Posts
በሁለተኛው ዙር 14ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ አዋሳ ከነማና ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል ሲቀናቸው ሲዳማ ቡና ነጥብ ተጋርቷል
- Get link
- Other Apps
10 ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ቅዱስ ጊዮርጊስና አዳማ ከነማ ባደረጉት ጨዋታ በቅዱስ ጊዮርጊስ 2 ለ 0 ሲያሸንፍ አዋሳ ከነማ አርባ ምንጭ ከነማን በተመሳሳይ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ማሸነፉን ተከትሎ መሪነቱን ከሲዳማ በመረከብ በ28 ነጥብ ሲመራ ሲዳማ ቡና በተመሳሳይ ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ ሁለተኝነት ይከተላል። ወላይታ ዲቻ ደግሞ በ26 ነጥብ ሶስተኛ ሆኗል። ለቅዱስ ጊዮርጊስ የአሸናፊነት ግቦችን ያስቆጠሩት ከዕረፍት በፊት ኡጋንዳዊ የመስመር አጥቂ ብሪያል ኦሙኒ እና ምንተስኖት አዳነ ናቸው፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ ዶስ ሳንቶስ '' ያገኘናቸውን አጋጣሚ መጠቀም ብንችል ተጨማሪ ግቦችን ማስቆጠር እንችል ነበር፤ ከመጀመሪያው አጋማሽ የበለጠ መንቀሳቀስም ችለን ነበር' ' ብለዋል፡፡ የአዳማ ከነማ አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ '' ከመጀመሪያው አጋማሽ በሁለተኛው የተሻለ መንቀሳቀስ ችለናል፣ ነገር ግን ቴክኒካልና ታከቲካል ስህተቶች ባለማረማችን ልንሸነፍ ችለናል '' ብሏል፡፡ አሰላ ላይ ሙገር ሲሚንቶ ከሲዳማ ቡና ጋር ያካሄደው ጨዋታ ያለምንም ግብ ሲጠናቀቅ አርባ ምንጭ ከነማ በሜዳው አዋሳ ከነማን አስተናግዶ 2 ለ 0 ተሸንፏል፡፡ በአዲስ አሰልጣኝነት አዋሳ ከነማን የተቀላቀለው ውበቱ አባተ በሜዳው አርባ ምንጭ ከነማን በማሸነፍ ፕሪሚየር ሊጉን በድል ጀምሯል፡፡ ለአዋሳ ከነማ ተመስገን ተክሉና መስቀል መንግስቱ ኳስን ከመረብ ያገናኙ ተጨዋቾች ናቸው፡፡ በነገው ዕለት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በአዲስ አበባ ደርቢ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ይጫወታሉ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ከናይጄሪያ ዋሪ ዎልቭስ ክለብ ጋር ዛሬ
የምርጫ ዘመቻና የመድረክ ወቀሳ
- Get link
- Other Apps
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ ባጭሩ) በቅርቡ በሚደረገዉ ምርጫ የሚወዳደሩ ዕጩዎቹና ምርጫዉን የሚያስፈፅሙ አባላቱ በየአካባቢዉ እየታሰሩ፤ እየተደበደቡና እየተንገላቱ ነዉ በማለት ወቀሰ። የመድረክ ባለሥልጣናት ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት አባላቶቻቸዉን የሚያስሩ፤ የሚደበድቡና የሚያንገላቱት የየአካባቢዉ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ፖሊሶች ናቸዉ። በደሉን ለማስቆም ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሁነኛ እርምጃ እንዲወስድ ባለሥልጣናቱ ጠይቀዋል።መድረክ ለምርጫዉ ያዘጋጀዉን የመወዳደሪያ ማንፌስቶም ይፋ አድርጓል። Read more
Hawassa Kenema collected 3 valuable away points following their 2-0 victory over Arba Minch Kenema
- Get link
- Other Apps
