ደመወዝ ጭማሪና አሳዛኙ ድርጊት
የአገሪቱ የግብይት ሥርዓት ሁሌም የሚተች ነው፡፡ ይሻሻላል ተብሎ ሲጠበቅ ብሶበት ይገኛል፡፡ በግብይት ሥርዓቱ ውስጥ ያሉ ተዋንያኖች ከእንከን ፀድተው አያውቁም፡፡ ጥቂት የማይባሉ ነጋዴዎች ከሸማቾች ሮሮ አምልጠው ያውቃሉ ተብሎ አይታሰብም፡፡ የንግድ ሥርዓታቸው ሚዛናዊ አይደለም፡፡ የራስን ጥቅም ያስቀድማሉ፡፡ በሸማቾች ሲረገሙ መስማትም የተለመደ ነው፡፡ ይህ አብዛኛውን የንግዱ ኅብረተሰብ የሚገልጽ ነው ባይባልም፣ ጥቂት የማይባሉ ነጋዴዎች መገለጫ ሊሆን እንደሚችል ግን ደፍሮ መናገር ይቻላል፡፡ የእስከዛሬውን ትተን ሰሞኑን ብዙዎቻችንን ያስገረመን፤ እንደውም ያበሳጨንን ድርጊት በአስረጅነት መግለጽ ይቻላል፡፡ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን እንደተሰማው መንግሥት ከሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ የመጨመሩን መረጃ ተከትሎ እየፈጸመው ነው የተባለው ድርጊት ነው፡፡ ነጋዴዎቻችንን ያስገረመን ብቻ ሳይሆን መች ይሆን እንዲህ ካለው ተግባር ፀድተው ሸማቾችን በአግባቡ የሚያስተናግዱት? ብለን አሁንም እንድንጠይቅ የሚያደርግ ነው፡፡ ደመወዝ ሊጨመር ነው የሚለውን ወሬ የሰሙ አንዳንድ ነጋዴዎች ወዲያው የዋጋ ለውጥ አደረጉ፡፡ ዋጋ ጨመሩ፡፡ ነገሩ ሠርግና ምላሽ ሆነላቸውም ብንል ማጋነን አይሆንም፡፡ ደመወዝ ከተጨመረ እኛም ዋጋ መጨመር አለብን የሚለው ስግብግብ ስሜትቸው ፈጥጦ ወጣና ሸማቹን ምስቅልቅል ስሜት ውስጥ ከተቱት፡፡ በደመወዝ ጭማሪው ሊደሰት የሚገባውን የኅብረተሰብ ክፍል ከወዲሁ አሸማቀቁት፡፡ ምን ዋጋ አለው ብሎ ከንፈሩን እንዲመጥ አስገደዱት፡፡ ይህ አሳዛኝ ድርጊት ነው፡፡ ገና ለገና ደመወዝ ሊጨመር ነው ተብሎ ወሬው እንደተሰማ ለዋጋ ጭማሪ መንቀልቀል ጤናማ የንግድ ባህሪ አይደለም፡፡ ሆኖም አደረጉት፡፡ ከሁሉም በላይ አስገራሚ