ሲኣን የዛሬ 12 ኣመት በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በኣደባባይ በግፍ የተገደሉት ንጽሃን ሲዳማውያን በሰላማዊ ስልፍ ለማሰብ ያቀረበውን ጥያቄ እንደማይቀበሉ የሲዳማ ዞን እና የሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ኣስታወቁ
የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ በኣዲስቷ ሲዳማ ታሪክ ልዩ ቦታ ያለውን የሎቄ ሰማዕታት ቀን በሃዋሳ ከተማ ግንቦት ቀን 16 በሰላማዊ ስልፍ እና በሌሎች በተለያዩ ዝግጅቶች ኣስቦ ለመዋል የዝግጅት ኮሚቴ ኣቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱ የሚታወስ ሲሆን፤ የዝግጅቱ ኣንድ ኣካል የሆነው እና በሃዋሳ ከተማ ለማድረግ የታቀደው ሰላማዊ ሰልፍ በከተማው ኣስተዳደር ተቀባይነት በማጣቱ የተነሳ ላይካሄድ ይችላል ተብሏል። የሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደርን የኣገሪቱ ወቅታዊ እና መሰረታዊ ችግሮች በሰላማዊ እና ዴምክራሲያዊ ኣግባብ እንዲፈታ መንግስትን በሰላማዊ ስልፍ ለመጠየቅ የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ በጽሁፍ ያቀረበለትን ጥያቄ የጸጥታ ኃይል እጥረት ኣለብኝ በምል ምክንያት እንደማይቀበለው ለሲኣን በጻፈው ደብዳቤ ኣስታውቋል። ለተጨማሪ መረጃ የከተማ ኣስተዳደሩን እና የሲዳማ ዞን ኣስተዳደር የደብዳቤ ምላሽ ከታች ያንቡ