Posts

Ethiopia: SMEs facing sever credit constraints-W/Bank

Image
Small and Medium Enterprises (SMEs) in Ethiopia have faced severe credit service constraints owing to absence of financial institutions catering them, the World Bank said on Thursday.A study by the bank released on Thursday has revealed that young and smaller firms across the country are much more likely to be rejected from line of credit and discouraged from applying for loans due to high collateral requirements. “Almost 70 percent of SMEs are either fully or partially credit constrained, meaning they don’t have access to external forms of finance,â€� said Francesco Strobbe, World Bank’ Senior Economist at the launching session of the Study in Addis Ababa. “Small and Medium enterprises are being underserved compared to micro and large firms as Micro Finance Institutions primarily cater micro firms and larger banks are discouraged to serve SMEs primarily due to perceptions of lower returns and higher risk,â€� Strobe added. The government of Ethiopia has managed to create

የሳምንቱ ምርጥ ፎቶ

Image
Hawassi gaaribba/የሃዋሳ ሐይቅ ሲዳማ ምንጭ፦ https://www.pinterest.com/pin/195343702557502904/

በሁለተኛው መላው የደቡብ ክልል የትምህርት ቤቶች የስፖርት ውድድር የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ሲዳማ ዞንን ሁለት ለባዶ አሸነፈ

Image
ሁለተኛው መላው የደቡብ ክልል የትምህርት ቤቶች የስፖርት ውድድር ተጀምሯል። ለ15 ቀናት በሚቆየው በዚሁ ውድድር ከ14 ዞኖች፣ 4 ልዩ ወረዳዎችና ሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ስር ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተወጣጡ አንድ ሺህ 780 ተማሪዎች በመሳተፍ ላይ ሲሆኑ ከመካከላቸውም 783 ሴቶች ናቸው፡፡ ተሳታፊዎቹ በቆይታቸው በእግር ኳስ፣ በአትሌቲክስ፣ በመረብ ኳስና ጠረጴዛ ቴንስን ጨምሮ በ13 የስፖርት አይነቶች ውድድር ያካሂዳሉ፡፡ ውድድሩ በሃዋሳ ሜዳ፣ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ፣ ግብርና ኮሌጅና  ሌሎች ማዘውተሪያ ቦታዎች ላይ የሚደረግ ይሆናል። በውድድሩ የተሻሉና ጥሩ ተፎካካሪ የሆኑ ተማሪዎችን በመመልመል በመጋቢት ወር በባህርዳር ከተማ በሚደረገው ሀገር ዓቀፍ የተማሪዎች ስፖርት ውደድር ላይ  ክልሉን ወክለው እንዲሳተፉ ይደረጋል ብለዋል። በሃዋሳ ስታዲየም በተጀመረው የመክፈቻ ስነስርአት ላይ የተለያዩ አዝናኝ የጅምናስቲክ ትርኢቶች የቀረቡ ሲሆን በወንዶች በተደረገ የእግር ኳስ ግጥሚያ የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ሲዳማ ዞንን ሁለት ለባዶ አሸንፏል፡፡ - See more at: http://www.ena.gov.et/index.php/politics/item/2079-2015-02-18-16-27-42#sthash.zZWTEekO.dpuf

ስለ ሲዳማ ባህላዊ ቤት ምን ይወራል?

Image
Una casa circular de bambú construida por el pueblo Sidama de Etiopía. Esta es una casa circular tradicional de bambú cortado y trenzado realizada por el pueblo Sidama de Etiopía. La cúpula, con su parte superior puntiaguda, está diseñada para repeler fuertes lluvias mientras que en una cúpula circular ese espacio tendría un área plana, propensa a las goteras. El bambú jugó un papel importante en las economías rurales del Este de África, pero la tala indiscriminada de los bosques naturales de bambú ha propiciado la pérdida de recursos naturales y de muchas de las técnicas tradicionales de construcción. Puedes encontrar más información sobre la  construcción tradicional con bambú  en la  Red Internacional del Bambú y el Ratán . ምንጭ፦ naturalhomes.org

ዩኒቨርስቲው የፖለቲካ ፓርቲዎች የርዕዮት ዓለም ክርክር የሚያካሂዱበት መድረክ ሊያዘጋጅ ነው

Image
የፖለቲካ ፓርቲዎች በርዕዮት ዓለማቸው ዙሪያ ክርክር የሚያካሂዱበትን መድረክ እንደሚያዘጋጅ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አስታወቀ። የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ቤት ከዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር የካቲት 21 የሚያካሂደው ክርክር ህጋዊ እውቅና ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች አማራጫቸውንና የርዕዮት ዓለም ፍልስፍናቸውን በነፃነት የሚያንሸራሽሩበት ይሆናል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ቤት ኃላፊ ዶክተር አብዲሳ ዘርዓይ ለኢዜአ እንደተናገሩት በአገሪቱ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች የርዕዮት ዓለም ፍልስፍና ከሦስት ማዕቀፎች አያልፍም። በዚህም መሰረት የልማታዊ ዴሞክራሲ፣ የሶሻል ዴሞክራሲና የሊበራል ዴሞክራሲ የርዕዮት ዓለምን እናራምዳለን የሚሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወክለው ክርክራቸውን ያደርጋሉ። ዶክተር አብዲሳ እንዳሉት ሦስቱን የርዕዮት ዓለም ፍልስፍናዎች ወክለው በክርክሩ ለሚቀርቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ለእያንዳንዳቸው የ30 ደቂቃ የመከራከሪያ ጊዜ ይሰጣቸዋል። በአገሪቱ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህጋዊ እውቅና አግኝተው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች በክርክር መድረኩ ላይ ይታደማሉ። በሦስቱ የርዕዮት ዓለም ፍልስፍናዎች ዙሪያ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሃሳብ ወክለው የሚያደርጉት አዎንታዊ የመድረክ ላይ ክርክርም የአገሪቱን የዴሞክራሲ ስርዓት በማጎልበት ረገድ የላቀ ሚና ይኖረዋል ብለዋል። በአሁኑ ወቅት ዩኒቨርሲቲው በክርክር መድረኩ ለሚሳተፉ የፖለቲካ  ፓርቲዎች የጥሪ ደብዳቤ ለማሰራጨትና ሌሎች ቅድመ ዝግጅቶችን እያከናወነ ነው። በመርሃ ግብሩ ላይ ከ100 እስከ 150 ተሳታፊዎች ይገኛሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በርካታ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችም ክርክሩን ለመዘገብ ተጋባዥ ይሆናሉ።