Posts

ህንድ በርበሬ የሚረጭ “አድማ በታኝ ድሮን” ልትጠቀም ነው፤ ከማን ኣይታ ይሁን?

Image
 “በርበሬን የመረጥነው የከፋ ጉዳት ስለማያደርስ ነው” - የአገሪቱ ፖሊስ    በሰሜናዊ ህንድ የምትገኘው ኡታር ፕራዴሽ ግዛት ዋና ከተማ የሆነችው የላክኖው ፖሊስ፣ ከአየር ላይ በርበሬ የሚረጩ አነስተኛ አድማ በታኝ ድሮኖችን በስራ ላይ ማዋል ሊጀምር ነው ሲል ቢቢሲ ዘገበ፡፡ ዘ ኢንዲያን ኤክስፕረስ ጋዜጣን ጠቅሶ ዘገባው እንዳለው፣ የግዛቷ ፖሊስ ህገወጥ ተቃውሞ የሚያደርጉ ዜጎችን ለመበተን የሚያስችሉና እያንዳንዳቸው 2 ኪሎ ግራም በርበሬ የመጫን አቅም ያላቸው አምስት አነስተኛ ድሮኖችን በስራ ላይ ለማዋል ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ “ህገወጥ አመጽ የሚያካሂዱ ዜጎችን በርበሬ እየረጨን እንበትናለን፡፡ ይህን ያልተለመደ የአድማ ብተና መሳሪያ ለመጠቀም የመረጥነው፣ በአመጹ ተሳታፊዎች ላይ የከፋ ጉዳት የማያደርስ በመሆኑ ነው፡፡ ህገወጥ ተቃውሞዎችንና የጎዳና ላይ አመጾችን በቁጥጥር ውስጥ በማዋል ረገድ ውጤታማ እንደሚሆንም ተስፋ አለን” ብለዋል ያሻዝቪ ያዳይ የተባሉት የግዛቲቱ ከፍተኛ የፖሊስ ባለስልጣን፡፡ የግዛቲቱ አስተዳደር ባለፈው አመት ባደረገው ሙከራ፤ በርበሬ የሚረጩ ድሮኖች አድማን በመበተን ረገድ ውጤታማነታቸውን በማረጋገጡ፣ ለእያንዳንዳቸው 10ሺህ ዶላር የከፈለባቸውን ድሮኖች በስራ ላይ ለማዋል መወሰኑንም ዘገባው አመልክቷል፡፡ ህንድ በርበሬ የሚረጩ አድማ በታኝ ድሮኖችን በመጠቀም ከዓለማችን አገራት ቀዳሚዋ እንደሆነችም ዘገባው አክሎ ገልጿል። ኣዲስ ኣድማስ

“የ97 ምርጫ ግርግር በኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች መረጃ ላይ ክፍተት ፈጥሯል”

Image
 የ1997 ዓ.ም የኮንዶሚኒየም ቤት ፈላጊዎች ምዝገባ ሂደት የተወሳሰቡ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ለተመዝጋቢዎች የመረጃ ሰነድ መጥፋትና አሁን ድረስ ለዘለቁ በርካታ ቅሬታዎች መነሻ ሆኗል ተባለ፡፡  በወቅቱ ምዝገባው በአዲስ አበባ አስሩም ክፍለከተሞችና በሌሎች ተቋማት የተከናወነ ሲሆን ሁሉም ወገን የምዝገባ ተራ ቁጥሮችን ከ001 የጀመሩ በመሆናቸው መረጃዎቹ ወደ አንድ ማዕከል ሲሰባሰቡ የመደበላለቅ ችግር ፈጥሯል ያሉት የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ሥራ አሥኪያጅ አቶ መስፍን መንግስቱ፤ አንድ ግለሰብ በተለያዩ መዝጋቢ ተቋማት ሶስትና አራት ጊዜ የተመዘገበበት አጋጣሚ እንዳለም ገልፀዋል፡፡  የምዝገባ ማረጋገጫ የነበረውን ቢጫ ካርድ ተመሳሳይ ቁጥር እስከ 15 የሚደርሱ ግለሰቦች ይዘው ወደ ማዕከሉ እንደሚቀርቡ ያስረዱት አቶ መስፍን፤ “ሁሉም መረጃዎች በአንድ ማዕከል ተሰባስበው ከተራ ቁጥር 001 እስከ 453ሺህ ድረስ በመቀመጡ፣ እነሱ ቁጥራችን የሚሉትና ሲስተሙ የሚያውቀው የምዝገባ ቁጥር የተለያዩ ናቸው” ብለዋል፡፡  ለወቅቱ ቤት ፈላጊዎች ምዝገባ እንደ ችግር የተጠቀሰው ሌላው ጉዳይ የ97 ምርጫን ተከትሎ የተፈጠረው ግርግር መረጃን በተገቢው መንገድ ለማደራጀት አለማስቻሉ ነው ይላሉ አቶ መስፍን። በወቅቱ ከተማዋን እንዲያስተዳድር አደራ የተሰጠው የባለአደራ አስተዳደር ስራውን ተላምዶ ወደ ተግባር እስኪገባ ድረስ መረጃዎቹ በተገቢው መንገድ ተይዘው ነበር ለማለት አያስደፍርም ብለዋል - ሃላፊው፡፡  በወቅቱ የተበላሸውን ለማስተካከል በርካታ ስራዎች መሠራታቸውን የጠቀሱት ሃላፊው፤ በ2005 ዓ.ም በተደረገው ምዝገባ፤ “መረጃን ጠፍቶብናል” ያሉ ቤት ፈላጊዎች በነባር የምዝገባ ስርአት ውስጥ ተካተው እንዲስተናገዱ መደረጋቸውን ተናግረዋል፡፡  የጋራ

THE XENOPHOBIC HORROR IN SOUTH AFRICA.

Image