መንግሥት የገንዘብ ምንዛሪ ተመን አላስተካክልም አለ
- ከሚመስሏት አገሮች ዝቅተኛ ተወዳዳሪነት አላት - መንግሥት የገንዘብ ምንዛሪ ተመን አላስተካክልም አለ የዓለም ባንክ ለሦስተኛ ጊዜ ባካሄደው የቅርብ ጊዜ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ጥናት፣ ኢትዮጵያ በአሥር ዓመት ውስጥ አስከፊ የተባለውን የወጪ ንግድ አፈጻጸም ማስመዝገቧን አመለከተ፡፡ መንግሥት የኤክስፖርት ዘርፍ መዳከሙን አምኗል፡፡ በባንኩ ዋና ኢኮኖሚስትና የፕሮግራም መሪ የሆኑት ዶ/ር ላርስ ክርስቲያን ሞለር፣ ‹‹ባለፉት 18 ወራት በተለይ አገሪቱ እያሽቆለቆለ የመጣ የወጪ ንግድ ውጤት አስመዝግባለች፤›› ብለዋል፡፡ ቀድሞውንም ለውድድር ተጋላጭ በሆኑ የግብርና ውጤቶች ላይ የተመሠረተው የአገሪቱ ኤክስፖርት ዘርፍ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዓለም ላይ በታየው የሸቀጦች ዋጋ መቀነስ የተነሳ፣ አጣብቂኝ ውስጥ በመግባቱ ነው አስከፊ የተባለውን አፈጻጸም ያስመዘገበው፡፡ ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ያሳየው ለውጥ ከሁለት እስከ ሦስት ከመቶ ዝቅ ያለ መሆኑን፣ ዓምና ጭራሽ ከዜሮ በታች አሽቆልቁሎ እንደነበርም ባንኩ አስታውሷል፡፡ 87 በመቶ የሚደርሱት ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ከአነስተኛ ገንዘብ አቅራቢዎች የብድር አቅርቦት እንደሚያገኙ፣ ከ94 በመቶ በላይ የሚሆኑት ትልልቅ ድርጅቶች ደግሞ ባንኮች ፋይናንስ እንደሚያደርጓቸው የባንኩ ጥናት ያመለክታል፡፡ በሁለቱ መካከል የሚገኙት አነስተኛና መካከለኛ ድርጅርቶች ግን ብድር እያገኙ እንዳልሆነ ተጠቁሟል፡፡ መሀል ላይ የተረሱ ወይም ‹‹ዘ ሚሲንግ ሚድል›› በሚል በባንኩ የተገለጹት ድርጅቶች ከባንክ የሚያገኙት ፋይናንስ ስድስት በመቶ ብቻ መሆኑን፣ ከአነስተኛ የገንዘብ ድርጅቶች ብድር የሚያገኙ ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ደግሞ 11 ከመቶ ናቸው፡፡ ይህ በመሆኑም አነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶች ወደላይ እንዳያድጉና ኤክስፖር