ለአካል ጉዳተኛ ህፃናት ድጋፍ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢ የእግር ጉዞ በሃዋሳ ከተማ ተካሄደ
አዲስ አበባ ጥቅምት 10/2007 የአካል ጉዳተኞች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በመቅረፍ እኩል እድል፣ ተጠቃሚነትና ሙሉ ተሳታፊነት እንዲረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የደቡብ ክልል ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ፡፡ “የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ እናድርግ” በሚል መሪ ቃል ለአካል ጉዳተኛ ህፃናት ድጋፍ እንዲውል ቸሻየር ሰርቪስ ኢትዮጵያ ሃዋሳ ቅርንጫፍ ለሰባተኛ ጊዜ ያዘጋጀው የገቢ ማሰባሰብ የእግር ጉዞ ትናንት በሃዋሳ ከተማ ተካሂዷል፡፡ የክልሉ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ አቶ ተሾመ ታደሰ በዚሁ ጊዜ እንደገለፁት አካል ጉዳተኞች በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ሙሉ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚረዱ ፖሊስዎችና ስትራቴጅዎች ወጥተው ተግባራዊ ተደርገዋል፡፡ የአካል ጉዳተኝነት መንስኤዎችንና ከሚያስከትሉት ችግር ጋር ተያይዞ የህብረተሰቡን ግንዛቤ የማሳደግ፣ አካል ጉዳተኛና ቤተሰቦቻቸው ከድህነት የሚላቀቁባቸውን ፕሮግራሞችን የመቀየስ እንዲሁም አድሏዊ አመለካከቶችን የመቀየር ስራዎች ትኩረት መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡ በክልሉ ከ190 ሺህ በላይ አካል ጉዳተኞች እንደሚገኙ ገልፀው ለአካል ጉዳተኞች የሚሰጡ አካላዊ የተሃድሶ አገልግሎቶችን ሊያሳደጉ የሚችሉ ተቋማትን በሰው ሀይል፣ በፋይናንስና በቁሳቁስ የማደራጀት ስራዎችም ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል፡፡ በተለይም በህዝብ መገልገያና መዝናኛ ሥፍራዎች፣ በማህበራዊ መስጫ ተቋማት፣ በህንፃዎች፣ በመንገዶችና በህዝብ መጓጓዣዎች አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ በማድረግ እንዲሰሩ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተጀመሩ ቅንጅታዊ ስራዎችም ተጠናክሮ ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡ ቸሻየር ሰርቪስ ኢትዮጵያ የሃዋሳ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ መሰረት ኪዳኔ በበኩላቸው የእግር ጉዞው ዓላማ