የሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ግለሰቦችን ያለፍቃዳቸው ከቤት ንብረታቸው ባያፈናቅላቸው ምን ይለዋል?
ገዥው ፓርቲ በሚከተለው የከተሞች ልማት ፖሊስ የተነሳ በኢትዮጵያ በርካታ የከተማ ኣስተዳደሮች በየከተሞች ዙሪያ የምገኙትን ገጠራማ ቀበሌዎችን በመዋጥ ላይ ናቸው። በቅርቡ የኣዲስ ኣበባ ከተማ ኣስተዳደር በኣከባቢው የሚገኙትን ገጠራማ ትናንሽ የኦሮሚያ ከተሞችን በልማት ስም ከስሩ ኣስገብቷል። በርግጥ ትናንሽ ገጠራማ ከተሞችና ቀበሌዎች በትላልቅ ከተሞች ስዋጡ ይህ ለመጀመሪያ ግዜ ኣይደለም። እንዳውም የኣዲስ ኣበባ ከተማ ኣስተዳደር ከእኛዋ ከሃዋሳ ከተማ ልምድ የወሰደ ነው የሚመስለው። ከኣመታት በፊት የሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር በዙሪያው በሲዳማ ዞን ስር ይተዳደሩ የነበሩትን 14 ቀበሌያት በቱላ ክፍለ ከተማ ስር ማጠቃለሉ ይታወሳል። በጊዜው የደኢህዴን ካድሬዎች ቀበሌያቱ ከሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ሰር ከተጠቃለሉ ብዙ ጥቅሞች እንደሚያገኙ በመስበክ የየቀበሌያቱን ነዋሪዎች መቆሚያ እና መቀመጫ በማሳጣት እንዲጠቃለሉ እንዳደረጉ ይታወቃል። በርግጥ በርካታ ሰዎች በጉዳዩ ላይ ደሰተኛ ባይሆኑም ለልማት እና ለለውጥ ጉጉ ስለነበሩ ደጋፋቸውን ከመስጠት ኣልተቆጠቡም። እንዳውም የቀበሌያቱን ከሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ስር መሆንን ኣስመልክተው ከብት ኣርደው ደግሰዋል። የሆነ ሆኖ፤ በኣሁኑ ጊዜ የቀበሌያቱ ነዋሪዎች በካድሬዎቹ የተገባላቸው የልማት ስራ ኣለመሰራቱን ይናገራሉ። በርግጥ ኣንዳንድ የልማት ስራዎች እየተሰሩ ያሉ ቢሆኑም እየተሰሩ ያሉት የልማት ስራዎች በሌሎች ክፍለ ከተሞች እየተሰሩ ካሉት ጋር የሚወዳደሩ ኣይደሉም ይላሉ። እንዳውም፤ የቀበሌዎቹ ከከተማ ኣስተዳደር ስር መሆናቸውን ተከትሎ በተለይ ከመሬት ይዞታ ጋር በተያያዘ በርካታ ችግሮች ኣጋጥሞቸዋል። በየቀበሌያቱ ያለው መሬት ተጠንቶ ፕላን እስኪሰራ ድረስ ቤት መገንባት በመከልከሉ የየቀበሌያቱ ነዋሪ