Posts

የኢትዮጵያ መንግሥት ጋዜጠኞችን ለመከታተል የስለላ የኮምፕዩተር ፕሮግራሞችን መጠቀም ጀመረ

Image
በቶሮንቶ ካናዳ ዩኒቨርሲቲ መንክ በተሰኘዉ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ተቋም የሚገኘዉ የሲትዝን ላይ ተመራማሪዎች ባለፈዉ ታህሳስ ወር መጨረሻ ገደማ ላብ ነበር ከኢሳት ዋና ሥራ አስኪያጅ ከአቶ ነአምን ዘለቀ ምንነቱን እንደሚለከቱ አንድ ኤሜይል የደረሳቸዉ። እንደዘገባዉ አቶ ነአምን ስለምርጫ 2015 መረጃዎች እንደያዘ የሚጠቁመዉን የኢሜይል መልዕክት ዉስጡን በመጠራጠር ነበር የፀጥታ፤ የሰብዓዊ መብቶችና የመረጃ ቴክኒዎሎጂን በሚመለከት ለሚመራመረዉ ቡድን ያስተላለፉት። ብዙም ሳይቆይ ሲቲዚን ላብ ያ መልዕክት በመንግሥት የሚተዳደረዉ የኢትዮ ቴሌኮም የኮምፕዩተር ማዕከል ጋ የተገናኘ መሆኑን እንደረሰበት ይገልጻል። የሂዉመን ራይትስ ዎች የኢትዮጵያ ጉዳይ ተመራማሪ ፊሊክስ ሆርን፤ «የሲቲዝን ላብ ተመራማሪዎች በርካት ተመሳሳይ ጉዳዮችን አግኝተዋል። ከኢሳት ጋ ግንኙነት ያላቸዉ በዉጭ የሚገኙ ጋዜጠኞች ለመንግሥታት ሰላይ የኮምፕዩተር ፕሮግራም በሚያቀርበዉ በጣሊያን ኩባንያ የስለላ ፕሮግራም በየግላቸዉ ጥቃት እንደደረሰባቸዉ አረጋግጠዋል። አንድ ኮምፕዩተር አንዴ በዚያ ሰላይ ፕሮግራም ከተጠመደ ኮምፕዩተሩን ያጠመደዉ ግለሰብ የፈለገዉን መረጃዎችን ማግኘት ይችላል። የኢሜል፤ የስካይፕ ግንኙነቶችን ና አድራሻዎችን ማግኘት ይችላል፤ ባለቤቱ ሳያዉቅ የዌብ ካሜራዉን ሊከፍት ይችላል፤ ባጠቃላይ የዚያን ሰዉ ኮምፕዩተርን ሙሉ በሙሉ ይቆጣጠረዋል።» ይላሉ። ከዚህ ቀደም በጎርጎሪዮሳዊዉ የዘመን ቀመር 2013 ዓ,ም ላይ ሂዉማን ራይትስ ዎችና ሌሎች ለጋዜጠኞች መብት የሚሟገቱ ድርጅቶች የኢትዮጵያ መንግሥት በዉጭ ሃገር የሚገኙ ጋዜጠኞችን ኮምፕዩተሮች ለማጥመድ የስለላ ፕሮግራም እንደሚጠቀም አመልክተዉ ነበር። ድርጊቱ አሁንም መቀጠሉ ፊሊክስ ሆርን እንደሚሉት እንዲህ ያለዉን የኮምፕዩተር የስለ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ረቂቅ አዋጅ ከሕገ መንግሥቱ ጋር እንዲታረቅ የፓርላማ አባላት ጠየቁ

