ግራ ያጋባው የኢትዮጵያ የአዘጋጅነት ጥያቄ
ከሰሞኑ የአብዛኛው የስፖርት ቤተሰብ መነጋገሪያ የሆነው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአፍሪካ ዋንጫን ማዘጋጀት አለመቻል እንደ አንድ አገራዊ አጀንዳ እያነጋገረ ይገኛል፡፡ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) አዲስ አበባ ላይ ጠቅላላ ጉባኤውን ማሰናዳቱን ተከትሎ አብዛኛው የስፖርት አፍቃሪ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. የ2017 የአፍሪካ ዋንጫ የአስተናጋጅነቱ ዕድል እንዲሰጣት ለካፍ ያቀረበችው ጥያቄ እንድትጠቀምበት ይረዳታል ተብሎ ቢጠበቅም፣ የኋላ ኋላ ግን ‹‹አቅም የለንም›› በሚል ምክንያት ፍላጐቷን ወደ ጎን ማድረጓ ከፌዴሬሽኑ ተሰምቷል፡፡ ‹‹ሲጀመር ምን ያህል አቅም ኖሮን ነበር?›› ሲል የሚጠይቀው የእግር ኳስ ቤተሰብ አገሪቱ የ2017ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት ዕድሉ እንዲሰጣቸው ከጠየቁ አገሮች አንዷ ሆና መቅረቧ አስገራሚና በዕቅድ ያለመመራት አሠራር መኖሩን በግልጽ እንደሚያመለክት ያወሳሉ፡፡ ካፍ ባለፉት ሳምንታት በአዲስ አበባ ባደረገው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ከተመለከታቸው አጀንዳዎች የ2019 የአፍሪካ ዋንጫ ለካሜሮን፣ የ2021 ለአይቨሪኮስት፣ የ2023 ለጊኒ የአስተናጋጅነቱን ዕድል የሰጠበት ይጠቀሳል፡፡ የ2017ቱን ቀደም ሲል የአስተናጋጅነቱን ዕድል ለሊቢያ የተሰጠ መሆኑ ቢታመንም፣ ወደ ኋላ ላይ ግን በአገሪቱ በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት ካፍ ዕድሉን ለሌሎች አገሮች አሳልፎ እንደሚሰጥ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ አልጄሪያና ዚምባቡዌ የ‹‹እናዘጋጃለን›› ጥያቄያቸውን ለካፍ አስገብተዋል፡፡ የመጨረሻው ቀን ገደብም መስከረም 30 ቀን መሆኑም ይታወቃል፡፡ ፌዴሬሽኑ ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ሦስት የአፍሪካ ዋንጫዎች ማስተናገዷን በመጥቀስ፣ በአህጉር ደረጃ ከፍተኛ ግምት የሚሰጠውን የ2017ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ በ