Posts

ለ200 ሺህ ኢትዮጵያውያን ስራ ፈጣሪዎች ስልጠና ሊሰጥ ነው

አዲስ አበባ ነሐሴ 8/2006 በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተባባሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም እና በምስራቅ አፍሪካ የማይክሮሰፍት ድርጅት 200 ሺህ ኢትዮጵያዊያን  ስራ ፈጣሪዎችን ለማብቃት የግል ዘርፍ የትብብር ስምምነት ተፈራራሙ። የልማት ፕሮግራሙ ለኢዜአ እንደገለጸው ስምምነቱ ሁለቱ ደርጅቶች በኢትዮጵያ ለሚካሄደው የስራ ፈጠራ ፕሮግራም ለ200 ሺህ ስራ ፈጣሪዎች የስልጠናና የክትትል አገልግሎት ለመስጠት ተስማምተዋል። እነዚሀ አገልግሎቶችም አገር በቀል ስራ ፈጣሪዎችን በማብቃት የአፍሪካን ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማፋጠንና በዓለም ተወዳዳሪነቷን ለማሳደግ  የማይክሮሶፍት ፎር አፍሪካ ኢኒሽዬቲቭ አካል ይሆናሉ፡፡ ስምምነቱ በስራ ፈጠራ ዙሪያ የሚከናወኑ ተግባራትን ለማሳደግ ያለመ ነው። በስምምነቱ መሰረት ከፍተኛ የማይክሮሶፍት በጎ ፍቃደኞች ስራ ፈጣሪዎችን በመከታተል በስትራቴጂና በገበያ ድጋፍ በማድረግ ምርጥ ስራ ፈጣሪዎችን በመደገፍ ለማይክሮሶፍት ፎር አፍሪካ ኢንሽዬቲቭ ሽልማት እጩ ያቀርባሉ። በተጨማሪም ለጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች ነጻ ሶፍትዌር ለሚያቀርበው ማይክሮሶፍት "ቢዝስፓርክ" ለተሰኘ የዓለም ፕሮግራም እድል እንዲያገኙ ለማስቻል ይሰራሉ። በቀጣይም ስራ ፈጣሪዎችን ምርታቸውንና አገልግሎቶቻቸውን በማቅረብ  በማይክሮሶፍት ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ በኩል ዓለም  አቀፍ ተቀባይነት እንዲያገኙ ድጋፍ ይሰጣሉ። ስምምነቱ ጥቃቅንና አነስተኛ ቢዝነስና ስራ ፈጣሪዎችን ለማነሳሳት ለተቀረጸው የራስን ቢዚነስ መገንባት በሚል ስያሜ  የስልጠና ፕሮግራም  ያካትታል፡፡ በኢትዮጵያ  የልማት ፕሮግራሙ ተወካይ ኢዩጌኔ ኦውሱ  በማይክሮሶፍት የሚቀርቡ ምርቶችና አገልግሎቶች  ወጣትና ተስፋ ሰጪ ስራ ፈጣሪዎችን አቅም ለማመንጨት ልዩ የሆነ እድ

Sidama: Assessment on the Impacts of Investments in Hawassa City Administration

Image
Photo from hawassaonline Abstract The study was undertaken with the prime objective of assessing the impacts brought out by investments in Hawassa City. As the study is basically both empirical and analytical in nature, field survey method was adopted. The study considered only the projects which are operational and at implementation stages. Among the nine investment streams, investors from six streams had given consent to cooperate in the data collection process.  Thus the total population for the sample purpose from six streams is 288. Out of 288 projects, 40 sample investors were selected on disproportionate to size sampling basis. Both primary and secondary sources were sought for data collection. Semi structured questionnaire was prepared and distributed among the sample investors. Interviews were conducted with officials of Hawassa City Investment and Environmental Protection Bureau. Focus group discussion was conducted among the dwellers residing near to factories.

Aleta Wondo: the Coffee Capital of Sidama Country

Image
Photo by sweet maria's Dejazmach Balcha Safo , Governor of Sidamo , originally constructed his ketema or fortified camp in Wendo, but he later moved it to Hagere Selam . While passing through the area February 1909, Dr. Drake Brockman notes that the governor of Western Sidamo, Dejazmach Tessema Nadew made this town (which he calls "Alata") his headquarters. American naturalists arrived at the Wendo village 29 December 1926, and camping outside the village for a while. Grazmach Kebede Dihala Mikael, the village potentate, implored them to camp near his house, explaining that there were plenty of shiftas or outlaws in the area. Wendo was occupied by the Italian Laghi Division on 30 November 1936. It was retaken by the 1st Gold Coast Regiment on 22 May 1941, without a single shot fired. The Allied forces accepted the surrender of a Brigadier General and some 3,000 prisoners. By 1958 Wendo was one of 27 places in Ethiopia ranked as First Cla

