Posts

ኢትዮጵያ ወደ ውጪ ከምትልከው ቡና የምታገኘው ገቢ በ25 በመቶ እንደሚያድግ እየተነገረ ነው፤ 1/3ኛውን የቡና ምርት ኣቅራቢ የሆኑትን የሲዳማ ቡና ኣምራቾችን ተጠቃሚ ለማድረግ ምን ታስቧል?

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 15፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) ኢትዮጵያ በ2014/15 ወደ ውጪ ከምትልከው የቡና ምርት ከ900 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ልታገኝ እንደምትችል ተገለጸ። ይህም ቀደም ሲል ከነበረው ገቢ የ25 በመቶ እድገት ያሳየ ነው ተብሏል። የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አለምሰገድ አሰፋ እንደተናገሩት፥ በያዝነው አመት የብራዚል ቡና በድርቅ በመመታቱ የቡና ዋጋ መሻሻል አሳይቷል። በዚህም አሁን በገበያ ላይ ያለው የቡና ዋጋ ባለበት ሊቀጥል እንደሚችል ነው አቶ አለምሰገድ የጠቆሙት። ዋነኛዋ ቡና አምራች ሀገር ብራዚል ባስተናገደችው ድርቅ የተነሳ አቅርቦቷ መቀነሱን ተከትሎ፥ ኒውዮርክ እስከ ጥር ወር ድረስ 70 በመቶ የቡና ፍላጎትን ከኢትዮጵያ በመግዛት ስትሸፍን መቆየቷም ተዘግቧል። በአፍሪካ ቀዳሚዋ ቡና አምራች ሀገር ኢትዮጵያ፥ ባለፉት 12 ወራት ወደ ውጪ ከላከችው ቡና 719 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ያገኘች ሲሆን ፥ ይህም ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፃር በ3 ነጥብ 7 በመቶ ዝቅ ያለ ነው። ሀገሪቱ በዚህ አመትም ከ500 ሺህ ቶን በላይ ቡና ታመርታለች ተብሎ ይጠበቃል ያሉት ስራ አስኪያጁ፥ ከአጠቃላይ ምርቱ ግማሽ ያህሉም ለውጭ ገበያ እንደሚቀርብ ተናግረዋል። የቡና አምራች አካባቢዎች መስፋፋት ለምርቱ ማደግ አስተዋፅኦ ያደርጋልም ነው ያሉት። በሼክ ሙሃመድ አላሙዲ የሚተዳደረው የሆራይዘን ፕላንቴሽን፥ 10 ሺህ ሄክታር  በበበቃ እንዲሁም 12 ሺህ 114 ሄክታር የቡና እርሻ መሬት መግዛቱን አስታውሶ የዘገበው ብሉምበርግ ነው። ኤፍ.ቢ.ሲ

ኢትዮጵያ በናንጂንግ ኦሎምፒክ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆነች

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 19፣ 2006 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ በቻይና ናንጂንግ እየተካሄደ ባለው የታዳጊ ወጣቶች የኦሎምፒክ ጨዋታ ቅዳሜና ትናንት በተደረጉ የአትሌቲክስ የፍጻሜ ውድድሮች ከአፍሪካ አንደኛ ከአለም የ21ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። በሴቶች ኮከብ ተስፋዬ በ1 ሺህ 500 ሜትር 4 ደቂቃ ከ15 ሰኮንድ ከ38 ማይክሮ ሰከንድ ውድድሩን በአንደኝነት በማጠናቀቅ የወርቅ ሜዳሊያ አስመዝግባለች። በ8 መቶ ሜትር ሴቶች የፍጻሜ ውድድርደግሞ ሀዊ አለሙ በ2 ሰዓት ከ6 ደቂቃ ከ01 ማይክሮ ሰከንድ ሁለተኛ ሆና ስትጨርስ፥ በሴቶች የ3 ሺህ ሜትር ብርሃን ደምሴ ውድድሩን በሶስተኝነት አጠናቃለች። በወንዶች ዮሚፍ ከጀልቻ በ3 ሺህ ሜትር ፍጻሜ በ7 ደቂቃ ከ56 ሰከንድ ከ20 ማይክሮ ሰከንድ ውድድሩን በአንደኝነት በማጠናቀቅ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝቷል። በወንዶች 1 ሺህ 500 ሜትር ደግሞ ሙሉጌታ አሰፋ በሁለተኝነት ማጠናቀቅ ችሏል። ውድድሩ በመጪው ረቡዕ ፍጻሜውን የሚያገኝ ሲሆን፥ ኢትዮጵያውያን ወጣት ታዳጊ ስፖርተኞች ጥሩ ፉክክር እያደረጉ ይገኛሉ። ዛሬ ከሰዓት በኋላ የ2 ሺህ ሜትር መሰናክል በሁለቱም ጾታና በ800 ሜትር ወንዶች ኢትዮጵያውያን በርቀቱ ተካፋይ ይሆናሉ ። ምንጭ፦  ኤፍ/ቢ/ሲ

