ያለሐኪም ትዕዛዝ የፀረ ተህዋስያን መድኃኒቶችን መጠቀምና ጠንቆቹ
መድኃኒት ማለት በሽታን ለመመርመር፣ ለመከላከል፣ ለማከምና ለመፈወስ የምንጠቀምበት ኬሚካል ነው፡፡ መድኃኒት ለበሽተኛ በሐኪም ትዕዛዝም ሆነ ያለሐኪም ትዕዛዝ ሊሰጥ ይችላል፡፡ ያለሐኪም ትዕዛዝ የሚሰጡ መድኃኒቶች በሽተኛው ላይ ብዙ የጎንዮሽ ጉዳቶች የሌሏቸውና በሽተኛው በሚፈልግበት ጊዜ በመድኃኒት ባለሙያው ድጋፍ፣ ምክርና መረጃ በመመርኮዝ የሚወስዳቸው ናቸው፡፡ በአገራችን ባለው የምግብ የመድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን መመርያ መሠረት ለራስ ምታት፣ ለጉንፋን፣ ለሆድ ቁርጠትና ለመሳሰሉት ቀላል ሕመሞች የሚወሰዱ መድኃኒቶች ያለሐኪም ትዕዛዝ ሊሸጡ የሚችሉ ናቸው፡፡ በሐኪም ትዕዛዝ (በማዘዣ ወረቀት) የሚሰጡ መድኃኒቶች፤ በባለሙያው ከፍተኛ ጥንቃቄ ተወስዶባቸው ካልታዘዙ በስተቀር በበሽተኛው ላይም ሆነ በማኅበረሰቡ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ ናቸው፡፡ በአግባቡ ካልተወሰዱም በሽታ አምጭው ተህዋስ መድኃኒቱን እንዲላመድ ያደርጋሉ፡፡ በሐኪም ትዕዛዝ ከሚወሰዱት መድኃኒቶች መካከል የፀረ ተህዋስያን መድኃኒቶች (Antimicrobials) ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ፀረ ተህዋስያን መድኃኒቶች የሚባሉት በቫይረስ፣ በባክቴሪያ፣ በፈንገስና በፕሮቶዝዋ አማካይነት የሚመጡ በሽታዎችን ለማከም የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ ፀረ ተህዋስያን መድኃኒቶችን ያለሐኪም ትዕዛዝ መውሰድ ከሚያስከትላቸው ችግሮች መካከል አንዱና ዋነኛው የፀረ ተህዋስያን መድኃኒቶች መላመድ (Drug Resistance) ነው፡፡ አንድ የፀረ ተህዋስያን መድኃኒት በትክክለኛ መጠኑ ወይም የሰውነታችን ሴሎች ሊቋቋሙት በሚችሉት መጠን ወይም ከመጠኑ በላይ ተሰጥቶ ተህዋስያኑ የማይሞቱ ወይም መራባታቸውን የማያቆሙ ከሆነ ተህዋስያኑ መድኃኒቱን ተላመዱ ይባላል፡፡ የፀረ ተህዋስያን መድኃኒ