በሐዋሳ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ ለግምት የሚያዳግት ንብረት መውደሙ ተጠቆመ
‹‹ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል›› የታቦር ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ‹‹አንድ ሕፃን ልጅ ብቻ ሕይወቱ አልፏል›› የሐዋሳ ከተማ ፖሊስ ምክንያቱ በውል ያልታወቀው የካቲት 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ከምሽቱ 1፡30 ሰዓት ላይ በሐዋሳ ከተማ ታቦር ክፍለ ከተማ ታራ ቀበሌ አዲስ ከተማ ተብሎ በሚጠራው ሥፍራ የተነሳው ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ፣ ለግምት የሚያዳግት ንብረት መውደሙን ተጎጂዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ የወደመው የንብረት ግምት በውል ባይታወቅም፣ ከ800 በላይ ሱቆች በመቃጠላቸው በርካታ ንብረት መውደሙን ግን የክልሉ ፖሊስ አረጋግጧል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎችና ጉዳት የደረሰባቸው ባለሱቆች እንደገለጹት፣ ገበያው ከተመሠረተ ሦስት ዓመታት ሆኖታል፡፡ ቀኑ ሞቅ ያለ ገበያ የሚካሄድበት ከመሆኑ አንፃር፣ ከሌሎቹ ቀናት በተለየ ሁኔታ እያንዳንዱ ሱቅ በሸቀጣ ሸቀጦች ተሞልቷል፡፡ ነጋዴዎች ሙሉ ቀን ሲገበያዩ ውለው ሒሳባቸውን የሚሠሩት በነጋታው በዕለተ እሑድ በመሆኑ፣ አብዛኞዎቹ ከሽያጭ የሰበሰቡትን ገንዘብ እንኳን ይዘው አለመሄዳቸውን ተጎጂዎቹ ገልጸዋል፡፡ አደጋው የደረሰበት ሰዓት አብዛኛዎቹ ነጋዴዎች ሱቆቻቸውን ቆልፈው ወደ ቤታቸው የሚገቡበት በመሆኑና እሳቱ በፍጥነት ሱቆቹን በማዳረሱ፣ የተወሰነ ንብረት እንኳን ማዳን አለመቻሉን ገልጸዋል፡፡ ሐዋሳ ከተማ በተለይ የቱሪስቶችና የተለያዩ የአገሪቱ ዜጎች መዝናኛ ከተማ ከመሆኗ አንፃር፣ ድንገተኛ አደጋን ለመከላከል ልዩ ጥንቃቄ የሚያስፈልግ ቢሆንም፣ በቂ የሆነ የእሳት አደጋ መቆጣጠሪያ ባለመኖሩ ገበያው ሙሉ ለሙሉ ሊወድም መቻሉን ተናግረዋል፡፡ በርካታ ሚሊዮን ብሮች የሚገመት ንብረት መውደሙን የሚናገሩት ተጎጂዎቹ፣ የነበራቸውን ሀብት በሰዓታት ልዩነት ማጣ