ሁለቱ የሲዳማ የሴቶች እግር ኳስ ክለቦች 7 ተጫዋቶችን ለሉሲ ኣስመረጡ
በአሰልጣኝ በኃይሏ ዘለቀ የሚመራው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን መጋቢት 23 ቀን 2007 ለመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ማጣርያ ከካሜሩን አቻው ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ 40 ተጫዋቾችን የመረጠ ሲሆን የሲዳማ ክለቦች የሆኑት ሲዳማ ቡና እና ሐዋሳ ከነማ በድምሩ ሰባት ተጨዋቾችን ኣስመርጠዋል፡፡ በተለይ ሲዳማ ቡና የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ሊያ ሽብሩን በግብ ጠባቂነት፤ ፋስካ በቀለን በተከላካይነት፤ የካቲት መንግስቱን በኣማካይነት፤ መሳይ ተመስገን እና ወርቅነሽ መልሜሎን በኣጥቂነት በድምሩ ኣምስት ተጫዋቶችን ለብሔራዊ ቡድኑ በማስመረጥ ስድስት ተጫዋቾችን ካስመረጠው ደደቢት ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ሐዋሳ ከነማ በበኩሉ፧ ኣዲስ በፍቃዱን እና ምህረት መለሰን በኣማካይ እና በተከላካይ ቦታ ኣስመርጧል። ሉሲዎቹ ዝግጅታቸውን ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የሚጀምሩ ሲሆን የኢትዮጰያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግም ለአንድ ወር ያህል ይቋረጣል ተብሏል፡፡ ለሉሲዎቹ የተመረጡት 40 ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው፡- ተ.ቁ ስም ክለብ ግብ ጠባቂዎች 1 ዳግማዊት መኮንን የኢት. ንግድ ባንክ 2 ማርታ በቀለ ዳሽን ቢራ 3 ትእግስት አበራ ወላይታ ድቻ 4 ታሪኳ በርገና ድሬዳዋ ከነማ 5 ሊያ ሽብሩ ሲዳማ ቡና ተከላካዮች 6 ሳምራዊት ኃይሉ መከላከያ 7 መስከረም ኮንካ ደደቢት 8 ጥሩአንቺ መንገሻ የኢት.ንግድ ባንክ 9 ፅየን እስጢፋኖስ ቅዱስ ጊዮርጊስ 10 ፋሲካ በቀለ ሲዳማ ቡና 11 አረጋሽ ፀጋ አርባምንጭ ከነማ 12 እፀገነት ብዙነህ የኢት. ንግድ ባንክ 13 ውባለም ፀጋዬ ደደቢት 14 ፋጡማ አሊ ደደቢት 154 መልካም ተፈራ ቅዱስ ጊዮርጊስ 16 ምህረት መለሰ ሀዋሳ ከነማ 17 አሳቤ ምኤሶ አዳማ ከነማ 18 ገነት ኃይሌ ድሬዳዋ ከነማ አማካዮች 19