Posts

"Sidamo means kiss in the native language of our children, who were born in the Ethiopian region of Sidama"

Image
WEDNESDAY, 28 JANUARY 2015 Sport quote us.   Not a basketball court or a football field or in a pool. The meeting point to start this route is  the "Olympic stadium bowls"  as defined ironically the host of DIY  you already do, Catalonia Television and neighbor Guinardó. When Rafael Vives (Cala Bona, Son Servera, Mallorca, 1966) came to the neighborhood where he has lived for almost fifteen years, next Guinardó Recovering But as municipal facilities and equipped with two bars with terrace, which is the Petanque also  "had a basketball court,"  he recalls.   But when the urban renewal of the area's ancestral house of Horta-Guinardó,  "I guess they had retired to devote his time to claim a space for practice petanque, and that is why it has filled all this land for petanquers esplanade "exposes  the neighbor who comes to your appointment accompanied by a  dog." It's a rabbit dog Andalusian we found abandoned Vila Round (Alt Camp), th

በመጪው እሁድ ሃዋሳ ከነማ ደደቢትን ይገጥማል

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2007 ግማሽ የውድድር ዓመት እሑድ ጥር 24 ቀን 2007 ዓ.ም. ሐዋሳ ላይ ሐዋሳ ከነማ ከደደቢት፣ በድረ ላይ ወላይታ ድቻ ከቅዱስ ጊዮርጊስና በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ኢትዮጵያ ቡና ከመብራት ኃይል ጋር የሚቀሩት ተስካካይ ጨዋታዎች ተደርገው ይጠናቀቃል፡፡ የፕሪሚየር ሊጉ ሁለተኛው ዙር ጨዋታ በመጋቢት ወር መጀመርያ በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚቀጥልም የፌዴሬሽኑ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ወንድምኩን አላዩ ገልጸዋል፡፡  እስካሁን ባለው ፕሪሚየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ሲዳማ ቡና በ27 ነጥብ ሲመራ ቅዱስ ጊዮርጊስ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀየረው በ24 ነጥብ ይከተላል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ እሑድ ወላይታ ድቻን የሚያሸንፍ ከሆነ ግን ሲዳማ ቡና በጎል ክፍያ ስለሚበለጥ መሪነቱን ያስረክባል፡፡  በተመሳሳይ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ የሚቀረው ኢትዮጵያ ቡና ወላይታ ድቻን በጎል ክፍያ በልጦ ሦስተኛና አራተኛ ሲሆኑ፣ አዳማ ከነማ በ19 አምስተኛ፣ አርባ ምንጭ ከነማ በ19 ነጥብ በጎል ክፍያ ተበልጦ ስድስተኛ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባነክ በ16 ነጥብ ሰባተኛ፣ ዳሸን ቢራና መከላከያ በተመሳሳይ 16 ነጥብ በጎል ክፍያ ተበልጠው ስምንተኛና ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡ ደደቢት በ15 ነጥብ 10ኛ፣ መብራት ኃይል በ14፣ ሙገር ሲሚንቶ በ13፣ ሐዋሳ ከነማ በ10 እና በመጣበት አኳኋን ለመመለስ እያኮበኮበ የሚገኘው ወልዲያ ከነማ በ5 ነጥብ ከ11ኛ እስከ 14ኛ ያለውን ደረጃ ይዘው እንደሚገኙ አቶ ወንድምኩን አስረድተዋል፡፡

የተጨማሪ እሴትና የገቢ ግብር ሕጐች እንዲሻሻሉ ጥያቄ ቀረበ

የተጨማሪ እሴትና የገቢ ግብር ሕጐች ጥናትን መሠረት ያደረገ ማሻሻያ ሳይደረግባቸው ከአሥር ዓመታት በላይ ሥራ ላይ መዋላቸው፣ የታክስ መርህን የሚፃረር መሆኑ በጥናት ተመለከተ፡፡ ፎረም ፎር ሶቫል ስተዲስ (FSS) ጥር 15 ቀን 2007 ዓ.ም. ባዘጋጀው መድረክ ላይ ‹‹የታክስ ሕጐችና ፖሊሲዎች በኢትዮጵያ›› በሚል ርዕስ ጥናታቸውን ያቀረቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፋይናንስና የአካውንቲንግ ትምህርት ክፍል መምህር ዶ/ር ወለላ አቤሆዴ እንዳብራሩት፣ በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ በርካታ ለውጦች የተስተዋሉ ቢሆንም፣ እ.ኤ.አ. በ2002 ሥራ ላይ የዋሉት እነዚህ የግብር ዓይነቶች ይህ ነው የሚባል ለውጥ ሳይደረግባቸው ለአሥራ ሦስት ዓመት መዝለቃቸው ችግር ነው፡፡  ‹‹ታክስ በባህሪው ለውጦች ከሥር ከሥር እየታዩ ሁኔታዎች እንዲጣጣሙ የሚጠይቅ ነው፡፡ ነገር ግን ሕጐቹ ብዙ ለውጥ ሳይደረግባቸው በሥራ ላይ ይገኛሉ፤›› ብለዋል የጥናቱ አቅራቢ፡፡  በእነዚህ የታክስ ሕጐች ላይ ለውጥ ሳይደረግ እስካሁን ሥራ ላይ መዋላቸው የፈጠረውን ተፅዕኖ የሚያመለክተው ጥናቱ፣ የገቢ ግብር ሕግን በመጥቀስ በሕጉ መሠረት የሠራተኛ ደመወዝ የመጀመሪያው 150 ብር ከታክስ ነፃ ቢሆንም በዛሬ ግሽበት የዚህ ገንዘብ መጠን ከግብር ነፃ መሆን ትርጉም የሚሰጥ እንዳልሆነ ያስረዳሉ፡፡ ይህ ከድህነት ወለል አንፃር ቢታይም ትርጉም የሌለው መሆኑን፣ የቢዝነሶች ከግብር ነፃ የሚሆንበት የመጀመሪያው 1,800 ብርም በተመሳሳይ ትርጉም አልባ አሠራር መሆኑን ጥናቱ ይጠቁማል፡፡ በተመሳሳይ የገቢ ግብር የምጣኔ ወሰኖች ቢታዩ፣ ከፍተኛው የገቢ ግብር መጣል የሚጀምርበት 5,000 ብር አቅሙ የተሸረሸረ በመሆኑ የታክስ መጠኑን ማሻሻል የግድ እንደሆነ ጥናት አቅራቢዋ ገልጸዋል፡፡ የድርጅቶች ደረጃ

Ethiopia Sidama Natural

Image
This month we are featuring our natural processed coffee from the Sidama region of Ethiopia. This isn’t one of our newest offerings. It’s certainly not unique to Heine Brothers’.  It’s not even a “seasonal”; we are usually able to stock this coffee year round.  But these facts and the general ubiquity of the name Sidama (aka Sidamo) among specialty coffee roasters make this coffee no less remarkable. In fact, among Heine Brothers’ offerings, Ethiopia Sidama is always atop my list of favorites.  It speaks volumes to the expertise and ingenuity of the farmers (nearly 80,000 of them) organized under the Sidama Coffee Farmers Cooperative Union (SCFCU) that they are so well known in the coffee world, and produce such a unique and interesting cup profile season after season. This natural, or dry processed, coffee is handled with the fruit on for the drying stage of processing.  The whole cherries dry in the sun for weeks until the desiccated skin resembles fruit leather.  Processi

የተጫዋቾች የዝውውር ረቂቅ ሰነድ ለምን አነጋጋሪ ሆነ?

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ሕጋዊ ሰውነት አግኝቶ መንቀሳቀስ ከጀመረ ከስድስት አሠርታት በላይ እንዳስቆጠረ ማስረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ በዚህ ታሪካዊ ጉዞው ፌዴሬሽኑም ሆነ ክለቦች ከመነሻው እንደሌሎቹ አገሮች ወጥ የሆነ አደረጃጀት ኖሯቸው ሊቀጥሉ ባለመቻላቸው ዛሬም በተለያዩ የአሠራር ክፍተቶች እሰጣ ገባ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ)፣ የአገሪቱ ክለቦች በፊፋ የክለብ አደረጃጀትና የተጨዋቾች የዝውውር መርሕ እንዲተዳደሩ የተለያዩ ሥልጠናዎችን ሲሰጥ መቆየቱ እንደማሳያ ሊወሰድ እንደሚገባውም የሚናገሩ አሉ፡፡  የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና ክለቦች በአገሪቱ የሚፈፀመው የእግር ኳስ ተጨዋቾች ደረጃና ዝውውር በሕግና በሥርዓት እንዲመራ በፊፋ ዝቅተኛውን የተጨዋቾች ደረጃና ዝውውር መስፈርት ያሟላ እንዲሆን፣ በተጨማሪም አሠራሩ በሕጋዊ ወኪል እንዲመራና ሒደቱም ተጨዋቾችን፣ ክለቦችንና መንግሥትን ተጠቃሚ በማድረግ ለአገሪቱ የእግር ኳስ ዕድገት መፋጠን የራሱን አወንታዊ ሚና ይጫወታል በሚል የተለያዩ አንቀፆችን የያዘ የተጨዋቾች ደረጃና የዝውውር መመሪያ ረቂቅ ሰነድ ለውይይት አቅርበዋል፡፡ ረቂቅ ሰነዱ ከጥር 25 ቀን 2007 ዓ.ም. በኋላ ሕጋዊ መመሪያ ሆኖ በፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እንደሚፀድቅና እስከዚያ ግን ክለቦች በረቂቅ ሰነዱ በተካተቱ ነጥቦች ውስጥ አለን የሚሉትን ሐሳብ እንዲያንሸራሽሩ ጥር 12 ቀን 2007 ዓ.ም. ፌዴሬሽኑና ክለቦች በካፒታል ሆቴል ባደረጉት የመጀመሪያ የውይይት መድረክ ከስምምነት ደርሰዋል፡፡ ሆኖም ግን መመሪያው ደንብ ሆኖ ሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት ረቂቅ ሰነዱ ለክለቦች ቀደም ብሎ እንዲደርስ ተደርጎ በተለይ የክለብ አስተዳዳሪዎችና ባለቤቶች ጉዳዩን በሰከነና በጥልቀት እንዲመክሩበት መደረግ ነበረበት በሚል አንዳ