ሁለተኛው ቱር መለስ የአረንጓዴ ልማት የብስክሌት ውድድር በሀዋሳ ከተማ
ሃዋሳ ነሐሴ 14/2006 በሀዋሳ ከተማ ዛሬ የተጀመረው ሁለተኛው ቱር መለስ የአረንጓዴ ልማት የብስክሌት ውድድር በደቡብና ኦሮሚያ ክልል በሚገኙ 11 ከተሞች ከቀጠለ በኋላ ነሀሴ 27 ፍጻሜውን በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚያደርግ ተገለጸ፡፡ በሀዋሳ ከተማ በተካሄደው የ80 ኪሎ ሜትር ውድድር ከትግራይ ክልል የጉና፣ ትራንስ ኢትዮጵያና መሰቦ ክለብ ብስክሌተኞች አሸናፊ በመሆን የተዘጋጀላቸውን ሽልማት ከእለቱ የክብር እንግዶች ተቀብለዋል። በስፖርታዊ ውድድሮች ሀገሪቱ ውጤታማ መሆን እንድትችል የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን በቱር መለስ አረንጓዴ ልማት የብስክሌት ውድድር ላይ የተሳተፉ ተወዳዳሪዎች አስታውቀዋል፡፡ በሁለተኛው የቱር መለስ አረንጓዴ ልማት የብስክሌት ውድድር ላይ ከተሳተፉ ተወዳዳሪዎች መካከል የሜታ አቦ ፣የመቀሌ ብሩህ ተስፋና የድሬደዋ ከነማ ተወዳዳሪዎች ለኢዜአ እንደገለጹት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያ በልማቱ መስክ ያስመዘገበችው ድል በስፖርቱ መድገም እንድትችል ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡ የሜታ አቦን ክለብ የወከለው ተወዳዳሪ በርይሁን መርሶ እንዳለው መለስ ስፖርትን የልማት አንዱ አካል በማድረግ ባበረከቱት አስተዋጽኦ ሀገራችን በየውድድሩ የምታመጣው ውጤት ከፍተኛ መሻሻል እየታየበት ነው፡፡ የመቀሌ ብሩህ ተስፋ ክለብ ተወዳዳሪ ቴዎድሮስ ሀብቱና የድሬደዋ ከነማ ተወዳዳሪ ብሩክ አለማየሁ እንዳሉት መለስ ሀገሪቱ በልማት መስክ ብቻ ሳይሆን በስፖርቱም የቀድሞ የበላይነቷ እንዲረጋገጥና እየተመዘገበ ላለው ውጤት መሰረት የጣሉ ጀግና መሪ ናቸው፡፡ በመለስ የተጀመሩ የልማት የመልካም አስተዳደርና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የሚጠበቅባቸውን ግዴታ ለመወጣት ዝግ