Posts

አይ ኤስ በሊቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ላይ የፈፀመውን አሰቃቂ ግድያ በማውገዝ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ነገ ሰልፍ ያካሂዳሉ

Image
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2007( ኤፍ.ቢ.ሲ ) አይ ኤስ በሊቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ላይ የፈፀመውን አሰቃቂ ግድያ በማውገዝ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ነገ ሰልፍ ያካሂዳሉ። በደቡብ አፍሪካ በወገኖቻችንና ሌሎች አፍሪካ ሃገራት ስደተኞች ላይ የተፈፀመውን ግፍና በሊቢያ አይ ኤስ አይ ኤስ የተባለው አሸባሪ ቡድን በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ የፈፀመውን የጅምላ ግድያ የሚያወግዝ ታላቅ ሃገራዊ የተቋውሞ ሰልፍ ነው ብሏል ሰልፉን ያስተባበረዉ የአዲስ አበባ ወጣቶች ፌዴሬሽን። የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደርም ድርጊቱ በሰው ልጅ ላይ የተፈጸመ አስነዋሪና አረመኔያዊ ድርጊት በመሆኑ መላው የከተማችን ነዋሪ በተደራጀ መልኩ ነገ ከጠዋቱ 3 ሰአት በመስቀል አደባባይ በመገኘት ድርጊቱን አምርረን እናውግዝ በማለት ጥሪ አስተላልፏል። በሰልፉ ላይ መንግስትና የከተማው ነዋሪ በተደራጀ መልኩ አስቀድሞ የጀመረውን የፀረ ሽብር ትግል አጠናክሮ እንደሚቀጥልበት ለሁሉም አሸባሪዎች፣ አክራረዎች እና ከዚህ ከሽብር የጥፋት ተልዕኮ ፖለቲካዊ ትርፍ እናገኛለን ብለው ለሚያልሙ ሃይሎች ጭምር ግልፅ መልእክት ይተላለፋል ተብሎም ይጠበቃል። በሰልፉ ላይም እስከ ግማሽ ሚሊዮን የሚደርሱ የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚገኙ ይጠበቃል። አይ ኤስ በኢትዮጵያዊያኑ ላይ ያደረሰው ዘግናኝ ግድያ ከአለማቀፉ ማህበረሰብ መወገዙን የቀጠለ ሲሆን፥ በርካታ ሀገራት እና አለማቀፍ ተቋማትም በአሸባሪ ቡድኑ ለተሰው ቤተሰቦችና በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ ህዝብ መፅናናትን እየተመኙ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝም ኢትዮጵያውያን ሽብርተኝነት የሀይማኖት ጭምብል ለብሶ መምጣቱ ሳያዘናጋቸው ሀይማኖት ሳይለዩ በአንድ ልብ እና ሃሳብ ቆመው ሊዋጉት እንደሚገባ ገልፀዋል። የሃይማኖት መሪዎችም ሆኑ ሰፊው ህዝብ

Ethiopia: 3 days of mourning after confirmation of Islamic State killings

ADDIS ABABA, Ethiopia –   Ethiopia's government has declared three days of mourning after confirming that many Ethiopians held captive in Libya were killed by the Islamic State group, after the group released a video on Sunday of the killings. The government said in a statement Monday that the days of mourning will be observed starting Tuesday and that during this time the national flag will fly at half-mast. The statement said that Ethiopia's lawmakers will meet Tuesday to discuss the killings and consider a response. A 29-minute video believed to be released by the Islamic militants shows at least 35 Ethiopian Christians held captive in Libya being shot or beheaded by extremists. Redwan Hussein, an Ethiopian government spokesman, said on Sunday that he believed the victims were Ethiopian migrants trying to reach Europe. http://www.foxnews.com/world/2015/04/20/ethiopia-3-days-mourning-after-confirmation-islamic-state-killings/

የኣብዘኛዎቹ የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ወንድ ተማሪዎች በዘንድሮው ኣገር ኣቀፍ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ በመረጭነት ኣለመመዝገባቸው ምስጥር ምንድነው?

