የኣብዘኛዎቹ የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ወንድ ተማሪዎች በዘንድሮው ኣገር ኣቀፍ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ በመረጭነት ኣለመመዝገባቸው ምስጥር ምንድነው?
የወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ የ ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጠቅሶ እንደዘጋበው በሃዋሳ ዩኒቨርስቲ በዘንድሮው ምርጫ ላይ በመራጭነት ከተመዘጋቡት ተማርዎች መካከል 70 ከመቶ የሚሆኑት ሴት ተማሪዎች ናቸው። እንደዜና ምንጩ ዘጋባ ከሆነ በዩኒቨርሲቲው በስድስት ካምፓስ በተቋቋመዉ 31 የምርጫ ጣቢያዎች በመራጭነት ከተመዘገቡት 4 ሺህ 359 ተማሪዎች መካከል 3 ሺህ 40 ያህሉ ሴቶች መሆናቸውን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደርና ሲዳማ ዞን ምርጫ ማስተባበሪያ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ዱካሞ ተናግረዋል፡፡ ለዝርዝር ወሬውን ከታች ያንቡ፦ ሃዋሳ ሚያዝያ 10/2007 የፖለቲካ ፓርቲዎች በመገናኛ ብዙሃን እያካሄዱት ያለው የምረጡኝ ቅስቀሳና የክርክር መድረክ የተሻለ አማራጭ ፖሊሲና ፕሮግራም ያለውን ፓርቲ ለይተው እንዲያውቁ እንዳስቻላቸውን አንዳንድ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አስታወቁ። ከዩኒቨርስቲው ተማሪዎች መካከልየመስኖና ዉሀ ሃብት አስተዳዳር የአራተኛ ዓመት ተማሪ ፍሬወይን ኢታይ በሰጠችው አስተያየት በመገናኛ ብዙሃን የሚካሄደው የምረጡኝ ቅስቀሳና የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር ማንን መምረጥ እንዳለብኝ ካሁኑ ለመወሰን ረድቶኛል " ብላለች። ተፎካካሪ ፓርቲዎቹ እያካሄዱት ያለው የምረጡኝ ቅስቀሳ በሀገሪቱ እየተገነባ ያለው የዴሞክራሲ ሥርዓት ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ የሚያሳይ መሆኑንም አስረድታለች፡፡ እንዲሁም በዙሁ ትምህርት ዘርፍ የአምስተኛ ዓመት ተማሪ መዓዛ ገብረ መድህን በበኩሏ ከባርቲዎች የምረጡኝ ቅስቀሳና ክርክር በምርጫው ሀገሪቱንና ህዝቦቿን ከድህነትና ኃላቀርነት ለማላቀቅ ብቃት ያለውን ፓርቲ ለይታ ለመምረጥ የሚያስችላትን ዕውቀት እንዳገኘች ገልፀዋለች፡፡ " በተለይ የሴቶችን ዴሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶች