ለመሆኑ ኢትዮጵያ በሃይማኖቶች መከባበር ለኣፍሪካ ምሳሌ ናትን?
የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች መከባበር ለአፍሪካ ምሳሌ ነው ተባለ ምንጭ፦ ኢብኮ Ethiopia Destroys Evangelical Church Building; 100 Christians Forced Underground . ምንጭ፦ ቦስኒውላይፍ ሰሞኑን ኢትዮጵያ በሃይማኖቶች መከባበር ለኣፍሪካ ምሳሌ መሆናን በመግለጽ የመንግስት የወሬ ኣውታሮች የዘገቡ ሲሆን፤ በተቃራኒው ደግሞ በኣገሪቷ የሃይማኖቶች የመቻቻል ባህል ኣደጋ ላይ መሆኑን የምገልጹ ወሬዎች ተሰምቷል። በኢትዮጵያ ባለው የሃይማኖቶች መከባበር ዙሪያ የተነገሩትን ሁለት ፊት ወሬዎችን ከታች ያንቡ፦ መቀመጫውን በደቡብ አፍሪካ ያደረገው አክሽን የድጋፍ ማዕከል የተባለ የሠላም ተቋም ባካሄደው የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ላይ ከአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ የሃይማኖት መሪዎች ተካፋይ ሆነዋል፡፡ የማዕከሉ ስራ አስኪያጅ ፒላኒ ዲዴቤሌ እንዳሉት በኢትዮጵያ ያለው የሃይማኖቶች መከባበር ለአፍሪካ ሀገራትም በምሳሌነት ሊማሩበት የሚገባ ነው፡፡ በመሆኑም ጉባኤው በአዲስ አ,በባ እንዲካሄድ መደረጉን ነው የተናገሩት፡፡ ፒላኒ ዲዴቤሌ የአፍሪካ ሀገራት ከሠላምና ጸጥታ ባሻገር በሀገር ልማት ሃይማኖቶች እንዴት አስተዋጽኦ ያደርጉ ለሚለው ጥያቄ መልሱን የምናገኘው ከኢትዮጵያ ነው ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሃፊ ፓስተር ዘሪሁን ደጉ የዕምነት ተቋማትንና 97 በመቶ ህዝብ ያቀፈው ጉባኤው የሚያደርገው የሠላምና የልማት አስተዋጽኦ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡ የሃይማኖት ተቋማት በራሳቸው የሚሰሩት የሠላምና የልማት ተግባርም ለአፍሪካ ሀገራት እንደአህጉር ያለንን የሠላምና ልማት የማረጋገጥ አላማ የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡ በአፍሪካ ህብረት በተካሄደው ጉባኤ የአፍሪካ የህዝብ ለህዝብን መደጋ