በጃፓኑ ፈጣን ባቡር ከአሥር ሺሕ በላይ ተጓዦች የኢትዮጵያን የጫካ ቡና ይጠጣሉ
ከይርጋጨፌ፣ ከሐረርና ከሲዳማ ቡናዎች በመቀጠል በዓለም የተመዘገ የኢትዮጵያ የጫካ ቡና የመሆን ዕድል እንዳለው ይነገርለታል፡፡ ይህ የተፈጥሮ የጫካ ቡና በአሁኑ ወቅት ተፈጊነቱ እየጨመረ ሲሆን በተለይ በጃፓን ቡና ጠጭዎች ዘንድ ከምንጊዜው በላይ እየተወደደ መምጣቱን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በጅማ ዞን አስተዳደር ውስጥ ከሚገኙ አካባቢዎች ውስጥ በተለይ በለጠና ጌራ የተባሉት በቻካ ቡና ሀብታቸው ይታወቃሉ፡፡ የሰው ንክኪ የሌለው የጫካ ቡና እየለቀሙ የሚተዳደሩ በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ቡናቸው በጃፓን ገበያ ተፈላጊነቱ እንዲጨምር ካቻሉት መካከል ሬንፎረስት አሊያንስ የተባለው አሜሪካ ኩባንያ የጫካውን ቡና ተፈጥሯዊ ይዞታ እያረጋገጠ የምሥክር ወረቀት መስጠት መጀመሩን ተከትሎ ነበር፡፡ ከሰባት ዓመታት በፊት የተጀመረው ማረጋገጫ የመስጠት ተግባር ከወደጃፓን ስመ ወፍራም የሆኑ ኩባንያዎችን ለመሳብ አብቅቷል፡፡ የበለጠ-ጌራ የጫካ ቡናን በመግዛት ላይ የሚገኘው ዩሺማ ኮፊ ኮርፖሬሽን (ዩሲሲ) ሲሆን፣ ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ቡናውን እንዲገዛ መንገዱን ያመቻቸው፣ የጃፓን ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ (ጃይካ) ነው፡፡ በጃይካ በኩል የተመሠረተው የዩሲሲና የበለጠ-ጌራ ቡና አምራቾች ግንኙነት እየዳበረ መጥቶ በአሁኑ ወቅት ቡናቸው የልዩ ጣዕም ቡናነቱ ተመስክሮለት፣ በጃፓኑ ፈጣን ባቡር ለሚሳፈሩ ተጓዦች እየተሸጠ ይገኛል፡፡ በዓለም ላይ ፈጣን ከሚባሉት አንዱ የሆነውና ‹‹ቡሌት ትሬን›› የሚባል መጠሪያን ያተረፈው የባቡር ትራንስፖርት ላይ በየቀኑ ከአሥር ሺሕ በላይ የቡና ስኒዎች እየተሸጡ ሲሆን፣ ዩሲሲ ከዚህ በፊት በዚህ መጠን ለተሳፋሪዎች ቡና ሸጦ እንደማያውቅ፣ የኩባንያው አማካሪ የሆኑትና በቅርቡ ጅማን ጎብኝተው የተመለሱት ናዖሚ ናካሒራም ሆኑ በጃይካ የግብርና