ብሔራዊ ሊግ የሚቀላቀሉ ክለቦችን ለመለየት ከመጪው ሃሙስ ጀምሮ ውድድር ይካሄዳል

Image
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) በቀጣዩ አመት ወደ ብሔራዊ ሊግ የሚቀላቀሉ ክለቦችን ለመለዬት ከመጪው ሃሙስ ጀምሮ በሃዋሳ ከተማ ውድድር ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ። የፌዴሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ውንድምኩን አላዩ እንደገለጹት፥ በቀጣዩ ዓመት ወደ ብሔራዊ ሊግ የሚቀላቀሉ ስምንት ክለቦችን ለመለየት ከዘጠኙ ክልሎች እና ከሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ 31 ክለቦች በውድድሩ ተሳታፊ ይሆናሉ። አማራ፣ ደቡብ፣ ኦሮሚያና ትግራይ ክልሎች እንዲሁም የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳድሮች እያንዳንዳቸው አራት ክለቦችን ያሳተፋሉ፡፡ የአፋር እና የቤንሻንጉል ጉምዝ  ክልሎች ደግሞ እያንዳንዳቸው ሁለት ክለቦችን የሚያሳትፉ ሲሆን፥ ጋምቤላ፣ ሐረር እና ሶማሌ ክልል እያንዳንዳቸው በአንዳንድ ክለቦች ይወከላሉ። ውድድሩ ከሃሙስ ጀምሮ እስከ ነሐሴ 25 ቀን ድረስ ለሁለት ሳምንታት የሚቆይ ይሆናል፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሊግ ውድድር ከዋናው ፕሪሚየር ሊግ ቀጥሎ ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው ውድድር ሲሆን 69 ክለቦችን የሚያሳትፍ ነው። ምንጭ፦ ኢዜአ _____________________________________________________________ We welcome comments that advance the story through relevant opinion and data. If you see a comment that you believe is irrelevant or inappropriate, please! inform us. The views expressed in the comments do not represent those of Bloggers.

ዩኒቨርስቲው የቆጮን ምርት በቀላል ዘዴ ጥቅም ላይ ለማዋል እየሰራ ነው

Image
ዲላ ነሐሴ 4/2006 የቆጮን ምርት በቀላል ዘዴ ጥቅም ላይ ማዋል የሚያሰችል አዲስ ቴክኖሎጂ ለአርሶ አደሩ እያስተዋወቀ መሆኑን በሃዋሳ ዩኒቨርስቲ የቴክኖሎጂ ኢንሰቲትዩት ገለጸ፡፡ ኢንሰቲትዩቱ የቆጮ ማጠብያ ቴክኖሎጂ ማሽንና የአሰራሩ ዘዴውን ከሚገልጽ ሙሉ መረጃ ጋር ሰሞኑን ለዲላ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ሰጥቷል፡፡ የኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይርክተር ዶክተር ሞልቶት ዘውዴ እንደገለጹት የቆጮን ምርት በዘመናዊ መንገድ በቀላል ዘዴ ለማምረት የሚያስችል ቴክኖሎጂን በማስፋፋት በተለይ የሴት አርሶ-አደሮችን ድርብ ስራ ለመቀነስ እየሰሩ ናቸው፡፡� ቴክኖሎጂው በአንድ ጊዜ ከሶስት ኪሎ በላይ ቆጮ በማጠብ ጥራቱን የጠበቀና ከብክነት የፀዳ ምርት ከመስጠቱም ባሻገር በሴቶች ላይ የሚደርሰውን የስራ ጫና ያቃልላል፡፡ ዶክተር  እንዳሉት ከዚህ በፊት ቆጮን አጥቦ ለመጠቀም የሚወሰደውን ጊዜ በግማሽ መቀነስ የሚያስችል አሰራር ነው፡፡ በእንሰት ምርት ላይ ችግር ፍቺ የሆኑ ምርምሮችን በማድረግ ቴክኖሎጂን በማስፋፋት የቆጮን ምርትና ምርታማነት ለመጨመር የቴክኖሎጂ ኢንሰቲትዩቱ ትኩረት መስጠቱን ተናግረዋል፡፡ ምርቱ በሚሰጠው ግልጋሎት ልክ ምርምር አልተደረገበትም ያሉት ዳይሬክተሩ በክልሉ ቆጮ አምራች የሆኑ በርካታ አካባቢዎች ቴክኖሎጂውን በመጠቀም እየደረሰ ያለውን የምርት ብክነትንና የአርሶ አደሩን ጉልበት ስለሚቀንስ ቴክኖሎጂውን በስፋት ለማዳረስ እየሰሩ ናቸው፡፡ የዲላ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ምክትል  ዲን አቶ ተሾመ እንግዳ በበኩላቸው ከሃዋሳ ዩኒቨርስቲ የቴክኖሎጂ ኢንሰቲትዩት ጋር በመተባበር የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ማደረጋቸው ኮሌጁ ላለበት አካባቢ ማህበረሰብ በርካታ ጠቀሜታ እንዳለው አስረደተዋል። ቴክኖሎጂውንም በአጭር ጊዜ ውስጥ በዝቅተኛ ዋጋ በማምረትና