Image
የወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ የ ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጠቅሶ እንደዘጋበው በሃዋሳ ዩኒቨርስቲ በዘንድሮው ምርጫ ላይ በመራጭነት ከተመዘጋቡት ተማርዎች መካከል 70 ከመቶ የሚሆኑት ሴት ተማሪዎች ናቸው። እንደዜና ምንጩ ዘጋባ ከሆነ በዩኒቨርሲቲው በስድስት ካምፓስ በተቋቋመዉ 31 የምርጫ ጣቢያዎች  በመራጭነት ከተመዘገቡት 4 ሺህ 359  ተማሪዎች  መካከል 3 ሺህ 40 ያህሉ ሴቶች መሆናቸውን  የሀዋሳ ከተማ አስተዳደርና ሲዳማ ዞን ምርጫ ማስተባበሪያ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ዱካሞ ተናግረዋል፡፡ ለዝርዝር ወሬውን ከታች ያንቡ፦ ሃዋሳ ሚያዝያ 10/2007 የፖለቲካ ፓርቲዎች በመገናኛ ብዙሃን እያካሄዱት ያለው የምረጡኝ ቅስቀሳና የክርክር መድረክ የተሻለ አማራጭ ፖሊሲና ፕሮግራም ያለውን ፓርቲ ለይተው እንዲያውቁ እንዳስቻላቸውን አንዳንድ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አስታወቁ። ከዩኒቨርስቲው ተማሪዎች መካከልየመስኖና ዉሀ ሃብት አስተዳዳር  የአራተኛ ዓመት ተማሪ ፍሬወይን ኢታይ በሰጠችው አስተያየት በመገናኛ ብዙሃን የሚካሄደው የምረጡኝ ቅስቀሳና የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር ማንን መምረጥ እንዳለብኝ ካሁኑ ለመወሰን ረድቶኛል " ብላለች። ተፎካካሪ ፓርቲዎቹ እያካሄዱት ያለው የምረጡኝ ቅስቀሳ በሀገሪቱ እየተገነባ ያለው የዴሞክራሲ ሥርዓት ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ የሚያሳይ መሆኑንም አስረድታለች፡፡ እንዲሁም በዙሁ ትምህርት ዘርፍ የአምስተኛ ዓመት ተማሪ መዓዛ ገብረ መድህን በበኩሏ ከባርቲዎች የምረጡኝ ቅስቀሳና ክርክር በምርጫው ሀገሪቱንና ህዝቦቿን ከድህነትና ኃላቀርነት ለማላቀቅ ብቃት ያለውን ፓርቲ ለይታ ለመምረጥ የሚያስችላትን ዕውቀት እንዳገኘች ገልፀዋለች፡፡ " በተለይ የሴቶችን ዴሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶች

ክልል አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች መድረክ ዛሬ በሃዋሳ ከተማ ተካሄደ

Image
(ኤፍ.ቢ.ሲ) በመጪው ግንቦት የሚካሄደው 5ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ ፣ ፍትሃዊ፣ ነፃ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ እና ፓርቲዎች እስካሁን የተጓዙበትን መንገድ ቆም ብለው የሚመክሩበት ክልል አቀፍ መድረክ በሀዋሳ ከተማ ዛሬ ተካሂዷል። በመድረኩ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ለክልል እና ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የሚወዳደሩ ፓርቲዎች ተሳትፈውበታል። የእስካሁኑን የምርጫ ሂደትን ለመፈተሽ ምርጫውን ሰላማዊ በሆነ መልኩ በስኬት ለማካሄድ የባለድርሻ አካላት ሚና የሚል የመነሻ ፅሁፍም ቀርቦም ውይይት ተካሂዶበታል። መድረኩ ደኢህዴን /ኢህአዴግ በምርጫው የድርጅቱ የእስካሁን እንቅስቃሴ የሚፈተሽበት ምቹ አጋጣሚ መሆኑን በፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የድርጅቱ ተወካይ አቶ ሁሴን ኑረዲን ቀደም ብለው ተናግረዋል። መድረኩ ፓርቲው ያጋጠሙ ችግሮችን እና የተፈቱበትን መንገድ እንዲሁም መጪው ምርጫ የተሳካ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሚጠበቅበትን ሁሉ ለማድረግ መዘጋጀቱን ለማሳወቅ ጠቃሚ መሁኑን ነው ያነሱት። በደቡብ ክልል የኢትዮጵያውያን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኢዴፓ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ለገሰ ላንቃሞ በበኩላቸው ፥ መድረኩ በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ መዘጋጀቱ ፓርቲዎች ያሏቸውን አማራጮች ለህብረተሰቡ ለማቅረብ ይረዳል ብለዋል። በሃዋሳ እየተካሄደ ባለው መድረክ ላይ የተለያዩ ፓርቲዎች ሃላፊዎች እና ተወካዮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ታድመውበታል። ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት፣ ደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ፅህፈት ቤት በጋራ በመተባባር ነው መድረኩን ያዘጋጁት። በአጠቃላይም በመድረኩ ላይ ሶስት ጥናታዊ ፅሁፎች ለውይይት ቀርበዋል።