Posts

Eritrea Blamed for Embassy Disturbance

Image
Photo: allafrica.com The Ethiopian government has pointed a finger at the opposition and Eritrea following a disturbance that took place at the Ethiopian Embassy in Washington DC. Read more at: allAfrica.com

ዋሊያዎቹ ቅዳሜ ማሊን ያስተናግዳሉ

Image
ብዙ ድካምና ጉልበት ብቻ ሳይሆን፣ ከውጤቱ አንፃር ብዙ ገንዘብም እየፈሰሰበት የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሚፈለገውን ነጥብ ማስገኘት ሳይችል ከአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ግርጌ ላይ ይገኛል፡፡ ቡድኑ የምድቡን ሦስተኛ ጨዋታ ቅዳሜ ጥቅምት 1 ቀን 2007 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ስታዲየም የማሊ አቻውን ያስተናግዳል፡፡ የማሊ ቡድን ከነገ በስቲያ ዓርብ አዲስ አበባ ይገባል ተብሎ እንደሚጠበቅም ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡ በሜዳቸው በአልጄሪያ፣ ከሜዳቸው ውጪ ደግሞ በማላዊ ሁለት ሽንፈቶችን ያስተናገዱት የዋሊያዎቹ አሠልጣኝ ፖርቱጋላዊው አሠልጣኝ ማርያኖ ባሬቶ፣ ለቅዳሜው ጨዋታ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስ 27 ተጨዋቾችን ይዘው በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡ የሚቀንሷቸውን ተጨዋቾች አስመልክቶ አሠልጣኙም ሆነ ፌዴሬሽኑ ምንም ያሉት ነገር ባይኖርም፣ ግን ደግሞ የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ ከአምስት ቀን በኋላ ረቡዕ ጥቅምት 5 ቀን ስለሚሆን በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ አሠልጣኙ የመጨረሻዎቹን ተጨዋቾች ለፌዴሬሽኑ እንዲያሳውቁ በፌዴሬሽኑ በኩል ጥያቄ መቅረቡ እንደማይቀር የሚገልጹ አሉ፡፡ አሠልጣኝ ማሪያኖ ቀደም ሲል ከመረጧቸው ተጨዋቾ በተጨማሪ በግብፅ የሚጫወቱት ሽመልስ በቀለና ኡመድ ኡክሪ፣ እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ የሚጫወተው ጌታነህ ከበደ፣ በአውሮፓ ከሚጫወቱት ደግሞ የሱፍ ሳላህ፣ አሚን አስካርና ዋሊድ አታ ዋሊያዎቹን የተቀላቀሉ ሲሆን፣ ከአገር ውስጥ የኢትዮጵያ ቡናው ዴቪድ በሻህና የደደቢቱ ሔኖክ ካሳሁን በተመሳሳይ በአዲስ መልክ ጥሪ ተደርጎላቸዋል፡፡ በሌላ በኩል ሪፖርተር ያነጋገራቸው የፌዴሬሽን ምንጮች አሠልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶና የፌዴሬሽኑ ብሔራዊ ቴክኒክ ኮሚቴ በቡድኑ ውጤት ዙሪያ መግባባት እንዳልቻሉ ይናገራሉ፡፡  አሠልጣኙ በበኩላቸው፣ ከደጋፊው

ኢሕአዴግ ለመድበለ ፓርቲ የፖለቲካ ሥርዓት ቁርጠኛ አይደለም ሲል ኢዴፓ ከሰሰ

ኢዴፓ ሐምሌ 12 ቀን 2006 ዓ.ም. ሊያደርግ የነበረው ስብሰባ የተደናቀፈው በሕጋዊ መንገድ አለመሆኑን ያረጋገጠውን የአጣሪ ኮሚቴ ሪፖርት ያልተቀበለው ብቸኛው የአገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባል ኢሕአዴግ በመሆኑ፣ ለመድበለ ፓርቲ የፖለቲካ ሥርዓት መጠናከር ቁርጠኛ እንዳልሆነ ያረጋግጣል ሲል ከሰሰ፡፡ መስከረም 26 ቀን 2007 ዓ.ም. ለሪፖርተር በላከው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ኢዴፓ እንደገለጸው፣ በመብራት ኃይል አዳራሽ ሕዝባዊ ስብሰባ ለማካሄድ አስቦ ሲንቀሳቀስ በፀጥታ ኃይሎች ከተደናቀፈ በኋላ፣ በጉዳዩ ላይ በወቅቱ ለሕዝቡ በመገናኛ ብዙኃን መረጃ ቢሰጥም ጉዳዩን ለጋራ ምክር ቤቱ አቅርቧል፡፡  የኢዴፓ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ያቀረበውን ቅሬታ ያጣራው ኮሚቴም በደረሰበት መደምደሚያ የአዲስ አበባ የሰላማዊ ሠልፍና የሕዝባዊ ስብሰባ ፈቃድ ክፍል የስብሰባ ጥሪ ዕውቅና ፈቃድ እንጂ የስብሰባ ጥሪ ፈቃድ ሰጥቶ እንደማያውቅ፣ የስብሰባ ጥሪ ለማድረግ የሚያስችል የመኪና ቅስቀሳ ፈቃድ ለመስጠትም ሆነ ለመከልከል የሚያስችል ሕጋዊ ማዕቀፍ የሌለ መሆኑን፣ የስብሰባ ጥሪው እንዲደናቀፍና አባላቱም እንዲታሰሩ መደረጉ ተገቢ ያለመሆኑን፣ በስብሰባ ጥሪው ላይ ፓርቲው ሲጠቀምበት የነበረው የኪራይ መኪና መቀጣቱ አግባብ ያለመሆኑን ማተቱንም ጋዜጣዊ መግለጫው ይገልጻል፡፡ ይሁንና በሪፖርቱ ላይ በቂ ውይይት ከተደረገ በኋላ ድምዳሜውን ሁሉም የምክር ቤቱ አባላት ሲቀበሉት ኢሕአዴግ ብቻ ለመቀበል ፈቃደኛ ሳይሆን እንደቀረ፣ የኢዴፓ ጋዜጣዊ መግለጫ ያመለክታል፡፡ ይህ ድርጊትም ኢሕአዴግ ለመድበለ ፓርቲ ሥርዓት መጠናከር ቁርጠኝነት እንደሚጎድለው ያረጋገጠበት ድርጊት ሆኖ እንዳገኘውም ጠቁሟል፡፡  የምክር ቤቱ አቋም በመገናኛ ብዙኃን ተዛብቶ መቅረቡም ሚዲያው በገዥ

