስተዳደሩ የውስጥ ገቢ የሚሸፈን ቀሪው ከክልሉ መንግስትና ከዓለም ባንክ የሚገኝ ነው ብለዋል። ምንጭ፦ ኢዜአ