በሐዋሳ ከተማ ህዝባዊ ስብሰባዎችን ማድረግ ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ኣስቸጋሪ እንደሆነ ቀጥሏል

-ኢራፓ በሐዋሳ ሊያደርገው የነበረው ስብሰባ እንዳይካሄድ መከልከሉን ገለጸ - በወጣው መግለጫ የፓርቲው መሪዎች አልተግባቡም የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ) ነሐሴ 11 ቀን 2006 ዓ.ም. እና በተለዋጭ በተያዘ ፕሮግራም ነሐሴ 18 ቀን 2006 ዓ.ም. በደቡብ ክልል ርዕሰ ከተማ በሐዋሳ ሊያደርገው የነበረው ሕዝባዊ ስብሰባ፣ በኢሕአዴግ ተፅዕኖ ፈጣሪነት ተገቢ ባልሆነ ምክንያትና ቢሮክራሲ መከልከሉን አስታወቀ፡፡ በፓርቲው የተሰጠው መግለጫ ስብሰባ እንዳናካሂድ ተከልክለናል ቢልም፣ የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ተሾመ ወልደ ሰማያት ግን መግለጫው የወጣው ‹‹የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ሳይወያይበት›› ነው በማለት ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ምክትል ፕሬዚዳንቱ፣ ‹‹ኢራፓ የፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባል ስለሆነ ጉዳዩን ወደዚያ መውሰድ እንጂ መግለጫ ለማውጣት መቸኮሉ አስፈላጊ አይደለም፤›› በማለት ገልጸዋል፡፡   የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ ተሻለ ሰብሮ በበኩላቸው፣ ‹‹›እያንዳንዱ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አይወያይም፤›› ብለው፣ መግለጫውን በፓርቲው ማሕተም ማውጣታቸውን ገልጸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ‹‹በሁሉም ጉዳዮች ላይ መግለጫ ለመስጠት የግድ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መሰብሰብ አይኖርበትም፤›› በማለት የወጣው መግለጫ የፓርቲው አቋም ነው በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ፓርቲው በሐዋሳ ሊያደርገው የነበረው ሕዝባዊ ስብሰባ ዓላማ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ የፖለቲካ ፕሮግራሙን ለማስተዋወቅ፣ በአገራዊና ሕዝባዊ መግባባት አስፈላጊነት ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ፣ እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎችን የሥነ ምግባር ደንብን ለማስረዳት እንደነበር በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡  ከዚህ በተጨማሪም መግለጫው፣ ‹‹ፓርቲያችን በያዘው የሕዝባዊ ስብሰባ ፕሮግ

የፊቼን በዓል በዓለም ቅርስነት ለመስመዝገብ ከሚያስፈልጉ ዶክሜንቶች መካከል ኣንዱ የሆነው እና የፊቼን በኣል ኣከባበር የምያሳይ ፊልም እስከኣሁን ድረስ ኣለመሟላቱ ተገለጸ

