Posts

Image
Tourism Natural Attraction in Sidama The magnificent natural scenery & hot spring water in the Sidama zone include: Wondo Genet, Burqito Gidabo, etc.  Like wise the zone is blessed with spectacular water falls; Logita Fall Sidama 120km from Hawassa with torrential sound and Bonora Fall Sidama 135km from Hawassa cataract & blue winged birds There are two areas proposed as protected wildlife reserve that are now being delimited. Garamba   Mountain  is the highest point in the zone. It is located at a distance of 363 km from  Addis Ababa , 84 km distance from Hawassa, and also only 14 km away from Yaye (District main town). The height of the mountain is between 2800m and 3360m. The mountain is surrounded by bamboo forest; and it is convenient for tourists who have mountain trekking hobby. The mountain is home for various wildlife and bird species. There is an attractive topography round the foot of the mountain. One can watch  Bale   Mountains  from here.

ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ይርጋለም ተጉዞ ሲዳማ ቡናን 1 ለ0 በማሸነፍ ነው የዋንጫ ባለቤት መሆኑን አስቀድሞ ኣረጋገጠ

ሀዋሳ ከተማ በሜዳው ኢትዮጵያ መድህንን አስተናግዶ 1 አቻ ሲለያይ ፥ በሊጉ ግርጌ የሚገኘው ኢትዮጵያ መድህን በበኩሉ ሶስት ነጥብ ከሀዋሳ ባለማግኘቱ በሊጉ ለመቆየት የመቆየቱ ነገር አጣብቂኝ ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል የዜና ምንጭ፦  www.fanabc.com አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19፣ 2006 ( ኤ ፍ.ቢ.ሲ)   የ21ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 5 ጨዋታዎች ትናንት በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ተካሂደዋል፡፡ 5 ጨዋታዎች በቀሩት ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከወዲሁ የ2006 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑን ያረጋገጠበትን ውጤት አስመዝግቧል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ይርጋለም ተጉዞ ሲዳማ ቡናን 1 ለ0 በማሸነፍ ነው የዋንጫ ባለቤት መሆኑን አስቀድሞ ያረጋገጠው፡፡ ሀዋሳ ከተማ በሜዳው ኢትዮጵያ መድህንን አስተናግዶ 1 አቻ ሲለያይ ፥ በሊጉ ግርጌ የሚገኘው ኢትዮጵያ መድህን በበኩሉ ሶስት ነጥብ ከሀዋሳ ባለማግኘቱ በሊጉ ለመቆየት የመቆየቱ ነገር አጣብቂኝ ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል። ወላይታ ድቻ የወራጅ ስጋት የሚታይበትን ሙገር ሲሚንቶ በሜዳው አስተናግዶ 1ለ0 ማሸነፍ የቻለ ሲሆን ፥ የመውረድ ስጋት ያንዣበበበት ዳሽን ቢራ በበኩሉ ፤ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን አዲስ አበባ ስታዲዮም ላይ 1 ለ0 በመርታት ሁለተኛ ተከታታይ ወሳኝ ድሉን አስመዝግቧል፡፡ የኢትዮጵያ ቡና እና አርባምንጭ ከነማ በአበበ ቢቄላ ስታዲዮም ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ ያደረጉት ጨዋታ ሊጠናቀቅ 20 ደቂቃዎች ሲቀሩት በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት ተቋርጧል ፡፡ በጨዋታው አርባምንጭ ከነማ ከእረፍት በፊት ባስቆጠራት ግብ አንድ ለዜሮ እየመራ መዝለቅ ችሏል። በዚህ መሰረትም የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ዛሬ ከጠዋቱ 3፡00 በአበበ ቢቂላ ስታድየም የሚቀጥል

ሲአን በሀዋሳ ጽ/ቤቱ ግንቦት 16/1994 ዓ/ም በሎቄ የተጨፈጨፉ ንጹሓን የሲዳማ ልጆች 12ኛ ዓመት የመታሰቢያ ቀን በተለያዩ ዝግጅቾች አክብሮ ውለዋል

