ባለስልጣኑ ሃዋሳን ጨምሮ የስምጥ ሸለቆ ሀይቆችን ከደለልና ከብክለት ለመከላከል እየሰራ ነው
ሀዋሳ ሰኔ 12/2007 የስምጥ ሸለቆ ሀይቆችን ከደለልና ከብክለት ለመከላከል ማህበረሰብ አቀፍ የተፈጥሮ ሀብትና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን በውሀ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ተፋሰስ ባለስልጣን አስታወቀ ። በባለስልጣኑ የስምጥ ሸለቆ ሀይቆች የተቀናጀ የተፋሰስ ልማትና እንክብካቤ ፕሮጀክት የ2007 የበጀት አመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና አውደ ጥናት በሃዋሳ ከተማ ተካሂዷል፡፡ ፕሮጀክቱ በ2004 በደቡብና ኦሮሚያ ክልሎች በሚገኙ ዘጠኝ ዞኖችና 21 ወረዳዎች የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ ስራን በማጠናከር በስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ላይ እያንዣበበ ያለውን አደጋ ለመከላከል ወደ ስራ መገባቱ ተገልጧል ። በዚህም በክልሎቹ ያሉ ሐይቆች፣ ወንዞችና ለተለያዩ አገልግሎቶች የተገነቡ ሰው ሰራሽ ግድቦችን ከደለል በመጠበቅ ዘላቂነት ያለው አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን የባለስልጣኑ ዳይሬክተር ዶክተር ከበደ ካንቹላ አስታውቀዋል ። ፕሮጀክቱ ተግባራዊ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ በጎርፍ እየታጠበ ወደ ሀይቆቹ የሚገባውን የደለል አፈር በመከላከል ረገድ የየአካባቢው ህብረተሰብ እያደረገ ያለው ተሳትፎም ውጤት እያስገኘ ነው ብለዋል ። በተለይ የሃዋሳን ሀይቅ ከብክለት ለመከላከል በተያዘው ጥረት ከከተማውና በዙሪያው ካሉ አካባቢዎች በጎርፍ ታጥቦ የሚመጣውን ኬሚካልና ደረቅ ቆሻሻ አጣርተው የሚያስቀሩ ሁለት ሰው ሰራሽ ኩሬዎችን በመገንባት እየተካሄደ ያለው የሙከራ ስራ አበረታች መሆኑ ተገልጧል ። በተጨማሪም ባለስልጣኑ በሀይቆቹ የሚገኙ ለምግብነት ያለደረሱ አሳዎችን ከጥፋት ለመታደግ በአሳ ማስገር ስራ ላይ ለተሰማሩ ማህበራት አባላት ስልጠና በመስጠት በሃላፊነት መንፈስ እንዲንቀሳቀሱ እየተደረገ መሆኑን አ