24ኛው አገር አቀፍ አጠቃላይ የትምህርት ዘርፍ ጉባኤ በሀዋሳ ከተማ ተጀመረ
ሀዋሳ ነሐሴ 5/2006 በመላው ሀገሪቱ ጠንካራ የትምህርት ልማት ሰራዊት በመገንባትና ምርጥ ተሞክሮዎችን በማስፋት የትምህርት ተሳትፎና ጥራትን ለማሳደግ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዳለበት ትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡ 24ኛው ሀገር አቀፍ አጠቃላይ የትምህርት ዘርፍ ጉባኤ” በመላው ህብረተሰብ የነቃ ተሳትፎ የትምህርት ልማት ግቦቻችንን እናሳካለን “በሚል መሪ ቃል ዛሬ በሃዋሳ ከተማ ተጀምሯል፡፡ በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፉአድ ኢብራሂም ጉባኤውን ሲከፍቱ እንደተናገሩት የሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች ህገ መንግስታዊ መብትና እኩልነት ከተረጋገጠ ወዲህ በራሳቸው ቋንቋ በመማር ባህላቸውን በትምህርት ለማሳደግና ለማስተዋወቅ በተፈጠረላቸው ምቹ ሁኔታ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ሁሉም ዜጋ ፍትሃዊ የትምህርት አገልግሎትን በነፃ እንዲያገኝ፣ የትምህርት ጥራት የሀገሪቱን ቀጣይ ተወዳዳሪ በሚያረጋግጥ ሁኔታ እንዲጠበቅ፣ በዘርፉ የተገኘውን ምርጥ ተሞክሮ በማስፋት ሂደቱን በተቀናጀ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ለማሳደግ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡ ለሀገሪቱ ልማት፣ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር መረጋገጥ ቁልፍ ሚና የሚጫወተውን ትምህርት በፍትሃዊነትና ጥራት ለሁሉም ዜጋ ለማዳረስ ባለፉት ዓመታት በተሰሩ ስራዎች አበረታች ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል፡፡ በዋናነት የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጅ ተቀርጾ ተግባራዊ መደረጉ፣ ህብረተሰቡ የትምህርት ጉዳይ የኔ ጉዳይ ነው በሚል ስሜት በጉልበት፣በገንዘብና እውቀት በተጨማሪ በየትምህርት ተቋማት በመገኘት የሚያደርገው የድጋፍና ክትትል ስራ ቁልፍ ሚና መጫወቱን ገልፀዋል፡፡ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ግለሰቦች በመንግስት ያልተሸፈኑ የትምህርት ስራዎችን ለማገዝ የትምህርት ተቋማት በመ