Image
ምንጭ፦  Selamu Bulado ሲአን በሀዋሳ ጽ/ቤቱ ግንቦት 16/1994 ዓ/ም በሎቄ የተጨፈጨፉ ንጹሓን የሲዳማ ልጆች 12ኛ ዓመት የመታሰቢያ ቀን በተለያዩ ዝግጅቾች አክብሮ ውለዋል!!!! በዕለቱ የተከናወኑ ድርጊቶች፦ 1ኛ) በተሳታፊዎች የህሊና ፀሎት ተደርጓል፤ 2ኛ) የእንኳን ደህና መጣችሁ እና የመክፈቻ ንግግር በዶ/ር አየለ አሊቶ ተደርጓል፤ 3ኛ) አጠቃላይ ባሁኑ ጊዜ በኢት/ያ ዘጎች ላይ በገዢው ፓርቲ እየተፈፀሙ ያሉ ኢ-ሰብዓዊና ኢ-ዴሞክራሲያ ድርጊቶች ላይ በዕለቱ እንግዳ አቶ ደጉ ደነቦ (ደቡብ የመድረክ ተወካይ) ገለጻ ተደርጓል፤ 4) የግንቦት 16/1994 ዓ/ም የሎቄ ጭፍጨፋ በማስመልከት በአቶ ለገሰ ዋንሳሞ ዋቃዮ በስፋት ገለጻ ተደርጓል፤ 5)የሲአን ትግል አመሠራረት እና ታሪካዊ አመጣጥ ላይ የቀድመው የሲአን መስራች ታጋይና ያሁኑ አመራር በአቶ አርጋታ ጉንሳ (አዱርማን) አጭር ገላጻ ተደርጓል፤ 6)በወቅቱ ሰዎች ስጨፈጨፍ አካል ጉዳተኛ ሆነው በአሁኑ ጊዜ በህይወት ያሉ አንዳንድ ግለሰቦች በገዢው ፓርቲ ላይ ያላቸውን ጥላቻ ለተሳታፊዎች ገልጸዋል፤ 7) በደምሴ ሱካሬ Qaangeemmo'ne በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ግጥም ለተሳታፊዎች ቀርበዋል፤ በመጨረሻም የሲዳማ አርነት ንቅናቄ(ሲአን) ግንቦት 16/1994 ዓ/ም ንጹሓን የሲዳማ ልጆችን በሎቄ ያስጨፈጨፉት ግለሰቦች ለፍርድ የሚቀርቡበት ጊዜ ቅርብ እንደሆነ በአቶ ደሳለኝ መሳ ለተሳታፊዎች ተገልጾ የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓት ተካሂዶ ፕሮግራሙ ተጠናቋል።

የኣለታ ላንድ ያስገነባቸውን ሶስት ፋብሪካዎች ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ በተገኙበት ልያስመርቅ መሆኑ ተሰማ

Image
የዜና ምንጭ፡ addisfortune.net Aleta Land Coffee Plc is going to inaugurate its three big factories in the Southern region of Ethiopia, in Hawassa city on Friday, May 24, 2014. According to the statement from Aleta, the inauguration ceremony will be graced by the president of the Federal Democratic Republic of Ethiopia Mulatu Teshome (PhD), the president of Hawassa and other invited ministers and guests. Aleta Land Coffee Plc was established in 2005 with an eight million dollar initial capital. The company is engaged with coffee exporting activities and providing coffee cleaning and warehousing services for other exporters. Currently, Aleta owns eight full-fledged washed-coffee factories in southern Ethiopia, particularly in the Sidamo highland areas.

መድረክ ፓርቲ በአዲስ አበባ የጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ

Image
ምንጭ፦ ሬዲዮ  ፋና  አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 16 ፣ 2006 ( ኤፍ.ቢ.ሲ. ) የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ፓርቲ ዛሬ በአዲስ አበባ የጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ። የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች መነሻቸውን ግንፍሌ ወንዝ ድልድይ ቅዱስ ማቲዎስ አንግሊካን ቤተክርስቲያን አድርገው ፥ በህንድ ኤምባሲ በመታጠፍ አቧሬ አደባባይን ፣ አድዋ ድልድይን በማቋረጥ ማጠቃለያቸውን የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 በተለምዶ ታቦት ማደሪያ እየተባለ በሚጠራው ሜዳ ላይ አድርገዋል። ሰልፈኞቹ ኢህአዴግ ለሰላማዊ ድርድር በሩን ክፍት ያድርግ ፤ በአንድነት ኢትዮጵያን እንገነባለን ፤ የፕሬስ ነፃነት ይከበር ፤ የታሰሩ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ይፈቱ ፤ መልካም አስተዳደር እውን ይሁን እና የውሃ ፣ መብራትና ስልክ አገልግሎቶች ይስተካከሉ የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል። በሰልፉ ማጠቃለያ ላይ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጎይቶም ፀጋዬ እና ዋና ፀሃፊው አቶ ገብሩ ገብረማሪያም ንግግር ያደረጉ ሲሆን ፥ ፓርቲው ባዘጋጃቸው ወቅታዊ ጥያቄዎች ላይ  ኢህአዴግ  ምላሽ እንዲሰጥ ጠይቀዋል። በአዲስ አበባና ፊንፊኔ ዙሪያ የተዘጋጀው የጋራ ማስተር ፕላን ህዝባዊ ውይይት ተደርጎበት በህዝቡ መልካም ፈቃድ ተግባራዊ ሊደረግ ይገባልም ብለዋል።