ከምግብ በኋላ ልናደርጋቸው የማይገቡ ሰባት ነገሮች!
ምግብ ከወሰዳችሁ በኋላ ወዲያው ልታደርጓቸው ስለማይገቡ ነገሮች ዛሬ ልንነግራችሁ ወደናል። ከዚህ በታች የተጠቀሱት ነጥቦች ምግብ ከወሰድን በኋላ ብናደርጋቸው ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው ስለሚያመዝን መጠንቀቅ ይበጃል ሲል ዘክሬዚ ፋክትስ የተባለ ድረ ገፅ ያወጣውን ፅሁፍ ነው ልናጋራችሁ የወደድነው። አንዳንዶቹ እንደ ሲጋራ ማጨስ ያሉት ደግሞ ፈፅሞም ባይደረጉ ነው የሚመከረው። 1. ሲጋራ ማጨስ ሲጋራ ማጨስ ምን ያህል ለጤና አደገኛ መሆኑ ቢታወቅም ከምግብ በኋላ ሲሆን ደግሞ እጅግ አደገኛ እንደሚሆን ጥናቶች ይጠቁማሉ። ቢቻል ቀንም፣ ማታም፣ በስራ ስዓትም ሆነ በእረፍት ጊዜ ሲጋራን ከማጨስ መቆጠብ ለራስ ጤና ዋስትና መግባት ነውና ቢታቀቡ ሲጋራ አጫሽ ከሆኑ ግን ከምግብ በኋላ ባያደርጉት ይላል ዘገባው። 2. ፍራፍሬዎችን መመገብ በየእለቱ ከምንወስዳቸው ምግቦች ውስጥ ፍራፍሬዎችን ማካተት ቢመከርም ከምግብ በኋላ እንደ ሙዝ አይነት ፍራፍሬዎችን መውሰድ የምግብ ዝውውር እንዲስተጓጎል ያደርጋል። ፍራፍሬዎች በፍጥነት የመዋሃድ ባህሪ ስላላቸውም ከምግብ ነክ ነገሮች ጋር በመጣበቅ ምግብን የማበላሸት እድል አላቸው። 3. ሻይ ወይም ቡና ከምግብ በኋላ ቡና ወይም ሻይ መጠጣት ምንም እንኳን የማነቃቃትና ከድብርት ለመውጣት ቢያስችልም በተለይ ሻይ ከምግብ በኋላ መውሰድ ምግብ በፍጥነት እንዲቃጠል ያደርጋል። ስለሆነም ከምግብ በኋላ ቢያንስ ከአንድ ስአት በኋላ ነው ሻይ መጠጣት የሚመከረው። 4. ሻወር የምግብ ውህደት የተስተካከለ እንዲሆን በቂ ጉልበትና የደም ዝውውር ወሳኝ ናቸው። በሞቀ ውሃ ሻወር በምንወስድበት ስዓት ወደ ቆዳችን የሚሰራጨው ደም ሙቀት ያዘለ ስለሚሆን፥ ለምግብ ፍጭት አስቸጋሪ ይሆናል። ስለሆነም ሻወር ለመውሰድ ከምግብ በኋላ