Posts

Ethiopia's Current Election - 'Eliminating the Contestant Ahead of the Match'

It could well be said that literally no election had been completed happily to the minimal satisfaction of many contending political actors, and notably to a fair contentment of the Ethiopian people, ever since the assumption of power by the ruling Ethiopian People Revolutionary Democratic Front (EPRDF) in 1991. Nor is it uncommon to hear the major opposition parties blaming the ruling party for imposing upon them unbearable financial, physical, psychological and morale constrains before or during every election. Often, at the center of dissension are issues that have to do with the questionable impartiality of the National Electoral Board of Ethiopia (NEBE) and other state institutions directly or indirectly impacting the process and outcome of general elections. Owing to this, there were even occasions in the past whereby some opposition parties have gone to the extent of boycotting the ensuing election all together. In somewhat unprecedented manner this time around however ins

ሲዳማ ቡና መሪነቱን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ተረከበ

Image
ሃዋሳ መጋቢት 28/2007 በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የእግር ኳስ ግጥሚያ በ17ኛው ሳምንት ሲዳማ ቡና አርባ ምንጭ ከነማን ትናንት በይርጋለም ስታዲዬም ሁለት ለዜሮ በማሸነፍ መሪነቱን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ተረከበ። ጨዋታው በተጀመረ በ15ኛው ደቂቃ በ13 ቁጥሩ ኤሪክ አማካኝነት ባስቆጠረው ግብ ሲዳማ ቡና በመምራት እረፍት ወጥተዋል፡፡ ሲዳማ ቡና ከእረፍት መልስ አጥቅቶ በመጫወት የሁለተኛው አጋማሽ ጨዋታው በተጀመረ በሶስተኛው ደቂቃ በ21 ቁጥሩ አንዷለም ንጉሴ አማካኝነት ባስቆጠረው ጎል በማሸነፍ በሊጉ አናት ላይ ለመቀመጥ ችሏል። የአርባ ምንጭ ከነማ  አሰልጣኝ  አለማየሁ አባይነህ ከእረፍት በኋላ ጨዋታውን ለማሸነፍ ተጽዕኖ ፈጥረን ለመጫወት ብንሞክርም ውጤቱን መቀየር  አልቻልንም ዕድሎኞች አልነበርንም ብለዋል። የሲዳማ ቡና  አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ጨዋታው በጣም ከባድ ነበር ነገር ግን ያገኘናቸውን ዕድሎች ወደ ጎል በመቀየራችን አሸንፈን ለመውጣት ችለናል ብሏል። አሸንፈን መሪነቱን ብንይዝም ግባችን በቀጣይ ያሉንን ጨዋታዎች በሙሉ አሸንፈን ዋንጫውን ማንሳት ስለሆነ ይህንን ለማሳካት  ትኩረታችን ቀጣይ በሚኖሩን ጨዋታዎች ላይ ነው ብለዋል፡፡ በሊጉ 17ኛ ሳምንት ጨዋታውን ያደረገው ሲዳማ ቡና 35 ነጥብ በመያዝ ቅዱስ ጊዮርጊስን አስከትሎ ቀዳሚ ደረጃ ላይ ይገኛል። - See more at: http://www.ena.gov.et/index.php/sport/item/3438-2015-04-06-19-36-44#sthash.T3gPUk38.dpuf

በየመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጥቃት ተፈጸመበት

Image
በየመን ዋና ከተማ ሰነዓ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ መጋቢት 24 ቀን 2007 ዓ.ም. በጦር መሣሪያ ድብደባ ጥቃት ተፈጸመበት፡፡ ጥቃቱ በኤምባሲው ሠራተኞች ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት አለማድረሱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሆነው በቅርቡ የተሾሙት አቶ ተወልደ ሙሉጌታ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በኤምባሲው ላይ ጥቃት የተፈጸመው በየትኛው ተፋላሚ ወገን መሆኑ ለጊዜው አልታወቀም፡፡ የደረሰው አደጋ ከፍተኛ አለመሆኑንም ገልጸዋል፡፡  ከደረሰው የጦር መሣሪያ ጥቃት በኋላም ኤምባሲው መደበኛ ሥራውን የቀጠለ መሆኑን፣ በንብረት ላይ የደረሰውን አደጋ በዕለቱ መገመት እንደሚያስቸግርና ገና ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን ቃል አቀባዩ ጨምረው አስረድተዋል፡፡  በየመን የኢትዮጵያ አምባሳደር ሐሰን አብደላና የሥራ ባልደረቦቻቸው ከኢትዮጵያውያን በፊት የመንን ለቀው ባለመውጣታቸውና ወገኖቻቸውን ለመርዳት  ሲሉ እዚያ በመቆየታቸው፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ምሥጋና አቅርበውላቸዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ኤምባሲው ከመንግሥት ጋር በመሆን በየመን በተቀሰቀሰው ውጊያ ምክንያት የታገቱ ኢትዮጵያውያንን የማውጣት ሥራ ተጠናክሮ እንደቀጠለ አቶ ተወልደ ጠቁመዋል፡፡ ከቀናት በፊት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በየመን የሚገኙ ከ2,000 በላይ ኢትዮጵያውያንን በመመዝገብ ወደ አገራቸው በሰላም እንዲመለሱ አንድ ግብረ ኃይል ማቋቋሙን ገልጿል፡፡  ከውጭ ጉይ ሚኒስቴር በተገኘው መረጃ መሠረት እስከ መጋቢት 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ድረስ 11 ሕፃናትና 12 ሴቶችን ጨምሮ 30 ኢትዮጵያውያንን ወደ ጂቡቲ እንዲጓዙ ተደርጓል፡፡ ነገር ግን በየመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ በመሆኑና ከአካባቢው አስቸጋሪነት አ

