የኢህአዴግ 1 ለ 5 አደረጃጀት፣ ቀጣዩ ምርጫ እና የተቃዋሚዎች ስጋት
“በልማት ሰበብ አፈና የሚፈፀምበት መዋቅር ነው” - መኢአድ “1ለ5 አደረጃጀት ለምርጫው ስጋት አይሆንም” - አንድነት “ፓርቲያችን፤ ህዝቡ የመዋቅሩ ሰለባ እንዳይሆን የማጋለጥ ሥራ ያከናውናል” - መድረክ “ተቃዋሚዎችም እንደ ኢህአዴግ የፈለጉትን አደረጃጀት መፍጠር ይችላሉ” - መኢአብ “ኢህአዴግ አፋኝ ሚሊሻ አድርጎ ያዘጋጃቸው ናቸው” - ኢዴፓ “አደረጃጀቱን ለምርጫ ይጠቀማል የተባለው የሃሰት ውንጀላ ነው” - ኢህአዴግ ምንጭ፦ www.addisadmassnews.com መንግስት 1 ለ 5 የተሰኘውን አደረጃጀት ለፈጣን ልማታዊ እድገት እየተጠቀመበት እንደሆነ ይናገራል፡፡ በገጠር ይሄንኑ አደረጃጀት ለጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች ተጠቅሞበት ባስገኘው ውጤት፣ ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካ አገራት ምሳሌ ለመሆን መብቃቱንም በኩራት ይጠቅሳል፡፡ ተቃዋሚዎች በበኩላቸው፤ አደረጃጀቱ ፖለቲካዊ ግብን ያነገበ የስለላ መዋቅር ነው፣ የገዥው ፓርቲ የምርጫ ማስፈፀሚያና መቆጣጠሪያ መዋቅር ነው ሲሉ ይተቻሉ፡፡ ኢህአዴግ በ1 ለ 5 አደረጃጀት በመላው ሃገሪቱ የልማት እንቅስቃሴዎችን በማፋጠን ረገድ ስኬታማ እየሆንኩ ነው ቢልም ተቃዋሚዎች ግን ለአፈና እየተጠቀመበት ነው ይላሉ፡፡ “ከክልል ክልል፣ ከወረዳ ወረዳ ተዘዋውረን ህዝብን በአላማችን ስር ማሰለፍና ማደራጀት ቸግሮናል፣ አባላቶቻችንና ደጋፊዎቻችን እስራትና ድብደባን ጨምሮ ለብዙ እንግልት እየተዳረጉ ነው፣ እንኳንስ ሰፊ ህዝባዊ መሰረት ያለው አደረጃጀት ልንፈጥር በአንድ ወረዳ ውስጥ እንኳን ፅ/ቤት መክፈት አቅቶናል፣ ከአዲስ አበባ ህዝብ የማደራጀት ተልዕኮ ተሰጥቷቸው የተሸኙ አመራሮች፣ የወረዳ ሹማምንት ሰለባ ይሆናሉ” የሚሉት ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ ገበሬው 1 ለ 5 ካልተጠረነፈ፣ ማዳበሪያና ምርጥ ዘር የመሳሰሉ የግብርና ግብአቶችን ማግኘት