ሲኣን/መድረክ ግንቦት 16 በሃዋሳ ከተማ ሊያደርገው የነበረውን ስላማዊ ሰልፍ ለሰኔ 7 ቀን 2006 ኣስተላለፈ
የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ / ሲኣን በሃዋሳ ከተማ በወቅታዊ ጉዳዮች እና የሎቄን ሰማዕታት ቀን በሰላማዊ ሰልፍ ላማሰብ የጸጥታ ጥበቃ እንዲያደርግለት ያቀረበውን የጽሁፍ ጥያቄ የከተማው ኣስተዳደር ባለመቀበሉ የሰላማዊ ሰልፉን ቀን ወደ ሰኔ 7 ለማዛወር መገደዱ ታውቋል። ሪፖርተራችን ጥቻ ወራና ሲኣንን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ድርጅቱ ለከተማው ኣስተዳደር በጻፈው ደብዳቤ በከተማ ኣስተዳደር የተሰጠውን ምላሽ እንደምቀበል የገለጸ ሲሆን፤ የሰላማዊ ሰልፍ ማድረጊያውን ቀን ወደ ሰኔ 7 ቀን 2006 ማዛወሩን በመጠቆም በዚሁ ቀን የጸጥታ ጥበቃ እንዲደረግለት በድጋሜ ጠይቋል። ሲኣን / መድረክ ለከተማ ኣስተዳደሩ የጻፈውን ደብዳቤ ከታች ኣያይዘነዋል ያንቡት፦