Addis Ababa, Ethiopia – Defending champions St. George joined Sidama Buna at the top of the Ethiopian Premier League following a 2-0 victory over Adama Kenema here today, while the latter was held to a scoreless draw by Mugher Cement in Assela. Although the two teams now have 28 points from 14 matches, St. George has a better goal difference (+12 vs +6). Meanwhile, struggling Hawassa Kenema collected 3 valuable away points following their 2-0 victory over Arba Minch Kenema. The second round of the league started in Gonder yesterday where the visiting Wolaita Dicha beat the Dashen Beer 1-0 and Mekelakeya defeated EEPCo 2-0 in Addis Ababa. The league will continue tomorrow with Commercial Bank of ethiopia (CBE) taking on Ethiopian Coffee and the match featuring Woldia Kenem a and Dedebit FC was postponed as the latter was competing in the CAF Confederation Cup
እንግሊዝ በኢትዮጵያ ያለው ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት አፈጻጸም ያሰጋኛል አለች
- Get link
- Other Apps
- የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ ላልተገባ ዓላማ እየዋለ ነው በሚል ተችታለች የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መጋቢት 3 ቀን 2007 ዓ.ም. ባወጣው የ2014 (እ.ኤ.አ.) የሰብዓዊ መብትና የዴሞክራሲ ሪፖርት፣ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ላይ ኢትዮጵያ በምትፈጽማቸው ገደቦች ሥጋት እንደገባው አስታወቀ፡፡ የፀረ ሽብርተኝነት አዋጁ ላልተገባ ዓላማ እየዋለ ነው በሚልም ተችቷል፡፡ የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ ሥራ ላይ ከዋለ በኋላ በቁጥጥር ሥር የዋሉት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላት፣ ጋዜጠኞች፣ ሰላማዊ ተቃዋሚዎችና ሌሎች አካላት ሕጉ ተጠቅሶ የተከሰሱት የመሰብሰብና ሐሳባቸውን በነፃነት የመግለጽ መብታቸውን ለመጠቀም ሙከራ ሲያደርጉ እንደሆነ ሪፖርቱ ይጠቁማል፡፡ በዓመቱ የዞን ዘጠኝ አባላት የሆኑ ሰባት ጦማሪያንና አቶ ተመስገን ደሳለኝን ጨምሮ 17 ጋዜጠኞች በቁጥጥር ሥር እንደዋሉም ሲፒጄን በመጥቀስ ሪፖርቱ አትቷል፡፡ ይህም ጋዜጠኞችን በማሰር ኢትዮጵያ ከዓለም በአራተኝነት ደረጃ እንደሚያስቀምጣት አመልክቷል፡፡ 30 ጋዜጠኞች በዓመቱ ከአገር እንደተሰደዱ የገለጸው ሪፖርቱ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የመክሰስ ሐሳብ ስለሌለው ሊመለሱ ይችላሉ ማለቱንም ጠቅሷል፡፡ እንግሊዝ ኢትዮጵያ የኦሮሚያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት 20 ጋዜጠኞች የተባረሩት በክልሉ የተከሰተውን የተማሪዎች አመፅ በዘገቡበት ተቺ አቀራረብ የተነሳ እንደሆነም እንደሚታመን ጠቅሷል፡፡ የአምስት መጽሔቶችንና የአንድ ጋዜጣ ኅትመት የተቋረጡትም በመንግሥት ውሳኔ እንደሆነ አመልክቷል፡፡ በአገሪቱ የኤሌክትሮኒክ ሚዲያ ተደራሽነት የተገደበ እንደሆነም ሪፖርቱ ጠቅሷል፡፡ የግል አሳታሚዎች በተመጣጣኝ ዋጋና በአስተማማኝ ሁኔታ የማተሚያ ቤት አገልግሎት ማግኘት አለመቻላቸውም እንደ ሳንካ እንደሚቆጠር ገልጿል፡፡ ለጋዜጠኞች