Image
የወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ከ ተባበሩት መንግስታት የትምህርት፤ ሳይንስ እና ባህል ማዕከል _ ዩኔስኮ ያሰባሰ ው መረጃ እንደሚያመለክተው፤ የፊቼን በኣል በኣለም ቅርስነት ለመመዝገብ መሟላት ካለባቸው ዶክመንቶች መካከል ኣንዱ የሆነው የ 10 ደቂቃ ፊልም ኣልተሟላም። ዩኔስኮ የማይዳሰሱና የማይጨበጡ ብሎም የመጥፋት ኣደጋ የተጋረጠባቸውን የሲዳማን ኣዲስ ኣመት በኣል ፊቼን የመሳሰሉ ኢንታጀብል ባህሎችን ለመጠበቅ እና ለመከባከብ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ቅርሶችን በኣለም ቅርስነት ለመመዝጋብ፦ ባህሉ ኢንታጀብል መሆኑን የምያሳይ ማስረጃ፤ ባህሉ በኣስቸኳል ጥበቃ ካልተደረገለት ልጠፋ እንደሚችል የሚገልጽ መረጃ፤ ባህሉ በኣለም ቅርስነት እንድመዘጋብ መመረጡ እና እንድመዘጋብም ዘንድ የባህሉ ባለቤት የሆነው ህዝብ እንደምፈል የገለጸበት በፊርማ የተደገፈ መረጋገጫ፤ ባህሉ እንድመዘጋብ የመጠያቂያ በጥንቃቄ የተሞላ ፎርም፤ ሰለባህሉ በስፋት የሚያትት ጥናት እና በፎቶናበፊልም የተደገፈ የባህሉን ኣከባበር ስነስርኣት የሚያሳዩ መረጃዎች መቅረብ ኣለባቸው። ኢንታጀብል ቅርሶችን የመመዝጋብ ስራ የሚስራው የዩኔስኮ ኮሚቴ ኣንድን ባህል በኣለም ቅርስነት ለመመዝጋብ የግድ ከላይ የተጠቀሱት ማስረጃዎች እንድሟሉለት ይጠይቃል። ኮሚቴው በየኣመቱ ወደ 50 የሚጠጉ ባህሎችን መርምሮ ለወሳኔ የሚያቀርብ ሲሆን፤ የምርመራው ህዴት ከሁለት ኣመታት በላይ ልወስድ ይችላል። የማስመዝጋቡን ህዴት ለማፋጠን ኮሚቴው በየኣመቱ የማስረጃ ማቅረቢያ ጊዜ ገደብ ያበጄ ሲሆን፤ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መሰረት ማስረጃዎች ያቀረቡ ባህሎች ብቻ በኮሚቴው የምታዩ የሆናል። የሲዳማ ኣዲስ ኣመት በኣል ፊቼን የተመለከቱ ማስረጃዎች በኣብዘኛው የተማሉ ቢሆን፤ የባህሉን ኣካባበር የሚያሳየ

The largest annual Advisory Forum of African Wildlife will be held in Hawassa

Image
The largest annual gathering of wildlife professionals, the wildlife agencies of the government and NGOs working in Africa will be the Advisory Forum of African Wildlife. This annual event, sponsored by SCI Foundation, will be held in Hawassa, Ethiopia, from 02 to 07 November. More information: http://www.safariclubfoundation.org/conservation/africaawcf El pasado lunes la Fundación del SCI (SCIF) asistió a la Cumbre de Líderes de EEUU y África, que se ha desarrollado en los días 4 a 6 de agosto en Washington DC, para participar en un debate sobre las mejores maneras de combatir el tráfico de vida silvestre. La reunión acogió a cincuenta jefes de estado africanos, miembros del Congreso de Estados Unidos, funcionarios de agencias gubernamentales y departamentos del Gobierno de EEUU, representantes de ONG y becarios de la Young African Leaders Initiative. El secretario del Interior de EE.UU, Sally Jewell, dirigió la discusión sobre los esfuerzos contra la caza furtiva y la futura