‹‹በአንዴ ቀነኒሳ በቀለን መተካት አይቻልም››

Image
‹‹በአንዴ ቀነኒሳ በቀለን መተካት አይቻልም›› አቶ ዱቤ ጂሎ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ጉዳይ ዳይሬክተር  ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ የ12ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ሻምፒዮና  ስድስት ወርቅ፣ 12 ብርና 10 ነሐስ በድምሩ 28 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ሦስተኛ ደረጃ በመሆን ማጠናቀቋ ይታወሳል፡፡ እንዲሁም ቻይና ጉያንግ በተደረገው በ41ኛው ዓለም አቀፍ የአገር አቋራጭ  ውድድር ላይ በሴቶች አምስት ወርቅ፣ ሦስት ብርና ሦስት ነሐስ ሜዳሊያ ማግኘት ችላለች፡፡ በወንዶች ምድብ ያሲን ሃጂና በሴቶች ለተሰንበት ግደይ የወርቅ ሜዳሊያ ሲያመጡ፣ ደራ ዲዳና እታገኝ ወልዱ የብርና የነሐስ ሜዳልያ አግኝተዋል፡፡ በዚህ ምድብ ኢትዮጵያ የግልና የቡድን ወርቅን አሳክታለች፡፡ በአገር ውስጥና በውጭ ከተደረጉት ውድድሮች የተገኘው ውጤት ለቀጣይ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ምን አመላካች ነገር አሳይቷል በሚልና በተያያዥ ጉዳዮች የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ጉዳይ ዳይሬክተሩን አቶ ዱቤ ጂሎን  ዳዊት ቶሎሳ  አነጋግሯቸዋል፡፡  ሪፖርተር፡- በአሁኑ ጊዜ አትሌቲክሱ ያለበት ደረጃ እንዴት ይገለጻል?  አቶ ዱቤ ፡- እንደሚታወቀው በዓለም አቀፍ ደረጃ በተደረጉ ውድድሮች ላይ ኢትዮጵያም ባዘጋጀችው የወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮናም እንዲሁ በቻይናው የዓለም አገር አቋራጭ  ውድድሮች ላይ አትሌቶቻችን አመርቂ ውጤት ማምጣት ችለዋል፡፡ የአትሌቲክስ ደረጃም የሚለካው በአትሌቶች ውጤት በመሆኑ በታዳጊዎች፣ በወጣቶችና በአዋቂዎች ውጤት ማምጣት ተችሏል፡፡ በዚህ ውጤት መምጣት ፌዴሬሽኑ በስፋት ለአትሌቲክሱ ዕድገት ከአሠልጣኞች ጀምሮ እስከ አትሌቶች ድረስ ከላይ እስከ ታች ከክልሎችና ከማናጀሮች ጋር በመሆን ሰፊ ሥራ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡   ሪፖርተር፡- በአዲስ

የሃዋሳ ከተማ የእሳት ኣደጋ መከላከያ ብርጌድ ከፖላንድ መንግስት የስልጠናና የቁሳቁስ ድጋፍ ልደረግለት ነው

Image
የወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ የኣውሮፓ ኮሮስፖንዳንት የፖላንድ ዓለም ኣቀፍ ተራድኦ ማዕከልን ጠቅሶ እንደዘጋበው፤ በእሳት ኣደጋ ቁጥጥር ልምድ ያላቸውን ባለሙያዎች ያቀፍ ኣንድ ቡድን በሃዋሳ ከተማ ለሚገኙ የእሳት ኣደጋ መከላከያ ብርጌድ የኣቅም ግንባታ እና የቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግ በመዘጋጀት ላይ ነው። ለኣቅም ግንባታ እና ለቁሳቁስ ድጋፍ ስራ የሚውል ኣንድ ሚሊዮን የፖላንድ ዞልት የገንዘብ ድጋፍ ከኣገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተገኘ ሲሆን፤ ገንዘቡ ከሃዋሳ ከተማ በተጨማሪ ለባህር ዳር ከተማ እና ለሌሎች የኬኒያ ከተሞች መስል ድጋፎችን ለማድረግ እንደምውል ታውቋል። የፖላንድ መንግስት ለሃዋሳ ከተማ ይህንን ድጋፍ ለማድረግ የወሰነው የከተማዋ እሳት ኣደጋ መከላከያ ብርጌድ ከከተማዋ የህዝብ ብዛት እና እድገት ጋር በተያያዘ የሚከስቱትን የእሳት ኣደጋዎች የመከላከል ኣቅሙ ዝቅተኛ በመሆኑ መሆኑን የፖላንድ ኣለም ኣቀፍ ተራድኦ የስራ ሃላፊ የሆኑ ኣቶ ዎጅቺዬች ዊልክ ተናግረዋል። "The Ethiopian town Hawass firefighters can not effectively extinguish fires without approaching a fire on a dangerous distance for them. They have specialized clothing or equipment of a professional firefighter. The only thing I have is a blank breathing apparatus, approx. 100 meters of hose and two generators . It must be sufficient for 300 thousand. residents "- emphasizes Wolf.   በቅርቡ በሃዋሳ ከተማ ኣዲሱ ገበያ