የዲያስፖራ ተቃዋሚዎች በስዊድን የኢትዮጵያ ኤምባሲን ጥሰው ለመግባት ሞከሩ
በዋሺንግተን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መሳሪያ የተኮሰው የፀጥታ ሰራተኛ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ በሳምንቱ መጀመሪያ ዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ በዳያስፖራ ተቃዋሚዎች የተደረገውን ጥሰት ተከትሎ፣ ባለፈው ረቡዕም በስዊድን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ በተቃዋሚዎች ተመሳሳይ የጥሰት ሙከራ መደረጉን ምንጮቻችን ለአዲስ አድማስ ገለፁ፡፡ በስዊድን ስቶክሆልም በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ ባለፈው ረቡዕ የዳያስፖራ ተቃዋሚዎች ተመሳሳይ የጥሰት ድርጊት ለመፈፀምና በስዊድን የኢትዮጵያ አምባሳደር ወይንሸት አሰፋ ላይ ለሁለተኛ ጊዜ ጥቃት ለማድረስ እንደሞከሩ የጠቆሙ ምንጮች፤ የፀጥታ ሃይሎች ደርሰው ሙከራውን እንዳከሸፉት ገልፀዋል፡፡ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲን ቅጥር ግቢ ጥሰው ከገቡ የዳያስፖራ ተቃዋሚዎች ጋር በተፈጠረ አተካሮ መሳሪያ ወደ ላይ የተኮሰው የኤምባሲው የፀጥታ ሰራተኛ ያለመከሰስ መብቱን ተጠቅሞ ወደ ኢትዮጵያ መመለሱን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሬስ ኃላፊ ጄን ሳኪ አስታወቁ፡፡ ባለፈው ሰኞ የተወሰኑ ያለ የዳያስፖራ ተቃዋሚዎች የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ጥሰው መግባታቸውን ተከትሎ በተፈጠረ አምባጓሮ ሰለሞን ገብረስላሴ (በቅፅል ስሙ ወዲ ወይን) የተባለው የኤምባሲው የፀጥታ ሰራተኛ መሳሪያ በመተኮሱ፣ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የግለሰቡ ያለመከሰስ መብት ተነስቶ ጉዳዩ በአሜሪካ ፍርድ ቤት እንዲታይ ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን ጥያቄው በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ተቀባይነት ባለማግኘቱ ወደ አገሩ እንዲመለስ ተደርጓል ተብሏል፡፡ በተመሳሳይ ምክንያት ከአሜሪካ የወጣ ማንኛውም ዲፕሎማት ወደ አሜሪካ መመለስ የሚችለው ክሱ በፍርድ ቤት እንዲታይ ብቻ ነው፡፡ በዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ በዳያስፖራ ተቃዋሚዎች የተፈጸመውን ጥሰ