No Good Governance without Political Commitment

Image
The Ethiopian political sphere witnesses divergent views on the issue of governance and effective public service delivery. At one end of the aisle sit the ruling EPRDFites who take pride in the reform efforts they have undertaken to improve public service provision and streamline good governance in the various tiers of the state structure. Though they are bold enough to admit that there remains a lot to be done, they argue that due recognition ought to be given to what has been achieved over the last 23 years. A showcase to this line of the ruling Revolutionary Democrats is the recent explanation that Prime Minister Hailemariam Desalegn provided to questions raised on the issue. The premier reflected that the reform undertakings of the ruling party are not just paper tigers, but verifiable activities bringing change in a public sector that had, for a long time, been a breeding ground for patrimonialism. As if to extend the premier’s argument, Temesgen Tilahun, a state minister

የዩኒቨርሲቲ ሰልጣኝ ተማሪዎች ስልጠናው ግጭትን የሚያስነሳ በመሆኑ እንዲቆም ጠየቁ

 *ሰልጣኞቹ ፌስ ቡክ እንዳይጠቀሙ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል ከነሀሴ 9 ጀምሮ በደብረማርቆስ ከተማ በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፣ ተክለኃይማኖት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ቤተ መንግስት፣ መምህራን ኮሎጅና የደብረ ማረቆስ መሰናዶ ትምህርት ቤት ተከፋፍለው በአራት የሥልጠና ቦታዎች እንዲሁም 45 የውይይት ቡድኖች ስልጠና እየወሰዱ የሚገኙት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስልጠናው ከፋፋይና ለትውልዱ ጎጅ በመሆኑ ሊቆም እንደሚገባ ማሳሰባቸውን ሰልጣኞቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ተማሪዎቹ በተለይም ‹‹የኢትዮጵያ ህዝቦች ትግልና የአገራችን ህዳሴ›› በሚል ህዝብን ከህዝብ ያጋጫል ያሉትን ያሉት ሰነድ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ እንዳሰሙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ተማሪዎች ‹‹እስር በእስር ለማናከስ የተዘጋጀ ሰነድ ነው፡፡ በመሆኑም ሰነዱ ሊቃጠል ይገባዋል፡፡ በቀጣይ ወደ ዩኒቨርሲቲ ስንገባ የሚያጋጨን ስለሆነ ስልጠናው በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል፡፡ የኦሮሚያ ተማሪዎችን አመጽ የቀሰቀሰው በዚህ የኢህአዴግ ከፋፍለህ ግዛ ሴራ ነው፡፡ ሰነዱ እንደሚለው ኢትዮጵያ ከታናሽንት ወደ ታላቅነት ሳይሆን ከታላቅነት ወደታናሽነት ነው የወረደችው፡፡ ለዚህ ከፋፋይ ሰነድ በርካታ ወጭ ወጥቶ እርስ በእርሳችን ለማናከስ ከሚጣር በገንዘቡ በየጎዳናው የወደቁ ኢትዮጵያውያንን ከርሃብ መታደግ ይችል ነበር፡፡›› በሚል ጠንካራ ተቃውሞ ማሰማታቸውን ገልጸውልናል፡፡ ተማሪዎቹ አክለውም ‹‹አጼ ምኒልክ በጊዜያቸው መልካም ስራ ሰርተዋል፡፡ ስህተት ሰሩ እንኳ ቢባል የዘመኑ ወጣቶች ያ ስህተት ላይ ተሳታፊዎች ባለመሆናችን የእኛም ስህተት ተደርጎ ከሌሎቹ ጋር ለማናከሻነት መዋል የለበትም፡፡ በዚህ ዘመን ህወሓት፣ ብአዴንና ሌሎቹ የኢህአዴግ አባላት እንጅ ህዝብ ነፍጠኛ ሊባል አይገባም፡፡ ብአዴን አማርኛ ተናጋሪውን አይወክልም፡፡››