Posts

ሁለቱ የሲዳማ የሴቶች እግር ኳስ ክለቦች 7 ተጫዋቶችን ለሉሲ ኣስመረጡ

Image
በአሰልጣኝ በኃይሏ ዘለቀ  የሚመራው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን መጋቢት 23 ቀን 2007 ለመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ማጣርያ ከካሜሩን አቻው ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ 40 ተጫዋቾችን የመረጠ ሲሆን የሲዳማ ክለቦች የሆኑት ሲዳማ ቡና እና ሐዋሳ ከነማ በድምሩ ሰባት ተጨዋቾችን ኣስመርጠዋል፡፡ በተለይ ሲዳማ ቡና የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ሊያ ሽብሩን በግብ ጠባቂነት፤ ፋስካ በቀለን በተከላካይነት፤ የካቲት መንግስቱን በኣማካይነት፤ መሳይ ተመስገን እና ወርቅነሽ መልሜሎን በኣጥቂነት በድምሩ ኣምስት ተጫዋቶችን ለብሔራዊ ቡድኑ በማስመረጥ ስድስት ተጫዋቾችን ካስመረጠው ደደቢት ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ሐዋሳ ከነማ በበኩሉ፧ ኣዲስ በፍቃዱን እና ምህረት መለሰን በኣማካይ እና በተከላካይ ቦታ ኣስመርጧል።   ሉሲዎቹ ዝግጅታቸውን ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የሚጀምሩ ሲሆን የኢትዮጰያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግም ለአንድ ወር ያህል ይቋረጣል ተብሏል፡፡ ለሉሲዎቹ የተመረጡት 40 ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው፡- ተ.ቁ ስም ክለብ ግብ ጠባቂዎች 1 ዳግማዊት መኮንን የኢት. ንግድ ባንክ 2 ማርታ በቀለ ዳሽን ቢራ 3 ትእግስት አበራ ወላይታ ድቻ 4 ታሪኳ በርገና ድሬዳዋ ከነማ 5 ሊያ ሽብሩ ሲዳማ ቡና ተከላካዮች 6 ሳምራዊት ኃይሉ መከላከያ 7 መስከረም ኮንካ ደደቢት 8 ጥሩአንቺ መንገሻ የኢት.ንግድ ባንክ 9 ፅየን እስጢፋኖስ ቅዱስ ጊዮርጊስ 10 ፋሲካ በቀለ ሲዳማ ቡና 11 አረጋሽ ፀጋ አርባምንጭ ከነማ 12 እፀገነት ብዙነህ የኢት. ንግድ ባንክ 13 ውባለም ፀጋዬ ደደቢት 14 ፋጡማ አሊ ደደቢት 154 መልካም ተፈራ ቅዱስ ጊዮርጊስ 16 ምህረት መለሰ ሀዋሳ ከነማ 17 አሳቤ ምኤሶ አዳማ ከነማ 18 ገነት ኃይሌ ድሬዳዋ ከነማ አማካዮች 19

የኢትዮጵያ ካንሰር ማህበር የህክምና ወጪያቸውን መሸፈን ለማይችሉ ሴት የካንሰር ታማሚዎች ድጋፍ የሚሰጥ ፕሮጀክት ጀመረ

Image
 ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ የኢትዮጵያ ካንሰር ማህበር የህክምና ወጪያቸውን መሸፈን ለማይችሉ ሴት የካንሰር ታማሚዎች ድጋፍ የሚሰጥ ፕሮጀክት ጀመረ ። ማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሀብታሙ በለጠ እንዳሉት ለታካሚዎቹ የሚሰጠው አገልግሎት የመኝታ፣ የምግብ፣ የትራንስፖርት፣ የመጸዳጃ እቃዎችና ለህሙማን አስፈላጊ የሆኑ ወጪዎችን የሚሸፍን ነው ።     ማህበሩ ካለፈው ዓመት ጀምሮ ለ132 ህመምተኞች አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱን የተናገሩት ሥራ አስኪያጁ በበሽታው ዙሪያ ለኅብረተሰቡ ግንዛቤ የማስጨበጥ ተግባር አከናውኗል ።      የአለም ጤና ድርጅት የጤና ጥበቃ አማካሪ ዶክተር በዛብህ አስማማው በበኩላቸው ማህበሩ ከተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ለህክምና የሚመጡና ረዳት ሳይኖራቸው ለችግር የተዳረጉ ዜጎችን በማሰባሰብ ድጋፍ ማድረጉ ሊበረታታ ይገባል ብለዋል። በአገሪቱ የሚገኙ የካንሰር ህክምና ባለሙያዎች ሶስት ብቻ በመሆናቸው ካለው የህሙማን ብዛት ጋር የማይመጣጠን ሲሆን ዜጎችን ከሞት ለመታደግ  ባለሙያዎች በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እየሰለጠኑ መሆኑን አስረድተዋል።