Image
መጋቢት 1 ቀን 2007 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ረቂቅ አዋጅ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ቢኖረውም፣ ከሕገ መንግሥቱ ድንጋጌዎች ጋር የሚቃረኑ አንቀጾችን የያዘ በመሆኑ እንዲስተካከል የፓርላማ አባላት ጠየቁ፡፡ የቀረበው ረቂቅ አዋጅ አገሪቱ የቀረፀቻቸውን ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች መሠረት በማድረግ ከ40 እስከ 50 ዓመታት ባሉት ጊዜያት ውስጥ በኢንዱስትሪ የዳበረችና ዜጎቿም ከፍተኛ ገቢ ያላቸው እንዲሆኑ እንዲሁም፣ እስከ 2017 ዓ.ም. ባለው የስትራቴጂው ምዕራፍ አገሪቱ ከድህነት ተላቃ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ጎራ መቀላቀል እንድትችል ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡ ረቂቅ አዋጁ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች እንዲከናወን የሚፈቅድ ነው፡፡ የኢንዱስትሪ ፓርኮች በመሬት አጠቃቀም ላይ የሚታየውን የኪራይ ሰብሳቢነት አደጋ ለማስቀረት፣ የሎጂስቲክስና የጉምሩክ አገልግሎት ችግሮችን ለማስወገድ፣ መሠረት ልማቶችን በማሟላት የአገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ያለብዙ ውጣ ውረድ እንዲሳተፉና በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ምርትና ኤክስፖርት ተግባር እንዲሸጋገሩ የሚያስችል መሆኑን የአዋጁ መግቢያ ይገልጻል፡፡ የረቂቅ አዋጁ ክፍል አንድ አንቀጽ ሁለት ንፁስ አንቀጽ ሦስት ለመሬት የሚሰጠው ትርጓሜ አግባብነት ላይ የፓርላማ አባላት ጥያቄያቸውን አንስተዋል፡፡ ‹‹መሬት ማለት ለኢንዱስትሪ ፓርክ ልማት ዓላማ የተሰየመ ማንኛውም መሬት ነው፤›› ይላል፡፡ የምክር ቤቱ የመከላከያና የውጭ ደኅንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሜቲ ሰብሳቢ አቶ ተሰፋዬ ዳባ በረቂቁ ላይ የተቀመጠው ድንጋጌ፣ ሕገ መንግሥቱ ለክልሎች የሰጠውን መሬት የማስተዳዳር መብት ጋር የሚጣረስ መሆኑን በመጠቆም ማስተካከል እንደሚገ

ኢሕአዴግ የምርጫ ሥነ ምግባር ማውጣት ብቻ ሳይሆን አርዓያ ሆኖ ይገኝ

በሽባባው በላይ በብዙ አገሮች በሥልጣን ላይ ያሉ ፓርቲዎች የሕዝቡን ይሁንታ አግኝተው በተጨማሪ ጊዜ አገር መምራትን ይመኛሉ፡፡ በተለይ ሕጉ ከፈቀደላቸው በአንዳንድ አገሮች የመንግሥትንም ሆነ የፓርቲን ጉልበት እየተጠቀሙ ወደ ውድድር መግባታቸው ይታያል፡፡ የሠለጠኑትና ያደጉት አገሮች ፓርቲዎች (ዕጩ ፕሬዚዳንቶች) ግን የተቀመጡበት ኮርቻው የመንግሥት ቢሆንም ከክሱ ላይ ወርደው ለመወዳደር ይጥራሉ፡፡  ኢሕአዴግ በአገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ለ25 ዓመታት ገደማ በመሪነት መቀመጡ ብቻ ሳይሆን፣ ‹‹ተጨማሪ 40 ዓመታት ካገኘሁ የአገሪቱን ህዳሴ አረጋግጣለሁ!›› ብሎ መናገር ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ ስለሆነም በሥልጣን ላይ ለመቆየት ብቻ ሳይሆን፣ በሕዝብ ይሁንታ በሥልጣን ለመዝለቅ ከፍተኛ ፍላጐት እንዳለው ጥርጥር የለውም፡፡  እንደ አንድ አስተያየት ሰጪ ድርጅቱ 40 ዓመት ልቆይ ማለቱ ብዙ ችግር አይመስለኝም፡፡ ነገር ግን የዴሞክራሲ መርሆዎች እየተሸራረፉ፣ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት እየተዳከመ፣ በዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ስም የጥቂቶች ፈላጭ ቆራጭነት እያቆጠቆጠ፣ ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል ሳይረጋገጥ፣ ልማትን ሽፋን በማድረግ የሕግ የበላይነትን በመዘንጋትና መልካም አስተዳደርን ባለማረጋገጥ ወዘተ፣ ለመጓዝ ካሰበ በየትኛውም መንገድ ቢሆን ያሰበውን ሊያሳካ አይችልም፡፡  የኢትዮጵያ ሕዝብ ኢሕአዴግን የሚያመሰግንበት በጐ ተግባሮችና አገራዊ መሻሻሎች የመኖራቸውን ያህል የሚያማርርበትና የሚወቅስበት በርካታ ችግሮች አሉ፡፡ ለአብነት ብናነሳ አንዱ የ‹‹ኢትዮጵያዊነት ስሜት መድከም›› ነው፡፡ ስለአገር ክብር፣ ሉዓላዊነት፣ የነፃነት አኩሪ ታሪክ፣ የሦስት ሺሕ ዘመን ቅርስ፣ የማይናወጥ አንድነት፣ ወዘተ ከሚያነሱ ሰዎች ይልቅ የብሔርና የመንደር ባንዲራን የሚያውለበልቡ ይደመጣሉ፡፡

