Sidaamu Fidalla
የሲዳማን ቋንቋ ለየት ባለ መልኩ ማቅረብን ኣላማ ያደረገው ይህ መጽሐፊ በውስጡ 33 የሲዳሙኣፎ ፊደላቲን የያዘ ሲሆን፤ ከዚሁ ውስጥ 26 ቱ ነጠላ ኣሃዝ ፊደላቲ ሲሆኑ የተቀሩት 7 ቱ ደግሞ ባለ ሁለት ኣሃዝ ፊደላቲ ናቸው። መጽሐፉ 26 ቱ በላቲን ማለትም በእንግሊዥኛ እና በሌሎች ቋንቋዎች የሚገኙትን ፊደላቲ በቀላሉ ለመማር እንድያመች ዘንድ በፊደላቱ የሚጀምሩትን ቃላት በስዕል ኣስደግፎ ኣቅርቧል። በተጨማሪም የፊደላቱን የያዙ ቃላት በሲዳማ እና በኣፍሪካ ኣፌ ታሪኮች በማዋዛት በማይሰለች መልኩ ይተርካል። የተቀሩት ሰባቱ ለሲዳማ ኣፎ እንድመቹ ተደርገው የተቀረጹት፦ ch, dh, ny, ph, sh, ts እና zh የተባሉ ፊደላቲ በተመሳሳይ የመማሩን ህደት በሚያቀላጥፍ መልኩ ቀርበዋል። የመጽሐፉ የመጨረሻ ክፍል ደግሞ የሲዳማን የቀን፤ ሳምንት እና ወራት ኣቆጣጠርን በተመለከተ በማብራሪያ ኣስደግፎ ኣቅርበዋል። በኣጠቃላይ ይህ በካላ ጋልፋቶ ዎናጎ የተዘጋጀው የሲዳማ ፊደላቲ መጽሐፍ ፤ለሲዳማ ቋንቋ ጀማሪ ተማሪዎች ቋንቋውን በቀላሉ መማሪ እንድችሉ ከፍተኛ እገዛ የሚያድርግ ነው። መጽሐፉ በኣሁኑ ጊዜ በኣማዞን ደረ ገጽ ላይ በሽያጭ ላይ ይገኛል። የሲዳማን ቋንቋ ለመማሪ ለምፈልጉ ወዳጆች በሰጦታ መልክ ለማበርከት ኣልያም ለልጆቻችሁ ማስተማሪያነት መጽሐፉን መግዛት የምትሹ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መግዛት የምትችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን። ሲዳሙ ፊዳላ