የጫት ነገር

Image
ጫት ከምን ጊዜውም የበለጠ በገጠርም ሆነ በከተማ በስፋት ጐልቶ የወጣበት ጊዜ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ በገጠሩ መልክአ ምድር፣ በከተማው ገበያ፣ ማስታወቂያና በመቃሚያ ቤቶች በብዛት ጫት እዚህም እዚያም እንዲታይ ሆኗል፡፡ አነቃቂው ዕፅ ጫት ሚሊዮኖች የሚጠቀሙት፣ አነስተኛ ደረጃ አምራች ገበሬዎች የሚመርጡት፣ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚያስገኝ፣ በጥቅሉ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖው ከባድ የሆነ ምርት ሆኗል፡፡ ከጫት ታክስ ለመሰብሰብ በመፈለግ የድንበር ግጭት የተፈጠረባቸው አካባቢዎች መኖር ደግሞ የጫት ፖለቲካዊ አንድምታም ቀላል ላለመሆኑ ምስክር ነው፡፡   ከአምራች ገበሬዎች ጀምሮ በአዘገጃጀት፣ በትራንስፖርት፣ በሥርጭት፣ በሽያጭ ላይ የተሰማሩ ብዙዎች ከጫት በመጠቀም ላይ ናቸው፡፡ ተጠቃሚነቱ ለውዝ፣ ውኃ፣ ሲጋራ፣ ሻይ ቡና ለሚሸጡ እታች ድረስ ወርዷል፡፡ ለአገር ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ቀዳሚዎቹ ደረጃ ላይ የሚገኘው፣ የብዙዎች የሀብት ምንጭና እንጀራ የሆነው ጫት በተለያየ መልኩ ለማኅበራዊ ቀውስ ምክንያት እየሆነ መሆኑንም በሚመለከት ብዙ ተብሏል ጥናቶችም ተሠርተዋል፡፡ በአፍሪካ፣ አውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካ፣ እስያና አውስትራሊያ መስፋፋቱን ተከትሎ በዓለም አቀፍ ደረጃም የጫት ጥቅምና ጉዳት አወዛጋቢና አከራካሪ ሆኗል፡፡ በጫት ዙሪያ ያለው ክርክር በዓለም አቀፍ ደረጃ አደንዛዥ ዕፅን መዋጋት፣ የሽብርተኝነት ፍርኃትና የምዕራባውያን የኢኮኖሚ ልማት ሞዴል የበላይነትን በመሰሉ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች የተቃኘ መሆኑን የሚያሳይ ጥናት አለ፡፡  ወደ አገራችን የጫት እውነታ ሲመጣ ጫትን በሚመለከት የተለያዩ አመለካከቶች ይንፀባረቃሉ፡፡ የተሠሩ ጥናቶችም ሲታዩ አንዳንዳቹ የጫት ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የጤና ተፅዕኖ ላይ ሲያተኩሩ ሌሎቹ በጫት ኢኮኖሚያዊ

Worancha

Image

Ethiopians deserve a free press

The Feb. 9 editorial “ Ethiopia’s stifled press ” raised fundamental issues of human rights, democracy and governance. The journalists and bloggers languishing in prison committed no crime except to criticize the ruling party.  If the government of Ethiopia is concerned for its citizens, as a spokesman asserted in a Feb. 13  letter  [“The Ethio­pian government’s duty is to protect all of its citizens”], it should respect the rights and views of journalists and civilians who oppose its policies. It is repressive to block popular Web sites and broadcasts, such as Voice of America, that provide an alternative to government-controlled media. Ethiopians should have the right to voice their concerns about their country’s affairs. Private, independent media outlets facilitate the venue for an open discourse. The government’s persistent attack on press freedom, therefore, will only exacerbate the people’s anguish. No government is perfect. Those who use pens to expose the imperfections s