የመድረክ የርእዮተ አለም አሰላለፉ እና የምርጫ ዝግጅቱ ሲቃኝ

Image
የምስረታ ጊዜው 2001 ዓመተ ምህረት የሆነው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንደነት መድረክ/መድረክ በምርጫ 2002 ተሳትፏል። የፓርቲው የወቅቱ ሊቀመነበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ስለፓርቲው አመሰራረትና ስሪት ሲገልፁ፥ መድረክ የአራት ፓርቲዎች ጥምረት በአደረጃጀቱም ግንባር መሆኑ ያነሳሉ። የኢትዮጵያ ማህበራዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ/ደቡብ ህብረት አንድነት ፓርቲ፣ የኦሮሞ ፌድራል ኮንገረንስ፣ አረና ትግራይ እና የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ናቸው አባላቱ። የኢትዮጵያ ማህበራዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ እና የኦሮሞ ፌድራል ኮንገረንስ ሀገር አቀፍ ፓርቲ ሲሆኑ፥ አረና ትግራይ እና የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ክልላዊ ፓርቲዎች ናቸው። መድረክ በጠቅላላ ጉባኤ በየአመቱ የሊቀመንበር ምርጫ ያካሂዳል፤ አንድ አባል ጠቅላላ ጉባኤው እስከ መረጠው ድረስ በተከታታይ ሁለት ጊዜ በሊቀ መንበርነት መምራት ይችላል። ከሁለት ጊዜ በላይ ግን መመረጥም፤ መምራትም አይቻልም። የሚከተለው ርእዮተ አለም ፓርቲው የተለያየ ርእዮተ አለም ያላቸው አራት ፓርቲዎች ስብስብ ነው። ስለዚህ የሚከተለው ርእዮተ አለም ምንነት ላይ ጥያቄ የሚያነሱ አሉ። ሊቀመንበሩ ፕሮፈሰር በየነ መድረክን ያስገኙት አባል ፓርቲዎች የየራሳቸው ርእዮተ አለም እንዳላቸው ነው የሚጠቅሱት። አራቱን ፓርቲዎች በአንድ ጥላ ስር መድረክ ብሎ ያሰባሰባቸው የሚከተሉት ርእዮተ ዓለም ሳይሆን ያላቸው መለስተኛ የፖለቲካ ፕሮግራም ነው ይላሉ ሊቀመንበሩ። መድረክ የተለያየ የፖለቲካ መስመርን ይዞ አንድ ፓርቲ መሆን ይቻላል ባይ ነው፤ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ፖለቲካ የርእዮተ አለም ሹክቻ ውስጥ የመግቢያ ደረጃ ላይ ያልደረሰ በመሆኑ የሚል መከራከራም አላቸው። በዚህ የተለያዩ ርእዮተ አለሞችን ይዞ በተመሳሳይ መለስተኛ የፖለቲካ ፕ

Agricultural Information System: The Case of Hawassa Area, Southern Ethiopia

Image
In this research, a combination of literature study, surveys, as well as annual research review participation were implemented. The results of the study showed that different factors are constraining the system in the area. Low capacity of farmers, lack of motivation of stakeholders, lack of motivation and knowledge of development agents, poor linkage among actors, negligence of farmers' indigenous knowledge, and low interest/resistance of farmers to newly emerging technologies were among the main bottlenecks in their respective orders. Based on the finding of this study, it is concluded that practicing participatory research approach, capacity building, training, and mobilization of farmers towards agricultural information & knowledge transfer system, equipping development agent workers with knowledge, motivating them and monitoring their performance, giving air time in the government Medias to broadcast agricultural information, considering and incorporating farmers indigeno