USAID provides lab equipment to Ethiopian Commodity Exchange coffee certification laboratories in Hawassa

Image
USAID provides lab equipment to Ethiopian Commodity Exchange The United States Agency for International Development (USAID) Agribusiness Market Development (AGP-AMDe) project provided new tools and instruments to equip Ethiopian Commodity Exchange coffee certification laboratories in Hawassa, Jimma and Dilla required for Specialty Coffee Association of American (SCAA) Certification. Coffee is the number one export earner for Ethiopia and the Government of Ethiopia strategy is to increase export volume and value. To support the expansion of the coffee market, the U.S. Government, invested $175,000 USD (3.3 million birr) in new quality testing and grading instruments for the ECX labs.   The tools and instruments, including coffee grinding and roasting machines, are those used for measuring moisture, grading the coffee, preparing tasting samples, and others needed for operating the facility to international standards. USAID AMDe also supported some refurbishing of the labor

በቡና ላይ የተመሠረተው ህልውና

Image
ከቀኑ ሰባት ሰዓት አካባቢ ሆኗል፡፡ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ትይዩ የተገነቡት ካፌዎችና ሬስቶራንቶች በረንዳቸው በደንበኞች ተጨናንቋል፡፡ ካንዱ ካፌ ፊትለፊት ሰፋ ባለ ረከቦት የተደረደሩ ሲኒዎች ስር ሳር ተጎዝጉዞ፣ እጣን ሲጨስ ይታያል፡፡ ለቡና ቁርስም በስፌት ፈንዲሻ ቀርቧል፡፡ የዕጣኑ መዓዛ ቤቱን አውዶታል፡፡ የአገር ባህል የለበሰች ኮረዳም ቄንጠኛ በሆነ መልኩ የምትቀዳው ቡና ቀልብ ይስባል፡፡ የቡናው ሥርዓት የሚጀምረው ከረፋዱ 5፡30 አካባቢ ሲሆን፣ ስምንት ሰዓት ማብቂያው ነው፡፡ ስለዚህም የአካባቢው ነዋሪዎች በተለይም ደግሞ ወጣቶችና በአቅራቢያው በሚገኝ መሥሪያ ቤት የሚሠሩ ሰዎች ምሳቸውን ከበሉ በኋላ ቡና ለመጠጣት ጎራ ይላሉ፡፡ ደንበኞችም ብዙ በመሆናቸው በካፌዎቹ የሚገኙ መቀመጫዎች ሁሉ ይያዛሉ፡፡ ስለዚህም በርካታዎቹ ቆመው ለመጠጣት ይገደዳሉ፡፡ በዚህ አካባቢ ጨዋታውም ይደራል፡፡ በየካፌውና ሬስቶራንቱ በባህላዊ ሥርዓት የሚቀርበው ቡና በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅ ሆኗል፡፡ እናም የቡና ሰዓት ከማለፉ በፊት ለመድረስ ይጣደፋሉ፡፡ ሀብታሙ አዲሱንም ያገኘነው የቡና ደንበኛው ወደ ሆነው ካፍቴሪያ ለመሄድ ሲዘጋጅ ነበር፡፡ ምንም እንኳን በየቀኑ ቤተሰቦቹ ቡና ቢያፈሉም የዘወትር ደንበኛው ወደ ሆነው ሬስቶራንት ጎራ ብሎ ከቅርብ ጓደኛው ጋር ቡና እየተጎነጨ መጫወት ልምድ ሆኖበታል፡፡ በቡና ሰዓት በሬስቶራንቱ ውስጥ የሚኖረው ድባብም ደስ ያሰኘዋል፡፡ የቡና ሱስ ባይኖርበትም ሰዓቱን ጠብቆ የመጠጣት ልምድ አለው፡፡ ‹‹አንዳንድ ሰዎች የቡና ሥርዓቱን እያዩ ለመጠጣት ሲሉ ብቅ ይላሉ፡፡ ምናልባትም አቀራረቡ የተለየ መስህብነት ስላለው ደንበኞች መቀመጫ ቦታ ቢያጡ እንኳ ቆመው እንዲጠጡ አድርጓቸዋል፡፡ ዋጋውም ሦስት ብር ከሃምሳ ሳንቲም በመሆኑ ኪስ አይጎዳም፤›› ይላል